ዛሬ መቀሌ ኵሃ አካባቢ የሚገኘው የልዩ ኃይል ፖሊስ ማሠልጠኛ ተቋም በአየር ኃይል ተመቷል። ይህ ተቋም በአሁኑ ወቅት በርካታ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች እየሰለጠኑበት ያለ ተቋም መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።
በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ የተጠኑና ወራሪው ሽብርተኛው ህወሓት ወያኔ መሳሪያ በማከማቸት የጦር ስልጠና የሚሰጥበት ቦታ ላይ የኢትዮጵያ አየር ሀይል ለ6 ተኛ ዙር ዛሬ የአየር ጥቃት አድርሷል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባደረጋቸው የአየር ጥቃቶች ኢላማውን አግኝቶ መምታቱና የጠላትን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለይቶ ከጥቅም ውጪ ማድረጉ ስኬታማነቱንና በቂ ሥልጠና እንዳለው እንደሚያሳይ የቀድሞ ሠራዊት አባል ብርጋዴር ጀነራል መስፍን ኃይሌ ገለጹ።
ብርጋዴር ጀነራል መስፍን በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሰሞኑ የአየር ጥቃቶች ኢላማውን አግኝቶ መምታቱና የጠላትን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለይቶ ከጥቅም ውጪ ማድረጉ በራሱ ስኬታማነቱንና በቂ ሥልጠና እንዳለው የሚያመለክት ነው።
የጦርነቱ አካሄድ ከምድሩ ኃይልና ከሕዝብ ጋር የተቀናጀና የተቀናበረ ሆኖ ይታያል ያሉት ብርጋዴር ጀነራል መስፍን፤ ሂደቱ የአየር ኃይሉ በቂ ሥልጠና ያለው ኃይል መሆኑን የሚያስመሰክር ነው፤ የአየር ኃይሉንም ስኬታማነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
አየር ኃይል ፈጣን መልስ መስጠት የሚችል፣ ቦታና ጊዜ የማይገድበው የጦር ኃይል ነው። በመሆኑም ይህንን ኃይል በተለያየ የውጊያ አውድ ላይ መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል ብርጋዴር ጀነራል።
በአሸባሪው ቡድን ላይ የሚደረገውን ጥቃት ማፋጠን ያስፈልጋል። ጠላት በውዥንብር ሰውን በሚረብሽበት ቦታ ላይ በቅኝትና ከቅኝት ውጪ የሚገኝ መረጃን መሠረት በማድረግ ማጥቃት ያስፈልጋል። የምድር ኃይሉን ለማገዝ ከጠላት ውጊያ በሚገጥምበት ጊዜ የጠላትን ኃይል የመምታት እንቅስቃሴ ሊኖር ይገባል ሲሉ መክረዋል።
ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply