በማይጠብሪ ግንባር የሚገኘው የወገን ጦር ጠላትን እየደመሰሰ ወደ ፊት እየገሰገሰ ነው። በጭና ቆርጦ ደባርቅና ዳባትን ሊይዝ የነበረው የትግራይ ወራሪ ቡድን በጭና እና በተለያዩ አካባቢዎች ድባቅ ተመትቶ አብዛኛው ተደምስሷል። የቀረው ወደ ኋላ በመመለስ ወደ መጣበት እየፈረጠጠ ነው። በግንባሩ የተሰማራው የወገን ጦርም እየተከታተለ እየደመሰሰው ነው። በግንባሩ የክፍለ ጦር አዛዥ እንደነገሩን ሠራዊቱ በቦዛ፣ በጭና፣ በብና እና በተለያዩ አካባቢዎች ከባድ ጦርነት ማድረጉን ነው የተናገሩት። በተደረገው ጦርነትም የጠላት ቡድን ተደምስሷል። በዛሪማና በድብ ባሕር አድርጎ ወደ ሊማሊሞ ሊወጣ የነበረው አሸባሪ ቡድንም በወገን ጦር ተመትቷል ነው ያሉት። ከድብ ባሕር እስከ ዛሪማ እየተቀጠቀጠ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ መመለሱን ነው የተናገሩት። ጠላት መልሶ እንዳይቋቋም ካደረጉት ምቶች መካከል … [Read more...] about የዛሪማን ድልድይ በውስጥ በኩል ቦርቡሮ ፈንጅ ለመደበቅ ያሤረው ጠላት ተደምስሷል
Archives for September 2021
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል መተከል ዞን ገባ
የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ወደ ቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ እንደገባና አቀባበል እንደተደረገለት ቡለን ወረዳ አሳውቋል። የቡለን ወረዳ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ፥ "ለዘላቂ ሰላም የሚንቀሳቀሰው የአማራ ክልል ልዩ ሀይል በቡለን ከተማ አቀባበል ተደርጎለታል" ሲል ፅፏል። ወረዳው በአቀባበሉ ላይ የቡለን ወረዳ ወጣቶች፣ ነዋሪው፣ ማህበረስቡና የሴክተር መስርያ ቤት ሰራተኞችና አመራሩን ጨምሮ ከከተማው 1 ኪ/ሜትር ወጣ ብሎ በመሄድ አቀባበል አድርገዋል ሲል ገልጿል። የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ወደቡለን ወረዳ መግባቱ በወረዳው ያለውን የፅጥታ ችግር ለመፍታት፣ ማህበረሰቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ለማድረግ አስተዋጽዖ ያደርጋል ተብሏል። ቡለን ወረዳ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ውስጥ የፀጥታ ስጋት ካለባቸው ወረዳዎች አንዱ ሲሆን በተደጋጋሚ ጊዜ … [Read more...] about የአማራ ክልል ልዩ ኃይል መተከል ዞን ገባ
CNN ትህነግን እንደ ማስረጃ ጠቅሶ የሠራው ዘገባና ያፈተለከው ቅሌት
ሲኤንኤን (CNN) “አሰቃቂው ዕይታ” የሚል ርዕስ የሰጠውን እና በሁመራ ተፈፅሟል ያለውን ግርፋት፣ ጅምላ እስር እና ግድያን በተመለከተ የምርመራ ዘገባ አቅርቧል። እነዚህ ግርፋት፣ ጅምላ እስር እና ግድያ የተፈፀሙት “በኢትዮጵያ ሠራዊት እና አጋሮቹ” ሲል በገለጻቸው ኃይሎች መሆኑንም ምስክሮቹን ጠቅሶ ደምድሟል። የዚህ የምርመራ ዘገባ መነሻ የሆነው በሱዳን ድንበር አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ላይ የሚንሳፈፉ አስከሬኖች ዳግም መገኘታቸው እንደሆነ ሚዲያው ጠቅሷል። ኒማ ኤልባጊር ይሁን እንጂ የዘገባው አዘጋጅ የሆነችው ሱዳናዊቷ ጋዜጠኛ ኒማ ኤልባጊር ለምስክርነት የመረጠቻቸው ሰዎች ገለልተኛ አለመሆን እና የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ደጋፊዎች መሆናቸው የዘገባውን ተዓማኒነት አጠያያቂ አድርጎታል። በተለይ ተፈፅመዋል የተባሉትን ግድያዎች በዝርዝር የሚናገረው እና የሞቱ ሰዎች … [Read more...] about CNN ትህነግን እንደ ማስረጃ ጠቅሶ የሠራው ዘገባና ያፈተለከው ቅሌት
ሲራጅ ዲቢል አሊ 5 ገድለው 6 ክላሽ የማረኩ የድሬ ሮቃው ጀግና
ስማቸው ሲራጅ ዲቢል አሊ ይባላሉ። በሀብሩ ወረዳ 024 ድሬ ሮቃ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው። ከሰሞኑ አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን ወደ ቀበሌያቸው ለመግባት ሲሞክር ቀበሌያቸውን ባለማስደፈር ታላቅ ጀብዱ ሰርተዋል። በሚኖሩበት ድሬ ሮቃ ቀበሌ ግንባር ላይ በመሰለፍ አንድ የአሸባሪው ቡድን አባል በወገን ጦር ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሲሞክር በድንጋይ አንገቱን ብለው የያዘውን ክላሽ ማርከውታል። ከዚያም ሌሎች አምስት የአሸባሪው ቡድን አባላት ጓደኛቸውን ለማንሳት ሲመጡ አምስቱንም በመግደል የያዙትን አምስት ክላሽ በመማረክ በአጠቃላይ 6 ክላሽ ከአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድን መማረክ ችለዋል። በሃይማኖቴ እና በኢትዮጵያዊነቴ አልደራደርም የሚሉት አቶ ሲራጅ ወጣቱ የሀገሩን ሰላም እንዲጠብቅ ጥሪ … [Read more...] about ሲራጅ ዲቢል አሊ 5 ገድለው 6 ክላሽ የማረኩ የድሬ ሮቃው ጀግና
❝አላህ ይፍረደኝ የልጆቼን አባት አንገላተው ገደሉት፤ ጅብ አስበሉት ብጥስጣሽ ልብሱ ውርማ ተገኘ❞ ወ/ሮ ጦይባ
አሸባሪው የትህነግ ቡድን መግደል ብቻ ሳይሆን የቤተሰቦቻችንን አስክሬን ጅብ አስበልቶ የግፍ ግፍ ፈጽሞብናል ሲሉ የወረባቦ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ። አሸባሪው የትህነግ ቡድን በወረባቦ ወረዳ ህጻናትን፣ ሴቶችን፣ አርሶአደሮችን በግፍ ገድሏል፤ ሃብትና ንብረት ዘርፏል ብሎም አውድሟል። በወረባቦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ካሊድ ሙሐመድ የተመራ ልዑክ አሸባሪው ትህነግ በወረዳው ጥቃት ያደረሰባቸውን፣ ንብረታቸው የተዘረፈባቸውንና የወደመባቸውን ወገኖች ተመልክቷል፡፡ በሰው ደም የሰከረው ሽብርተኛው የትህነግ ቡድን በየደረሰበት ሁሉ የጥፋት ሰይፉን እየመዘዘ ንጹሐንን ገድሏል። ለአማራ ያለውን ስር የሰደደ ጥላቻ በሚፈጽመው እኩይ ድርጊት እያሳየ ይገኛል። በሁሉም ግንባሮች ከፍተኛ ሽንፈት ሲደርስበት ኀይሉን አሰባስቦ ደሴ፣ ሐይቅና ኮምቦልቻን መዳረሻዎቹ ሊያደርግ በደቡበ ወሎ በወረባቦ … [Read more...] about ❝አላህ ይፍረደኝ የልጆቼን አባት አንገላተው ገደሉት፤ ጅብ አስበሉት ብጥስጣሽ ልብሱ ውርማ ተገኘ❞ ወ/ሮ ጦይባ
ባለፉት 100 ዓመታት ያልተገነባ ሠራዊት ለመገንባት እየሠራን ነው – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የ2014 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ከሠራዊቱ ጋር ለማክበር ማይጠብሪ ግንባር ተገኝተዋል። በማይጠብሪ ግንባር ከሠራዊቱ ጋር በዓልን ለማክበር የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ፣ ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌትናል ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የመከላከያ ኅብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሜጄር ጄኔራል ዘውዱ በላይ፣ የምእራብ እዝ እና የማይጠብሪ ግንባር አዛዥ ሜጄር ጄኔራል መሠለ መሠረት ጨምሮ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተገኝተዋል። የሠራዊት አባላት ተልዕኳቸን በላቀ ብቃት በመወጣት በአዲሱ ዓመት በሀገራችን አስተማማኝ ሠላም እናሰፍናለን ብለዋል። ሕዝባችን ያሳየንን ከፍተኛ ድጋፍ የሞራል ስንቅ አድርገን በአዲሱ ዓመት ለሕዝባችን ታላላቅ የድል ብሥራቶችን ለማሰማት እንዘጋጅ … [Read more...] about ባለፉት 100 ዓመታት ያልተገነባ ሠራዊት ለመገንባት እየሠራን ነው – ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
የአንድ ዓመት ደመወዙን ለመከላከያ ሰራዊት የለገሰው ዶክተር
በሚሰራበት የአዋሳ ከተማ አዳሬ ጠቅላላ ሆስፒታል ዶክተር ኤልያስ ጉልማ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስትና የልብ ምርመራና ህክምና ባለሙያ ሆኖ ከማገልገሉ ባለፈ በደቡብ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል በተደራቢነት ያገለግላል፡፡ ሃገርን በማትተካው እናት የሚመስላት ዶክተር ኤሊያስ እናት ስትቸገር ማየት ህመሙ ከባድ እንደሆነ በመግለጽ ሃገሬ የሆነችልኝ ከቃልም ከአድራጎትም በላይ በመሆኑ ሁለንተናዬን አሳልፌ ለመሰጠት ዝጉጁ ነኝ ብሏል፡፡ በዱር በገደል ውድ ህይወቱን እየሰዋ ሃገር ለሚያቆመው የመከላከያ ሃይል መላው ህዝባችን ተከፍሎ የማያልቅ ብድር አለበትም ብሎ ያምናል ዶ/ር ኤልያስ፡፡ በተለይም በአሁኑ ሰዓት እናት ሃገር ኢትዮጵያ የገጠሟትን ችግሮች ለመፍታት አድረን ለመገኘት የምንሳሳላትን ነፍስ እየሰጠ ትውልድ የሚያስቀጥለውን የመከላከያ ሃይል መርዳትና በምንችለው ሁሉ አብሮነታችንን መግለፅ … [Read more...] about የአንድ ዓመት ደመወዙን ለመከላከያ ሰራዊት የለገሰው ዶክተር
ኢትዮጵያ ለሩሲያ ሁልጊዜም ዋንኛ አጋር ሀገር ነች – በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር
የኒውክለር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ ለመዋል ሩሲያና ኢትዮጵያ ትብብር አድርገዋል ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በመተማመን ላይ የተመሰረተ አጋርነት እና መልካም ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸው በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ተረክህን ተናግረዋል፡፡ የሀገራቱ ግንኙነት በሁለትዮሽ መከባበር እና መረዳዳት እንዲሁም አጋርነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡ አምባሳደር ኤቭጌኒ ተረክህን እንደገለጹት አሁን ትኩረታችን በንግድ እና በኢኮኖሚ ዘርፍ ትብብርን ለማስፋት እና ዲፕሎማቲክ ግንኙነታችንን ለማጠናከር ነው ብለዋል፡፡ የኒውክለር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ ለመዋል ወሳኝ የሁለትዮሽ ፕሮጀክት ትብብር መደረጉን አስታውሰዋል፡፡ ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ማህበራዊ እና ኢኮኖሚ ልማትን ለማፋጠን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ለሩሲያ ሁልጊዜም ዋንኛ አጋር ሀገር ነች – በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር
ከብርሸለቆ ውትድርና ማሰልጠኛ ተመርቀው ለግዳጅ የተዘጋጁት ባልና ሚስት
በትዳር ዓለም ለአንድ ዓመት ያህል የቆዩት ሮዛ አህመድ እና ኤሊያስ አባሜጫ የኢትዮጵያ ነገር አይሆንላቸውም። ጣፋጭ ጊዜያቸውን በቤታቸው ቁጭ ብለው ሲያሳልፉ የነበሩት ጥንዶቹ የእናት ሀገርን የሕልውና ጥሪ ሲሰሙ ልባቸው ለዘመቻ መነሳሳቱን ይናገራሉ። "እኛስ ለምን መከላከያ ሠራዊቱን ተቀላቅለን ሀገራችንን አናገለግልም?" የሚል ሃሳብ ያድርባቸዋል። ጥንዶቹ በጉዳዩ ላይ በበቂ ሁኔታ ከመከሩ በኋላ ጅማ ዞን በሚገኝ አንድ ጣቢያ ሄደው ለውትድርና እንደተመዘገቡ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች ተናግረዋል። የአጋጣሚ ነገር ሆነና ጥንዶቹ ለውትድርና ስልጠናው ወደብርሸለቆ ማሰልጠኛ አንድ ላይ ገቡ። አሁን ላይ ጥንዶቹ ስልጠናቸውን አጠናቀው በመሰረታዊ ወታደርነት በመመረቃቸው ለዘመቻ ዝግጁ ሆነዋል። "ከዚህ በኋላ ዓላማችን ሁሉ የሀገር ጠላት የሆነውን ከሃዲ ቡድን … [Read more...] about ከብርሸለቆ ውትድርና ማሰልጠኛ ተመርቀው ለግዳጅ የተዘጋጁት ባልና ሚስት
ልዩ ልዩ የጦርነት ጀብዱዎችና የትህነግ ግፍ
የአፋር ክልል ልዩ ሀይል አባል የሆነው ሁመድ አሊ የአፋር ክልልን ለመውረር የመጡ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎችን ሲፋለም ጥይት በመጨረሱ በታጠቀው ጊሌ ታንክ የማረከ ጀግና ወጣት ነው! ህጻናት የታቀፉ ወላጆችን በግፍ የረሸነው አሸባሪው የህወሓት ቡድን ህጻን አማን እና ወንድሞቹን ያለወላጅ አስቀርቷል። ህጻና አማን በእናትና አባቱ አስከሬን መካከል በደም ተነክሮ ነው የተገኘው። የእናቱን ሞት አይቷል። የወላጅ እናቱን አስከሬን ታቅፎ ተገኝቷል። ይህ የጭካኔ ጥግ ሂሳብ እናወራርዳለን በሚል የአሸባሪው ቡድን አመራሮች ተናግረው በአማራ ክልል ወረራ ከፈጸሙ በኋላ የፈጸሙት የሽብር ተግባር ነው። "ኢትዮጵያዊያን እያለን አሸባሪው ህወሓት እንጂ አገር አትፈርስም"፦ ዘማቹ ረዳት ፕሮፌሰር የሕልውና ዘመቻ ጥሪውን ተቀብለው በግንባር የሚገኙት ረዳት ፕሮፌሰር ጌትነት … [Read more...] about ልዩ ልዩ የጦርነት ጀብዱዎችና የትህነግ ግፍ