ደሴን ለመውረር አሰፍስፎ የነበረ አሸባሪው የህወሃት ወራሪ ኃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷልበወሎ ዩኒቨርሲቲ ፎቶ ለመነሳት ገብቶ የነበረ የጥፋት ቡድኑ ፎቶ ናፋቂም ባለበት አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ እስከወዲያኛው ተሸኝቷልየደሴ ከተማና አካባቢዋን ተቆጣጥረናል በማለት ጮኸው የሚያስጮሁ የወራሪው ወሬ አራጋቢዎችም በስፍራው እየተፋለሙ የሚገኙትን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ወኔና ጀግንነት አልተረዱም ልዩ መረጃ፤ ከጥቂት ደቂዎች በፊት ጎልጉል እንዳረጋገጠው ደሴን ያረጋጋው መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሕዝባዊ ሚሊሻና ፋኖ በርካታ አካባቢዎችን እየተቆጣጠረና በወገን እጅ ሥር እያደረጋቸው ይገኛል። በዚህም ጠላት በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመሰሰና እየሸሸ እንደሆነ ለማረጋገጥ ችለናል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ መንግሥት የትግራይ ሕዝብ ላለቁት ልጆቹ ትህነግን ለመጠየቅ እንዲዘጋጅ … [Read more...] about ደሴ በወገን እጅ – መከላከያ እየገፋ ነው!
Archives for October 2021
ጀብዱ ፈጻሚዎቹ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጦር ሜዳ ፈርጦች
ጀግኖቹ በስሌት እና በቀመር የሚተኩሱት ተተኳሽ ዶግ አመድ የሚያደርገው የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን አባላት ክምር መረማመጃ ያሳጣል፡፡ በተረበሸው የጠላት ምሽግ ዙሪያ እንደ ዘንዶ የተጠመጠሙት የእናት ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ድልን ለማጣጣም መጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል፡፡ ሴት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላትም ከወንድሞቻቸው ጋር ጠላት የገባበት ጉድጓድ ገብተው ወደ ቋመጠው ሞት በመሸኘት ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ታፍራ እና ተከብራ እንደምትኖር እያሳዩት ነው፡፡ ፈርጣማ ወታደራዊ ተክለ ቁመና እና የገዘፈ ኢትዮጵያዊ ልብ የታደሉት እነዚህ እንስቶች የሚሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት ይፈጽማሉ፤ ቆፍጣና አዋጊዎችም ናቸው፡፡ አልመው አይስቱም፤ ሽብርተኛው ትህነግ የትኛውንም ያህል ብዛት እና ብቃት አለው ብሎ የሚያሰማራውን ወራሪ ቡድን በኮንክሪት ጭምር ተጨንቆ የገነባው ምሽግ ድረስ … [Read more...] about ጀብዱ ፈጻሚዎቹ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የጦር ሜዳ ፈርጦች
ስድስተኛው የአየር ጥቃት ተደርጓል፤ አየር ኃይሉ ብቃቱን አስመስክሯል
ዛሬ መቀሌ ኵሃ አካባቢ የሚገኘው የልዩ ኃይል ፖሊስ ማሠልጠኛ ተቋም በአየር ኃይል ተመቷል። ይህ ተቋም በአሁኑ ወቅት በርካታ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች እየሰለጠኑበት ያለ ተቋም መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል። በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ የተጠኑና ወራሪው ሽብርተኛው ህወሓት ወያኔ መሳሪያ በማከማቸት የጦር ስልጠና የሚሰጥበት ቦታ ላይ የኢትዮጵያ አየር ሀይል ለ6 ተኛ ዙር ዛሬ የአየር ጥቃት አድርሷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባደረጋቸው የአየር ጥቃቶች ኢላማውን አግኝቶ መምታቱና የጠላትን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለይቶ ከጥቅም ውጪ ማድረጉ ስኬታማነቱንና በቂ ሥልጠና እንዳለው እንደሚያሳይ የቀድሞ ሠራዊት አባል ብርጋዴር ጀነራል መስፍን ኃይሌ ገለጹ። ብርጋዴር ጀነራል መስፍን በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር … [Read more...] about ስድስተኛው የአየር ጥቃት ተደርጓል፤ አየር ኃይሉ ብቃቱን አስመስክሯል
የሱዳን ወታደራዊ አመራር ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክን በቁጥጥር ሥር አደረገ
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በሀገሪቱ ወታደራዊ አመራር የቁም እስረኛ እንዲሆኑ መደረጋቸውን መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። አል ሃዲት ቲቪ እንደዘገበው ከሃምዶክ በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ኢብራሒም ለ-ሼክ፣ የመረጃ ሚኒስትሩ ሃምዛ ባሉል፣ በሚዲያ ጉዳዮች የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ፋይሳል ሞሐመድ ሳሌህ በተጨማሪ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብሏል። ከእነዚህ በተጨማሪ የገዢው ምክርቤት አፈቀላጤ ሞሐመድ አል-ፊኪ ሱሊይማን እና የዋና ከተማዋ ካርቱም ገዢ አይማን ኻሊድም መያዛቸው ተዘግቧል። ባለፈው ወር በሱዳን የመፈንቅለ መንግሥት ከተሞከረ በኋላ አገሪቱ በተቃውሞ ሰልፍና ከሚሊታሪው ጋር ሲጋጩ በነበሩ የሲቪል ማኅበረሰቦች ስትናጥ ከርማለች። እንደ አልጃዚራ ዘገባ የመገናኛ መሥመሩ በከፍተኛ ችግር ላይ ወድቋል ከሰዎች ጋርም ግንኙነት ለማድረግ በጣም አስቸጋሪ ሆኗል። … [Read more...] about የሱዳን ወታደራዊ አመራር ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክን በቁጥጥር ሥር አደረገ
ለሸኔ የጦር መሣሪያዎችን በድብቅ ለማስተላለፍ የሞከሩ ተያዙ
የሽብር ተግባር ለመፈጸምና የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን በድብቅ ለማስተላለፍ የሞከሩ የሸኔ ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢቢሲ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ሽብርተኛው ሸኔ በንፁሃን ዜጎች እና በፀጥታ አካላት ላይ ግድያ እንዲፈፅሙ መልምሎ እና ስልጠና ሰጥቶ ለጥፋት ተልዕኮ ካሰማራቸው ግለሰቦች መካከል በስሩ 5 የገዳይ ቡድን አባላትን በማደራጀት በህቡዕ ሲንቀሳቀሰ የነበረው ጃፋር መሐመድ ሳኒ የተባለው ተጠርጣሪ በተደረገበት ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ይህ የሸኔ ታጣቂ በቁጥጥር ስር የዋለው በስሩ ካደራጃቸው 5 ግብረ አበሮቹ ጋር በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ኦዳ ቡልቱም ወረዳ ሚደግዱ ቀበሌ እና ቦረማ ጫካ እንዲሁም ዳሮ ለቡ ወረዳ ሚጨታ እና በዴሳ ከተማ ውስጥ በንፁሃን ዜጎች እና በመንግሥት ፀጥታ … [Read more...] about ለሸኔ የጦር መሣሪያዎችን በድብቅ ለማስተላለፍ የሞከሩ ተያዙ
የመቀሌ አየር ድብደባዎች ዒላማቸውን የመቱ ናቸው
የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎች ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎች ላይ ብቻ እንደሆነና ኢላማቸውን የመቱ መሆናቸው ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገጽ ባወጣው መግለጫ፤ የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸውን የአየር ድብደባዎች በተመለከተ የተዛባ ግንዛቤ ቢኖርም፣ በተቃራኒው ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው ብሏል። የመከላከያ ሠራዊት የሚያከውናቸው እነዚህ ሥራዎች የሽብር ድርጅቱ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን እና ሌሎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመሸሸግ የሚጠቀምባቸውን እና ወደ ወታደራዊ መገልገያነት የቀየራቸውን የተወሰኑ ቦታዎች ከጥቅም ውጭ ለማድረግ ያለመ ነው ሲልም አስታውቋል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የመቀሌ አየር ድብደባዎች ዒላማቸውን የመቱ ናቸው
ትህነግ የዛሪማን መስጊድ አወደመ
አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የዛሪማ መስጊድን በከባድ መሳሪያ ደብድቦ ማውደሙን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አረጋ ገጠ። አሸባሪ ቡድኑ የፈጸመው ድርጊትም የሰዎችን እምነት የሚጋፋ መሆኑን ምክር ቤቱ ገልጿል። የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ሀጂ ሙሀመድ ሀሰን፣ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፣ በሰሜን ጎንደር ውስጥ በሚገኘውና በቅርብ በተገነባው የዛሪማ መስጊድ ላይ በከባድ መሳሪያ ተኩሶ መስጊዱን በከፊል አውድሟል። በአካባቢው አሸባሪው ቡድን ሸሽቶ ጫካ በመግባቱና ደብቆ ባከማቸው የከባድ መሳሪያ ከርቀት በማስወንጨፍ በዛሪማ መስጊድና በአካባቢው በሚገኙ ቤተ-እምነቶችና ንፁሀን ላይ ጉዳት እያደረሰ እንዳለ ገልጸዋል። አሸባሪ ቡድኑ የፈጸመው ተግባርም ለእምነት ክብር እንደማይሰጥ አንዱ ማሳያ መሆኑንም … [Read more...] about ትህነግ የዛሪማን መስጊድ አወደመ
ለሸኔ ሊተላለፍ የነበረ የጦር መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጋምቤላ ከተማ ለአሸባሪው ሸኔ ሊተላለፍ የነበረ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ከሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ጋር ትናንት በቁጥጥር ስር መዋሉን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ አቶ ቡን ዌው ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የጦር መሳሪያው የተገኘው በጋምቤላ ከተማ በባጃጅ ተሽከርካሪ ተጭኖ ለማስተላለፍ ሲሞከር ነው። ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋለው የጦር መሳሪያ መካከል አንድ ላውንቸር፣ አንድ ክላሽንኮቭ ከ705 ጥይት ጋር እንዲሁም 76 ዲሽቃ እንደሚገኝበት አመልክተዋል። ተጠርጣሪ ግለሰቦቹ በሰጡት ቃል ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ ለሸኔ የሽብር ቡድን ሊተላለፉ እንደነበር መናገራቸውን ኃላፊው አስረድተዋል። የክልሉ ፖሊስና የፌዴራል ፖሊስ በጋራ በመሆን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል። … [Read more...] about ለሸኔ ሊተላለፍ የነበረ የጦር መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ
በባህርዳር ከተማ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ
በባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒሊክ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ማር ዘነብ ቀበሌ ሲቱ ዋርካ አካባቢ በአንድ ተጠርጣሪ ቤት ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማና ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 3 ሺህ 676 የክላሽ ጥይት፣ 1 ሺህ 288 የመትረየስ ጥይት፣ 3 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ እና 20 የተለያዩ ሽጉጦችን ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መያዙን የ9ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ቀለሙ ረታ አስታውቀዋል። እንደ ምክትል ኢንስፔክተር ቀለሙ ረታ ገለጻ በክፍለ ከተማው ብሎም በከተማዋ መሰል ወንጀሎች ከጊዜ ወደጊዜ ተደጋግመው ቢከሰቱም በፀጥታ ኀይሉ የጠነከረ ትጋትና በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛሉ። አሸባሪው ህወሓት በየቦታው ህዝብን ለማጥፋት እሳት እያነደደ ባለበት በዚህ ጊዜ መላው ህዝብ ከፀጥታ ኀይሉ ጎን በመሆን … [Read more...] about በባህርዳር ከተማ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጉጂ 119 ኪሎ ግራም፤ በአርሲ ሦስት መኪና ጭነት አደንዛዥ እጽ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጉጂ ዞን የአዶላ ሬዴ ወረዳ በሞተር ብስክሌት ሲጓጓዝ የነበረ 119 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ እጽ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብዱልከሪም ሁሴን እንደገለጹት፤ አደንዛዥ እጹ በቁጥጥር ስር የዋለው ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ጭለማን ተገን በማድረግ ወደ ነገሌ ከተማ ሲጓጓዝ በህብረተሰቡ ጥቆማ ተደርሶበት ነው፡፡ የሰሌዳ ቁጥር በሌለው ሞተር ብስክሌት ተጭኖ በገጠር ውስጥ ለውስጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረው አደንዛዥ እጹ አዳማ ዲባ በተባለ ገጠር ቀበሌ መቆጣጠር እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡ የሞተር ብስክሌቱ አሽከርካሪ ለጊዜው ሞተሩንና አደንዛዥ እጹን ጥሎ ከአካባቢው ሸሽቶ ቢያመልጥም ለመያዝ ክትትል እየተደረገበት መሆኑን አስረድተዋል። የወረዳው ህዝብ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ላደረገው … [Read more...] about በጉጂ 119 ኪሎ ግራም፤ በአርሲ ሦስት መኪና ጭነት አደንዛዥ እጽ በቁጥጥር ስር ዋለ