አሸባሪው ህወሓት በደብረ ዘቢጥ ግምባር በተወሰደበት እርምጃ የተደመሰሱበትን የጦር አመራሮች አንገታቸውን በመቅላት አስከሬናቸውን እየደበቀ መሸሹን በግምባሩ ላይ በውጊያ የተሳተፉ የዓይን እማኞች ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል።
በደብረ ዘቢጥ ግምባር ላይ ያሉት ሻምበል ጌታሁን ካሳዬ በስፍራው ለሚገኙት ዘጋቢዎቻችን በሰጡት መረጃ፤ በአውደ ውግያው አሸባሪው ቡድን የጦር አመራሮቹ ሲደመሰሱበት አንገታቸውን ቆርጠው በመደበቅ ማንነታቸውን ለመደበቅ እንደሚሞክሩ ተናግረዋል።
እንደ ሻምበል ጌታሁን ገለጻ፤ የአሸባሪው ቡድን ከዚህ ቀደም በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት አዋጊዎቹ ሲሰው ማንነታቸው ይፋ እንዳይወጣ አንገታቸውን ይቆርጥና ይደብቅ ነበር። በህልውና ዘመቻ ወቅትም ተመሳሳይ ድርጊት በመፈጸም በተለይም በደብረ ዘቢጥ ግምባር የተሰውበትን በርካታ የጦር አመራሮች አንገታቸውን በመቁረጥ እጅግ አስነዋሪ ተግባር እየፈጸመ ይገኛል።
ይህ የጠላት ቡድን ህጻናትን ፊት ለፊት በማሰለፍ እያስፈጃቸው ነው ያሉት ሻምበል ጌታሁን፤ በግምባሩ በኢትዮጵያ ሰራዊት በተወሰደበት ከፍተኛ ጥቃት በርካታ የጦር መሪዎቹም ተደምስሰውበታል። እውነቱ ይፋ እንዳይወጣ በሚልም የለመደውን አንገት የመቁረጥ ተግባር መፈጸሙን ገልጸዋል።
የሚሊሻ ቡድኑን ተቀላቅሎ በደብረ ዘቢጥ በግምባር ለውግያ የተሰለፈው ሰፊው በቀለ አሸባሪው በአውደ ውግያው ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት ስለመሆኑ ይናጋራል።
የጦር አመራሮቹ ጭምር እየተመቱ እንዳሉና በተለይም የተሰውበትን አመራሮች ዘግናኝና ኢ ሰብዓዊ በሆነ መልኩ አንገታቸውን በመቅላት ማንነታቸው እንዳይታወቅ በማድረግ ጥለው ከሸሿቸው አስከሬኖች መመልከቱን ገልጾልናል። (ኢ.ፕ.ድ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ከዝግጅት ክፍሉ፤ አንገታቸው የተቆረጡ የትህነግ ሰዎች ፎቶ ቢኖሩንም ከጋዜጣችን ሥነምግባር አንጻር አግባብ ስላልሆነ አላተምነውም።
Leave a Reply