የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎች ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎች ላይ ብቻ እንደሆነና ኢላማቸውን የመቱ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገጽ ባወጣው መግለጫ፤ የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸውን የአየር ድብደባዎች በተመለከተ የተዛባ ግንዛቤ ቢኖርም፣ በተቃራኒው ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው ብሏል።
የመከላከያ ሠራዊት የሚያከውናቸው እነዚህ ሥራዎች የሽብር ድርጅቱ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን እና ሌሎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመሸሸግ የሚጠቀምባቸውን እና ወደ ወታደራዊ መገልገያነት የቀየራቸውን የተወሰኑ ቦታዎች ከጥቅም ውጭ ለማድረግ ያለመ ነው ሲልም አስታውቋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Tesfa says
እናንተ ይህን የድብደባ ዜና ስታናፍሱ ሌላም ድግግሞሽ ድብደባ መፈጸሙን እየሰማን ነው። የሚገርመው እብደታችን ሰማይ ጠቀስ በመሆኑ የገነባነውን መልስን የምናወድም ጅላ ጅሎች ነን። ግን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ለትግራይ ህዝብ ነው እያለ ሰውና ሰው እንዲጫረስ ማድረጉ ምን ያህል የፓለቲካ ሰካራሞች እንደሆኑ ያረጋግጣል። ሰው በጦር መሳሪያ ሌላውን አስጎብሶ ለዘለቄታ መኖር አይችልም። ቢሞከርም ዘላቂነት የለውም። የሞከሩትም የሮም አወዳደቅን ሲወድቁ አይተናል። ለምን ይሆን ግን ከዘመን ዘመን ሰላም አጥተን ሁሌ ስንናቆር የምንኖረው? ወንድምና እህቱን ገድሎ የሚፎክር በአለም ላይ ያለ ወያኔ ሌላ ፍጥረት አይገኝም። አሁን ማን ይሙት የአማራና የአፋር ህዝብ ለትግራይ ህዝብ ጠላቱ ነው? የትግራይ ህዝብ ለእነዚህ ወገኖች ጠላት ነው? ይህ የውሸት ፓለቲካ የፈጠረው መርዝ እንጂ ሌላ አይደለም። አንድ ቤተሰብ 9 ልጆች ከወለድ በህዋላ ሳያስቡት ሌላ ተረገዘና ሰፈር ሁሉ ጉድ ሲል እናት ስም አውጭለት ትባላለች። ስሙንም በዛብኝ አለችው። እረ ይህ ስም ይቀየር ሲባል አይቻልም ከአባቱ ስም ጋር ስለሚገጣጠም ችግሬንም ሁሉንም የሚያሳይ ነው በማለት የልጅ ስም በዛብኝ በቀኑ ተባለ። አሁንም የሃበሻው ሃበሳና መከራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ነው። የጨነቀው እርጉዝ ያገባል አይነት። ይገርማል እንዴት ባለ ሂሳብ ነው ሌላው የለፋበትን ሃብትና ንብረት ወያኔ እያጨደና እየዘረፈ ወደ ትግራይ የሚያጓጉዘው? ይህ የታመመ ጭንቅላት አይደለም ለሚሉ ሁሉ እውነት ትመስክርላቸው።
ወያኔ ጊንጥ ነው በአየር ይሁን በምድር ተደበደበ በህዝብ መካከል በመደበቅና ለአለም ህዝብ የውሸትና የፈጠራ ዜናን በማሰራጨት ድረሱልኝ ማለቱ እሙን ነው። ወያኔን የሚያገለግለው የአሜሪካው CNN and BBC Online እንዲሁም ሌሎች ንፋስ ዘግነው ማእበል አመንጪ የውሸት የወሬ አውታሮች በኢትዮጵያ መንግስት የአየር ድብደባ አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት ተገደለች በማለት አናፈሱ። ይህች ያልታደለች ፍጥሩ ተጎድታ ሊሆን ይችላል። የሚገርመው ግን የኢትዮጵያ መንግስት የተከለከለ መርዝ ነክ መሳሪያ ተጠቀመ ብለውም የዘገቡም ነበሩ። ያው ወንዝ ላይ ወያኔ የጣላቸው አስከሬኖች አይነት ፓለቲካ። የሚገርመኝ ሰው ይህን ሁሉ ግፍ እያደረገ ቁጭ ብሎ እንጀራ ቆርሶ መብላቱ ነው። ከዘረኝነት የጠራ ጭንቅላት ያለው ሰው ወይ ያብዳል ወይም ይመንናል። በሰው አስከሬንና ሞት መሳለቅ የራስን አፈር መሆን መዘንጋት ነው።
ባጭሩ የሃበሻው ፓለቲካ እንደ ደ/አፍሪቃው የነጭ የዘር ፓለቲካ አፓርታይድ ነው። በክልሉ ብቻ ተወስኖ የሚኖር ከብት ብቻ ነው። የሰው ልጅ በፈለገው ተዘዋውሮ ሰርቶ ኑሮውን ያሸንፋል። የሃበሻው የዘር ፓለቲካ ሽፍላ እንደሆነ ዋናው ማሳያው ለዘራቸውና ለቋንቋቸው የሚያቀነቅኑ ሰዎች እግሬ አውጭኝ በማለት ወይም በልዪ ልዪ ብልሃት ውጭ ሃገር ወጥተው የሚኖሩት ከዝንቅና ነጻ ከሆነ ሃገርና ህዝብ ጋር ነው። በሰውኛ መለኪያ ሰውን እንደመለካት ወንዝ በማያሻግር ቋንቋ ራስን ሽፍኖ ሰውን በዘርና በጎሳ በመለየት ማሰቃየት አውሬነት ነው። አሁን በሰሜኑ የሃገራችን ክፍሎችና በሌሎችም ክልሎች የምናየው እኛ ብቻ ለእኛ ብቻ የሚል አብሮ መኖርን የገፈተረ አፓርታይድን የሚያሰፍን ጭፍን አስተሳሰብና ድርጊት ነው። ከዘመናት በፊት ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን እሳት ወይ አበባ በተሰኘው ግጥሙ አንድ ክፍል ውስጥ እንዲህ ይለናል።
እኔው ከእኔው ስከራከር
ተጨብጨ የማብላላው
ያው መቼም እኔም እንደ ሰው
የሃቅ ረሃብ ነፍሴን ሲያውከው
ልቤን ልቤ ሲሞግተው
እውነትስ ምንትስ ማን ነው?
እያለ ነው።
የእኔም ጥያቄ “እውነትስ ምንትስ ማን ነው”? መቼ ነው ከመገዳደልና መሰደድ፤ ተራብን ድረሱልን ከማለት ምድሪቱ የምታርፈው? ጠብቀን እንይ። በቃኝ!