
የሽብር ተግባር ለመፈጸምና የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን በድብቅ ለማስተላለፍ የሞከሩ የሸኔ ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢቢሲ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ሽብርተኛው ሸኔ በንፁሃን ዜጎች እና በፀጥታ አካላት ላይ ግድያ እንዲፈፅሙ መልምሎ እና ስልጠና ሰጥቶ ለጥፋት ተልዕኮ ካሰማራቸው ግለሰቦች መካከል በስሩ 5 የገዳይ ቡድን አባላትን በማደራጀት በህቡዕ ሲንቀሳቀሰ የነበረው ጃፋር መሐመድ ሳኒ የተባለው ተጠርጣሪ በተደረገበት ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ይህ የሸኔ ታጣቂ በቁጥጥር ስር የዋለው በስሩ ካደራጃቸው 5 ግብረ አበሮቹ ጋር በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ኦዳ ቡልቱም ወረዳ ሚደግዱ ቀበሌ እና ቦረማ ጫካ እንዲሁም ዳሮ ለቡ ወረዳ ሚጨታ እና በዴሳ ከተማ ውስጥ በንፁሃን ዜጎች እና በመንግሥት ፀጥታ አካላት ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም በህቡዕ ሲንቀሳቀሰ መሆኑ ተገልጿል።
ሰሞኑን ብቻ መነሻቸውን የተለያዩ አካባቢዎችን ያደረጉ እና በአሸባሪነት ለተፈረጀው የሸኔ ቡድን እንዲደርሱ ታቅደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 40 ሺህ 621 የክላሻንኮቭ ጥይቶች፣ 499 የስናይፐር ጥይቶች፣ 4525 የብሬን ጥይቶች መያዛቸው ተገልጿል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply