የህወሓት የሽብር ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች አብያተ ክርስቲያንን እና መስጅዶችን ከማውደም ባሻገር እንደ ጦር ካምፕ እየተጠቀመባቸው መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ። የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውይይት መድረክ በባህርዳር እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የህወሓት የሽብር ቡድን በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት ላይ የጋረጠውን የኅልውና አደጋ ለመቀልበስ ኅብረተሰቡ በኅልውና ዘመቻው እንዲሳተፍ የሃይማኖት አባቶች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። የህወሓት የሽብር ቡድን ለመደምሰስ በሚደረገው ጥረት የሃይማኖት አባቶች የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ መሆኑን የክልሉ መንግሥት በአድናቆት ይመለከተዋል ሲሉም ተናግረዋል። ነገር ግን ጥቂትም ቢሆኑ ሽማግሌ በመምሰል ለህወሓት … [Read more...] about ትህነግ ቤተ እምነቶችን እንደ ጦር ካምፕ እየተጠቀመባቸው ነው
Archives for September 2021
በማር በበርበሬ በጤፍና በቅቤ ምርት ላይ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ባዕድ ነገሮች የቀላቀሉ ተያዙ
በደቡብ ክልል በማር፣ በበርበሬ፣ በጤፍና በቅቤ ምርት ላይ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ባዕድ ነገሮች ተቀላቅሎ ሲዘጋጅ መያዙን የደቡብ ክልል ንግድ ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ ከፋ ዞን፣ ቦንጋ ፣ጌዴኦ ዞን ፣ዲላና ሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተሞች ላይ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት በማር ፤በበርበሬ በጤፍና በቅቤ ምርቶች ላይ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ባዕድ ነገሮች ተቀላቅሎ ሲዘጋጅ መያዙን የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሽመልስ ዋንጎሬ ተናግረዋል። የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ የምግብ ምርቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከቱና እየተላመዱ መምጣታቸውን በተደረገው የዳሰሳ ጥናት መረዳት ችለናል ያሉት ኃላፊው ህብረተሰቡ ምግብና ምግብ ነክ የሆኑ ነገሮችን ሲሸምት አጢኖ ሊሆን እደሚገባም አሳስበዋል። ፎሼ የተሰኘ የጥራት … [Read more...] about በማር በበርበሬ በጤፍና በቅቤ ምርት ላይ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ባዕድ ነገሮች የቀላቀሉ ተያዙ
“የትህነግ አመራሮች አንገታቸውን በመቅላት አስከሬናቸውን ደብቋል” የዓይን እማኞች
አሸባሪው ህወሓት በደብረ ዘቢጥ ግምባር በተወሰደበት እርምጃ የተደመሰሱበትን የጦር አመራሮች አንገታቸውን በመቅላት አስከሬናቸውን እየደበቀ መሸሹን በግምባሩ ላይ በውጊያ የተሳተፉ የዓይን እማኞች ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል። በደብረ ዘቢጥ ግምባር ላይ ያሉት ሻምበል ጌታሁን ካሳዬ በስፍራው ለሚገኙት ዘጋቢዎቻችን በሰጡት መረጃ፤ በአውደ ውግያው አሸባሪው ቡድን የጦር አመራሮቹ ሲደመሰሱበት አንገታቸውን ቆርጠው በመደበቅ ማንነታቸውን ለመደበቅ እንደሚሞክሩ ተናግረዋል። እንደ ሻምበል ጌታሁን ገለጻ፤ የአሸባሪው ቡድን ከዚህ ቀደም በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት አዋጊዎቹ ሲሰው ማንነታቸው ይፋ እንዳይወጣ አንገታቸውን ይቆርጥና ይደብቅ ነበር። በህልውና ዘመቻ ወቅትም ተመሳሳይ ድርጊት በመፈጸም በተለይም በደብረ ዘቢጥ ግምባር የተሰውበትን በርካታ የጦር አመራሮች … [Read more...] about “የትህነግ አመራሮች አንገታቸውን በመቅላት አስከሬናቸውን ደብቋል” የዓይን እማኞች
ሽንፋን በአራት አቅጣጫ ከብቦ ጦርነት የከፈተው ትህነግ እርምጃ እየተወሰደበት ነው
ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም አሸባሪው እና ተስፋፊው የትህነግ ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ በተካሄደው የሕግ ማስከበር እርምጃ የተረፈው የጠላት ጦር የሸሸው ምዕራብ ጎንደርን በሚያዋስነው የሱዳን ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ነበር፡፡ ከሕግ ማስከበር እርምጃው በኋላ ላለፉት 10 ወራት በአካባቢው ጥቃት ለመሰንዘር ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ቢያደርጉም በስፍራው ባለው የወገን ጦር እየተመታ ተመልሷል፡፡ ዛሬ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የጠላት ጦር ሽንፋን በአራት አቅጣጫ በኩል በመክበብ ጦርነት ከፍቶ ነበር ያሉት የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው በሁሉም ግንባሮች በአካባቢው የጥምር ጦር አባላት ተገቢው እርምጃ ተወስዶበታል ብለዋል፡፡ በጦርነቱ የጠላትን ጦር በማገዝ እና በመምራት የአሸባሪው እና ተስፋፊው የትህነግ ቡድን ሌላኛው ሴል … [Read more...] about ሽንፋን በአራት አቅጣጫ ከብቦ ጦርነት የከፈተው ትህነግ እርምጃ እየተወሰደበት ነው
የበረከት ስምዖን “ልጅ” የ360ው ኤርሚያስ፤ ከትህነጉ ጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው
የቀድሞው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ (ትህነግ) ይመራው የነበረው የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ደኤታ የነበረው ኤርሚያስ ለገሰ ከትህነጉ አሸባሪ ጌታቸው ረዳ ጋር በተናጠል ግንኙነት እንደሚያደርግ መታወቁ ተሰማ። ቀደም ሲል ጀምሮ “እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚለው የዲጂታል ወያኔ መዋቅር የሚፈሰውን “የተመረጠ የካድሬ ቃል” ኤርሚያስ ሲጠቀም መቆየቱን የሚናገሩ በዜናው እንዳልተገረሙ ገልጸዋል። መረጃውን ይፋ ያደረገው ኢትዮ 12 ነው። በ360 “ዛሬ ምን አለ?” ዝግጅት ላይ ከሃብታሙ አያሌው ጋር በጣምራ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትህነግን አቅጣጫ እንደሚያራቡ የከሰሷቸው የነበሩ ሃብታሙም ሆነ ኤርሚያስ ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በተለያዩ አውዶች ሲናገሩና ሲጽፉ እንደነበር ይታወሳል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “ኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ” በሚል ርዕስ July 2, … [Read more...] about የበረከት ስምዖን “ልጅ” የ360ው ኤርሚያስ፤ ከትህነጉ ጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው