34 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር አዉሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
ተጠርጣሪው ግለሰብ በጥቁር ፌስታል የተጠቀለለ ነገር ይዞ ሲንቀሳቀስ መደበኛ የወንጀል መከላከል ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነስቷል፡፡
ፖሊሶቹ ባደረባቸው ጥርጣሬ ግለሰቡን ሲፈትሹት 34 ሺህ የአሜርካ ዶላር ይዞ በህገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ነው ተብሏል፡፡
ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር በአዲስ አበባ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን የኑሮ ውድነት እንዲባባስ እና መንግስት ማግኘት ያለበትን ገቢ እንዲያጣ እያደረገ ይገኛል፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎች እና ህገ-ወጥ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ አካላት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ህግን በጣሰ መልኩ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ፖሊስ ጠቅሷል፡፡
ህብረተሰቡ ይህን ተገንዝቦ ነገሮችን በንቃት በማስተዋል ህግን የሚተላለፉ ሰዎችን በመከታተል ተጠያቂ እንዲሆኑ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ተባብሮ እንዲሰራ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ጠይቋል፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply