
የኒውክለር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ ለመዋል ሩሲያና ኢትዮጵያ ትብብር አድርገዋል
ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በመተማመን ላይ የተመሰረተ አጋርነት እና መልካም ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸው በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ተረክህን ተናግረዋል፡፡
የሀገራቱ ግንኙነት በሁለትዮሽ መከባበር እና መረዳዳት እንዲሁም አጋርነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡
አምባሳደር ኤቭጌኒ ተረክህን እንደገለጹት አሁን ትኩረታችን በንግድ እና በኢኮኖሚ ዘርፍ ትብብርን ለማስፋት እና ዲፕሎማቲክ ግንኙነታችንን ለማጠናከር ነው ብለዋል፡፡
የኒውክለር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ ለመዋል ወሳኝ የሁለትዮሽ ፕሮጀክት ትብብር መደረጉን አስታውሰዋል፡፡
ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር ማህበራዊ እና ኢኮኖሚ ልማትን ለማፋጠን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ ለማስተዋወቅ እየሰራች ነው ሲሉ አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡
በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የያዝነው አቋም የማይቀየር ነው ያሉት አምባሳደሩ ዓለም አቀፍ ህጎችን በጠበቀ መልኩ ሶስቱ ሀገራት በራሳቸው መፍትሔ ሊያበጁ ይገባል ብለዋል፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በተመለከተ ይህ ውስጣዊ ጉዳይ ስለሆነ የራስን ጉዳይ በራሳቸው በኢትዮጵያዊያን የሚፈታ ይሆናል ብለዋል፡፡
በክልሉ እያጋጠመ ያለው የሰብዓዊ እርዳታ ችግር ያሳስበናል ያሉት አምባሳደሩ፣ የሰብአዊ ቀውሱን ለመፍታት የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡ (EBCNEWS)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply