
የህወሓት የሽብር ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች አብያተ ክርስቲያንን እና መስጅዶችን ከማውደም ባሻገር እንደ ጦር ካምፕ እየተጠቀመባቸው መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ።
የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውይይት መድረክ በባህርዳር እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የህወሓት የሽብር ቡድን በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት ላይ የጋረጠውን የኅልውና አደጋ ለመቀልበስ ኅብረተሰቡ በኅልውና ዘመቻው እንዲሳተፍ የሃይማኖት አባቶች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የህወሓት የሽብር ቡድን ለመደምሰስ በሚደረገው ጥረት የሃይማኖት አባቶች የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ መሆኑን የክልሉ መንግሥት በአድናቆት ይመለከተዋል ሲሉም ተናግረዋል።
ነገር ግን ጥቂትም ቢሆኑ ሽማግሌ በመምሰል ለህወሓት የሽብር ቡድን እኩይ ዓላማ ተባባሪ የሆኑ አሉ ብለዋል።
እነዚህ በሃይማኖት ስም የሚነግዱ እና የጥፋት ቡድኑ ተላላኪዎች ላይ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።
የሃይማኖት አባቶች በበኩላቸው የህወሓት የሽብር ቡድንን ለመደምሰስ በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። (ኢብኮ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply