• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሃብትና ቀለባቸው በትህነግ ወራሪ ተዘርፎ የዕለት ጉርስ አልባ የሆኑት እማሆይ ሲሳይ ዋጋው

September 13, 2021 01:35 am by Editor Leave a Comment

እማሆይ ሲሳይ ዋጋው የደብረ ዘቢጥ ከተማ ነዋሪ ናቸው።

የዛሬን አያድረገውና በየዓመቱ የዘመን መለወጫ በዓል ሲመጣ ቤት ያፈራውን በማዘጋጀት በዓሉን በደስታ ያከብሩ ነበር።

“የዘመን መለወጫ ለእኔ ልዩ በዓል ነበር” ያሉት እማሆይ ሲሳይ አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ከተማቸውን በወረረበት ወቅት ሀብትና ቀለባቸው በመዝረፉ በዓልን አስፈላጊውን ነገር አዘጋጅቶ በደስታ ማሳለፍ ቀርቶ የዕለት ጉርስ ማጣታቸውን ተናግረዋል።

እማሆይ ሲሳይ እንዳሉት የእሳቸው ንብረት ብቻ ሳይሆን የቀበሌው ነዋሪዎች ሁሉ በሽብር ቡድኑ በመዘረፉ ችግሩን የበለጠ የከፋ ያደርገዋል።

“ይህ ክፉ ጊዜ ይለፍ እንጅ በዓል ሁሌም ይደረሳል። ብቻ ሀገራችንን ሰላም ያድርጋት” ነው ያሉት።

አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ከተማቸውን በወረረበት ወቅት አቅም በሌለው ጉልበታቸው ወደ ጫካ ገብተው ህይወታቸውን ማትረፍ እንደቻሉም ተናግረዋል።

“እንኳን በሕይወት ተረፍን እንጂ ሰላም ካለ በዓል በየዓመቱ ይመጣል” ብለዋል።

በወገን ኀይል ብርታት ቡድኑ ከቀያቸው ድራሹ ቢጠፋም በቤታቸው ውስጥ ምንም አይነት ቁሳቁስ እንዳልተረፈላቸው ነግረውናል። በቤታቸው ውስጥ የነበረው የዓመት ቀለባቸው ሁሉ እንደተወሰደባቸው ነው የተናገሩት።

እንኳንስ ለበዓሉ ሊደግሱ ቀርቶ ልጆቻቸውን የሚያበሉት እንደሌላቸው እማሆይ ሲሳይ አዝነው ነግረውናል።

አቅም ያለው ወገን ሁሉ ለእለት ጉርሳቸው እንዲደርስላቸውም ጠይቀዋል። ጎረቤቶቻቸውም ሆኑ የሚኖሩበት ቀበሌ እንዲሁም አካባቢያቸው ሁሉ በሽብር ቡድኑ ስለተዘረፈ ማንም ሊደግፋቸው ስለማይችል ለተጎዱት ሁሉ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊደርስላቸው እንደሚገባ ነው እማሆይ ሲሳይ የተማጸኑት።

የአሚኮ የጋዜጠኞች ቡድንም ደብረ ዘቢጥ ከተማን ጨምሮ በየአካባቢው በተዘዋወረበት ወቅት በሽብር ቡድኑ ምክንያት ኅብረተሰቡ ያለውን ቀለብና ሀብት እንደተዘረፈ ተመልክቷል። እያንዳንዱ የነዋሪዎች ቤት ውድመትና ዘረፋ እንደተፈጸመበትም በስፍራው በመገኘት አረጋግጧል። (አሚኮ:- ቡሩክ ተሾመ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, News, Social Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist, ሂሳብ እናወራርዳለን hisab enawerardalen

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule