ወ/ሮ ውዴ በለጠ ይባላሉ። ነዋሪነታቸው ጎንደር ከተማ ቀበሌ 17 ነው። ሀገሬ በችግር ውስጥ ሆና እኔ በድሎት አልኖርም በማለት ልጆቻቸው ለቀለብ ብለው ከሚሰጧቸው ጥቂት ገንዘብ እየቆጠቡ ለሰራዊት አባላት በግላቸው ስንቅ አዘጋጅተው አቅርበዋል። ወ/ሮ ውዴ የልጆቻቸውን እጅ ጠብቀው የሚኖሩ እናት ቢሆኑም ለህልውና ዘመቻ የሀገርን ክብርና የወገንን ህልውና ለማስጠበቅ ግንባር ለተሰለፉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የአማራ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ይሁንልኝ ሲሉ 3 ኩንታል በሶ አዘጋጅተው ድጋፍ አበርክተዋል። ግለሰቧ “ከዚህ በፊትም ልጆቼ በቻሉት አቅም ግንባር ለዘመቱ ወገኖቻቸው ድጋፍ አድርገዋል” ይላሉ። “አሁን ደግሞ የኔ ተራ ነው፤ ከወር ቀለቤ እየቀነስኩ በሰበሰብኳትና ልጆቼ በሰጡኝ ጥቂት ገንዘብ ይህንን አድርጌያለሁ” አሉ። እኔ በሰላም ወጥቼ እንዲገባ እነሱ ህይወታቸውን … [Read more...] about ከልጅ እጅ ጠብቀው፥ ከሚያገኙት ቀንሰው ለወገን ጦር ድጋፍ የቸሩ እናት
Archives for September 2021
ከ20 ቤተሰብ የመጡ 40 ወንድማማቾችና እህትማማቾች በአንድ ላይ ዘመቱ
አሸባሪውን ህወሓት የፈጸመውን ወረራ በመቀልበስ ኢትዮጵያን ለማዳን ከ20 የተለያዩ ቤተሰቦች 40 ወንድማማቾችና እህትማማቾች በአንድ ላይ ዘምተዋል። እነዚህ የኢትዮጵያ ዘማቾች ያለፈው ረቡዕ መስከረም 12፤2014ዓም ከደሴ ከተማ ወደ ስልጠና ማዕከል ሽኝት ተደርጎላቸዋል። (ኢፕድ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከ20 ቤተሰብ የመጡ 40 ወንድማማቾችና እህትማማቾች በአንድ ላይ ዘመቱ
በስልኩ ብቻ 15 የጁንታ ታጣቂዎችን ማርኮ፤ 40ዎቹን እንዲደመሰሱ ያደረገው ጀግና
ሰፊው በቀለ ናደው ይባላል። በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ ቀበሌ 03 ነዋሪ ሲሆን፤ ውልደትና እድገቱ ምንጭ ውሃ በሚባል አካባቢ ነው። ጁንታው ከነ ጀሌዎቹ ወደ ሥፍራው በመጣ ጊዜ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ለአማራ ልዩ ኃይሉ ስንቅና ትጥቅ በማቀበል ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ብዙ ተጋድሎም ፈጽሟል። አባቱ ሻምበል በቀለ ናደው የቀድሞ ሰራዊት አባል ሲሆኑ፣ አያቱም ታሪክ እንዳላቸውና የእነርሱን ታሪክ ለመድገም ቆርጦ መነሳቱን ያስታውሳል። በዚህም ያለ ጥይትና ያለ ክላሽ በያዛት ስልክ ብቻ ጠላቱን እንደተዋጋ ይናገራል። ኦፕሬሽኑን ለሚመሩት አካላት ጠላትን እየተከታተለ መረጃ በመስጠት ትልቅ ጀብዱ ፈጽሟል። ሰፊው የሹፍርና ሙያ ያለው ሲሆን፣ ጁንታዎች በመንገድ ቢያገኙት መታወቂያውን አይተው መኪና ሊያስነዱት እንደሚችሉ በማመኑ በመታወቂያው ላይ “ሹፌር” የሚለውን … [Read more...] about በስልኩ ብቻ 15 የጁንታ ታጣቂዎችን ማርኮ፤ 40ዎቹን እንዲደመሰሱ ያደረገው ጀግና
“የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ሲተኩስ ከአንገት በላይ መምታት እንዳለበት አምኖ ነው”
በጋሸና ግንባር የሚገኙ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በጠላት ላይ የላቀ የበላይነት እያገኙ እንደሆነ አባላቱና መሪዎቹ ተናግረዋል። ሳጅን ካሳዬ ወርቁ በጋይንት ግንባር ያለው የአማራ ልዩ ኃይል ተጋድሎ አኩሪ እንደነበረ ተናግሯል። ልዩ ኃይሉ ከጋሳይ ጀምሮ እስከ ደብረ ዘቢጥ ጀብድ ፈጽሟል ብሏል። የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ልዩ ኃይሉ አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድንን በተቀናጀ መልኩ እንደደመሰሱት ገልጿል። ጠላት ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ለማስረከብ እንደተገደደም አስረድቷል። ኮንስታብል አሳልፍ ተመሰለው ልዩ ኃይሉ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት የአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድንን እንደደመሰሱት ተናግሯል። የአማራ ብሎም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድን ነፃ እስኪሆኑ ድረስ ተጋድሏቸውን እንደሚቀጥሉ ነው … [Read more...] about “የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ሲተኩስ ከአንገት በላይ መምታት እንዳለበት አምኖ ነው”
“ዳፍንታም” ነኝ – ያሬድ ጥበቡ
“ጆሊው” ጀቤሳውን በአንድ ወቅት ኢትዮጵያዊነቷና “ኦሮማዊነቷ” ተምታቶባት ከነበረችው ቤተልሔም ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ አዳመጠሁት። ስለ ቤተልሔም ለመናገር ባይሆንም ዋናው ሃሳቤ፤ ቤተልሔም ከለውጡ በፊት ኦሮሞነቷን በአቅራቢያዋ የነበሩ ሰዎች እንኳን አያውቁም ነበር። በኋላ ግን እነ ጃዋር አራት ኪሎን በቅርብ ርቀት ማየት ሲጀምሩ “አኝከህ አኝከህ ወደ ወገንህ ዋጥ” ተብሎ በአማርኛ የተነገረው ብሒል ትዝ አላትና “ልትውጥ” ወደ “ዘመዶቿ” ዞር አለች። “ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን በምድር ላይ ቢኖር ኦሮሞ እንደሚሆን እርገጠኛ ነኝ” ብላ አምላክን ኦሮሞ አድርጋውም እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። ወደ ጉዳዬ ስመለስ … ቃለ ምልለሱ ሲጀመር የሚታየው አጅሬው ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) በዚያ አዛውትነቱ ነጭ ሸሚዙን ከደረቱ አጋማሽ ድረስ ከፈት አድርጎ ከውስጡ ካኔተራው እየታየ … [Read more...] about “ዳፍንታም” ነኝ – ያሬድ ጥበቡ
ልደቱ ትህነግን ለማዳን ጥሪ አቀረበ፤ አማራ የኅልውና ችግር አልገጠመውም
“አማራውም ሆነ አፋሩ ምንም ዓይነት የኅልውና አደጋ አላጋጠመውም፤ ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም በትህነግ የደረሰበት ችግር የለም፤ አማራውም ሆነ አፋሩ በትህነግ በጅምላ አልተጨፈጨፈም፤ ማይካድራ፣ ጭና፣ አጋምሳ፣ ጋሊኮማ፣ ወዘተ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተፈጸመ ጭፍጨፋ ነው እንጂ በዲሲፒሊን የታነጸው ትህነግ እንዲህ ዓይነት ግፍ አይፈጽምም፣ በአጠቃላይ “ሒሳብ እናወራርድብሃለን” የተባለው የአማራው ሕዝብ በትህነግ ምንም ግፍ አልደረሰበትም፤ ወልቃይት የምዕራብ ትግራይ አካል ነው፣ ራያም የትግራይ ነው፤ ወዘተ። ስለዚህ ትህነግ ሳትሞት በሽግግር መንግሥት ምሥረታ የአፍ ለአፍ ትንፋሽ እንስጣትና እንታደጋት”።ልደቱ አያሌው ትህነግ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ሲገባ ለመታደግ ከሚረባረቡት “ቅምጥ” ቡድኖች መካከል በቀዳሚነት የሚሰለፈው ልደቱ አያሌው ነው። ከእርሱ ሌላ የቀድሞ የትህነግ … [Read more...] about ልደቱ ትህነግን ለማዳን ጥሪ አቀረበ፤ አማራ የኅልውና ችግር አልገጠመውም
ልደቱ አያሌውን ስድስት ነገሮች ሆነው ይሆናል በሉት
አቶ ልደቱ አያሌው የፖለቲካ ህይወቱን አሀዱ ብሎ የጀመረው 1983ዓ.ም. ህወሃት/ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ የከተማዋን ወጣቶች የማደራጀት ስራ ላይ ከተሰማሩ ወጣቶች አንዱ ሆኖ ነው። በዚያ ወቅት ወጣቱ ልደቱ ለወያኔ መንግስት የመወገን ጫና በነበረበት የወጣት ማህበር ምስረታ ሂደት ንቁ ተዋናይ ነበረ። በመሆኑም የማህበሩ ሊቀመንበር የመሆን ፍላጎት እንደነበረው በወቅቱ አብረውት የነበሩ የመሰከሩት ነገር ነው። ነገር ግን በ1990 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በይፋ ሲመሰረት ወጣቱን በማደራጀት ምንም ተሳትፎ ያልነበረው የዳዊት ዮሃንስ (አፈጉባዔ የነበረ) ሚስት ወንድም የሆነው ወጣት ታጠቅ ካሳ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ። ይሄኔ ነው እንግድህ የልደቱ የመጀመሪያው የፖለቲካ አቋም እጥፋት የተጀመረው። የታጠቅን በሊቀመንበርነት መመረጥ አሚን ብሎ መቀበል አልፈለገም። … [Read more...] about ልደቱ አያሌውን ስድስት ነገሮች ሆነው ይሆናል በሉት
5 ሚሊዮን “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት” ዘመቻ ተጀመረ
ኢትዮጵያ የያዘችውን እውነታ ለዓለም የማስረዳትና የአሸባሪውን ህወሃት የጥፋት ድርጊት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳየትን አላማ ያደረገው "የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት" ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል። ዘመቻው ይፋ ሲደረግ ሚኒስትሮች፣ የተለያዩ ታዋቂ ግለሰቦችና በርካታ ወጣቶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። "የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት" ዘመቻ ከዛሬ ጀምሮ አስከ መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል። “በኢትዮጵያ ላይ በተሳሳተ መልኩ የሚነዛው አሉባልታ ከእውነት የራቀ መሆኑን ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ለማሳየት በዘመቻው ይሰራል” ተብሏል። በዚሁ ንቅናቄ ኢትዮጵያ የያዘችውን እውነታ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንዲደርስ ይሰራል ተብሏል። በዚህ ዘመቻ ከ5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። በሌላ በኩል … [Read more...] about 5 ሚሊዮን “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት” ዘመቻ ተጀመረ
ሃብትና ቀለባቸው በትህነግ ወራሪ ተዘርፎ የዕለት ጉርስ አልባ የሆኑት እማሆይ ሲሳይ ዋጋው
እማሆይ ሲሳይ ዋጋው የደብረ ዘቢጥ ከተማ ነዋሪ ናቸው። የዛሬን አያድረገውና በየዓመቱ የዘመን መለወጫ በዓል ሲመጣ ቤት ያፈራውን በማዘጋጀት በዓሉን በደስታ ያከብሩ ነበር። “የዘመን መለወጫ ለእኔ ልዩ በዓል ነበር” ያሉት እማሆይ ሲሳይ አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ከተማቸውን በወረረበት ወቅት ሀብትና ቀለባቸው በመዝረፉ በዓልን አስፈላጊውን ነገር አዘጋጅቶ በደስታ ማሳለፍ ቀርቶ የዕለት ጉርስ ማጣታቸውን ተናግረዋል። እማሆይ ሲሳይ እንዳሉት የእሳቸው ንብረት ብቻ ሳይሆን የቀበሌው ነዋሪዎች ሁሉ በሽብር ቡድኑ በመዘረፉ ችግሩን የበለጠ የከፋ ያደርገዋል። “ይህ ክፉ ጊዜ ይለፍ እንጅ በዓል ሁሌም ይደረሳል። ብቻ ሀገራችንን ሰላም ያድርጋት” ነው ያሉት። አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ከተማቸውን በወረረበት ወቅት አቅም በሌለው ጉልበታቸው ወደ ጫካ ገብተው … [Read more...] about ሃብትና ቀለባቸው በትህነግ ወራሪ ተዘርፎ የዕለት ጉርስ አልባ የሆኑት እማሆይ ሲሳይ ዋጋው
የሽብርተኛው ትህነግ ግፍና በደል በዛሪማ
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በዛሪማና አካባቢው ሰርገው በገቡባቸው ቀናት የተለያዩ ግፍና በደሎች መፈፀማቸውን ተጎጂ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በዛሪማ ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የተከራየውን ንብረትነቱ የኪዳነምህረት ገዳም የሆነ ህንፃ የሚቆጣጠሩት አባ ገብረማርያም ሳሙኤል እንደተናገሩት፣ አሸባሪ ቡድኑ እኔን እንኳ በአባትነት ሳያከብሩኝ ገፍትረው ጥለው የባንኩን ኤቲኤም ማሽን ሰብረው መዝረፋቸውንና ወደውስጥ በመግባትም የፈለጉትን አድርገው መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዛሪማ ከተማ ተወልደው ያደጉት አቶ ባዬ አትክልት እና አቶ ዳግማዊ ገነነውም የሽብር ቡድኑ ዘራፊዎች የሞቀ ቤታቸውን በማዘጋት ሱቃቸውንና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሳቸውን እንደዘረፏቸው ገልጸዋል፡፡ ቋንቋና ዘርን እየለዩ አሰቃይተውናል ያሉት አቶ ባዬ እና አቶ ዳግማዊ መሳሪያ … [Read more...] about የሽብርተኛው ትህነግ ግፍና በደል በዛሪማ