ስማቸው ሲራጅ ዲቢል አሊ ይባላሉ። በሀብሩ ወረዳ 024 ድሬ ሮቃ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው። ከሰሞኑ አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን ወደ ቀበሌያቸው ለመግባት ሲሞክር ቀበሌያቸውን ባለማስደፈር ታላቅ ጀብዱ ሰርተዋል።
በሚኖሩበት ድሬ ሮቃ ቀበሌ ግንባር ላይ በመሰለፍ አንድ የአሸባሪው ቡድን አባል በወገን ጦር ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሲሞክር በድንጋይ አንገቱን ብለው የያዘውን ክላሽ ማርከውታል። ከዚያም ሌሎች አምስት የአሸባሪው ቡድን አባላት ጓደኛቸውን ለማንሳት ሲመጡ አምስቱንም በመግደል የያዙትን አምስት ክላሽ በመማረክ በአጠቃላይ 6 ክላሽ ከአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድን መማረክ ችለዋል።
በሃይማኖቴ እና በኢትዮጵያዊነቴ አልደራደርም የሚሉት አቶ ሲራጅ ወጣቱ የሀገሩን ሰላም እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።
አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን በርካታ ሕዝብ አሰልፎ ድሬ ሮቃን ለመያዝ ቢመኝም በቀበሌው ነዋሪዎችና በመከላከያ ሠራዊት ጥቃት ህልም ሆኖበት ወደመጣበት ተመልሷል ብለዋል።
የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ ሸህ ሀሰን ከረሙ አሸባሪ ቡድኑ እኛን አልፎ እንዲሄድ አንፈቅድለትም፣ በቀጣይም ለሀገራችን መስዋእትነት እንከፍላለን ብለዋል። (አሚኮ – ተመስገን አሰፋ – ከድሬ ሮቃ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply