የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በሀገሪቱ ወታደራዊ አመራር የቁም እስረኛ እንዲሆኑ መደረጋቸውን መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። አል ሃዲት ቲቪ እንደዘገበው ከሃምዶክ በተጨማሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ኢብራሒም ለ-ሼክ፣ የመረጃ ሚኒስትሩ ሃምዛ ባሉል፣ በሚዲያ ጉዳዮች የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ፋይሳል ሞሐመድ ሳሌህ በተጨማሪ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብሏል። ከእነዚህ በተጨማሪ የገዢው ምክርቤት አፈቀላጤ ሞሐመድ አል-ፊኪ ሱሊይማን እና የዋና ከተማዋ ካርቱም ገዢ አይማን ኻሊድም መያዛቸው ተዘግቧል። ባለፈው ወር በሱዳን የመፈንቅለ መንግሥት ከተሞከረ በኋላ አገሪቱ በተቃውሞ ሰልፍና ከሚሊታሪው ጋር ሲጋጩ በነበሩ የሲቪል ማኅበረሰቦች ስትናጥ ከርማለች። እንደ አልጃዚራ ዘገባ የመገናኛ መሥመሩ በከፍተኛ ችግር ላይ ወድቋል ከሰዎች ጋርም ግንኙነት ለማድረግ በጣም አስቸጋሪ ሆኗል። … [Read more...] about የሱዳን ወታደራዊ አመራር ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክን በቁጥጥር ሥር አደረገ