34 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር አዉሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ተጠርጣሪው ግለሰብ በጥቁር ፌስታል የተጠቀለለ ነገር ይዞ ሲንቀሳቀስ መደበኛ የወንጀል መከላከል ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነስቷል፡፡ ፖሊሶቹ ባደረባቸው ጥርጣሬ ግለሰቡን ሲፈትሹት 34 ሺህ የአሜርካ ዶላር ይዞ በህገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ነው ተብሏል፡፡ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን የኑሮ ውድነት እንዲባባስ እና መንግስት ማግኘት ያለበትን ገቢ እንዲያጣ እያደረገ ይገኛል፡፡ ወንጀል ፈፃሚዎች እና ህገ-ወጥ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ አካላት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ህግን በጣሰ መልኩ እየተንቀሳቀሱ … [Read more...] about 34 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ
Archives for October 2021
በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ማን እንደሚገባ፣ እንደሚወጣና እንደሚቆይ ለማንም ማሳወቅ አይጠበቅብንም
አንድ ሀገር በግዛቷ ውስጥ ማን እንደሚገባ፣ እንደሚወጣና እንደሚቆይ የመወሰን መብቷ የተጠበቀ ነው፤ የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንን ውሳኔውን ለማንም ማሳወቅ አይጠበቅበትም ሲሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ ከተልዕኳቸው ውጪ ሲንቀሳቀሱ ከአገር እንዲወጡ የተደረጉ የተመድ ሰራተኞችን በተመለከተ ለጸጥታው ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል። አምባሳደሩ በሰጡት ማብራርያ “የዛሬው ስብሰባ መነሻ ምክንያት የአንድን ሉዓላዊት ሀገር ውሳኔ የሚጋፋ የመወያያ አጀንዳ መፍጠሩ ተገቢ ካለመሆኑ በላይ ራስን በራስ በማስተዳደር በተወሰነ ውሳኔ ላይ እንዲሁም በሉዐላዊት አገር ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው” ብለዋል። በዓለም አቀፍ ህጎች መነሻነት ኢትዮጵያ ውሳኔውን መወሰኗንም አስታውቀዋል። የተለያዩ አገራት በተለያየ … [Read more...] about በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ማን እንደሚገባ፣ እንደሚወጣና እንደሚቆይ ለማንም ማሳወቅ አይጠበቅብንም
ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚደነግጡት መቼ መቼ ነው?
የኢትዮጵያ መንግስት በውስጥ ጉዳዬ ላይ ገብተዋል፣ ከተፈቀደላቸው ዓላማና ተግባር ውጭ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል ያላቸውን 7 በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ግከለሰቦችን በ72 ሰአታት ውስጥ የኢትዮጵያን ግዛት ለቀው እንዲወጡ ሲል አዟል። ይህንን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ “በኢትዮጵያ ውሳኔ ደንግጫለሁ” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ በአሸባሪው ህወሓት በርካታ ንጹሀን ሲገደሉ፣ ከ400 በላይ መኪናዎች በአሸባሪው ድርጅት ታግተው ሲቀሩ፤ አሸባሪው ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰራሁ ነው ሲል ድምጻቸውን አጥፍተው አሁን ላይ መንግስት የአገር ሉአላዊነትን በተጋፉ የድርጅቶቱ ሰራተኞች ላይ እርምጃ ሲወስድ ደንግጫለሁ ማለታቸው ተገቢነት የጎደለው ነው ሲሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ … [Read more...] about ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚደነግጡት መቼ መቼ ነው?
ምግብ ከባዕድ ነገሮች ጋር ሲቀላቅሉ የተገኙ 23 ተቋማት ታሸጉ
በአዲስ አበባ በ2014 በጀት ዓመት ምግብ ነክ የሆኑ ግብቶችን ከባዕድ ጋር በመቀላቀላቸው 23 ተቋማት መታሸጋቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ የመድሀኒት፣ የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በምግብ እና ጤና ነክ ተቋማት ዙሪያ የቁጥጥር ሥራ እንደሚከናውን ይታወቃል፡፡ በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ በምግብ ክለሳ ላይ ሰፊ ሥራ መስራቱን አስታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት በ2014 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 146 ተቋማት ላይ በተደረገው የቁጥጥር ሥራ 23 ተቋማት መታሸጋቸውን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ የመድሀኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሙሬሳ ሚደቅሳ ተናግረዋል፡፡ ተቋማቶቹ ቂቤ፣ ማር እና የባልትና ምርቶችን ከባዕድ ነገር ጋር … [Read more...] about ምግብ ከባዕድ ነገሮች ጋር ሲቀላቅሉ የተገኙ 23 ተቋማት ታሸጉ
በአዲስ አበባ ሕገወጥ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ፍተሻ የተለያዩ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች እና ሰነዶች በቁጥጥር ስር ዋሉ። በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው 32 ቀበሌ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውሰጥ ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት በተደረገ ፍተሻ የጦር መሳሪያዎች እና ሰነዶች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ላይ ጥናት በማድረግና የፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት በተደረገ ብርበራ 85 የክላሽን-ኮቭ እና የሽጉጥ ጥይቶች፣ 3 ሽጉጦች ፣ 2 ሳንጃዎች እና 1 የእጅ ቦንብ መያዙን ነው ፖሊስ የገለፀው፡፡ በተጨማሪም 10 ሺህ የኢትዮጵያ ብር እና በርካታ ፓስፖርቶችን ጨምሮ የትምህርት ማስረጃዎች በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ውስጥ መገኘታቸውን ከአዲስ ከተማ ክፍለ … [Read more...] about በአዲስ አበባ ሕገወጥ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ