የፌዴራል መርማሪ ፖሊስ በአቶ ጃዋር ሲራጅ መሃመድ ቤት በድጋሚ ባደረገው ፍተሻ በግለሰብ እጅ የማይገኙ ሳተላይቶችና ከውጭ በድብቅ የገቡ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ማግኘቱን ገለጸ። መርማሪ ፖሊስ በሃምሌ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. በፍርድቤቱ በተሰጠው የ13 ቀን ተጨማሪ ጊዜ የሠራውን አዳዲስ የምርመራ ሥራዎችን ይፋ አድርጓል። መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 13 ቀናት ሰራው ያለው አዲስ ሥራ፤ በአቶ ጃዋር ቤት በድጋሚ በተደረገው ፍተሻ የቴሌኮም መሳሪያዎች፣ በግለሰብ እጅ የማይገኙ የኤሌክትሮኒክስና የሳተላይት ዲሾችን ጨምሮ ሌሎችንም አግኝቷል። መሣሪያዎቹ ከውጭ በድብቅ መግባታቸውና ከውጭ ሀገር ባለሞያ አስመጥተው በድብቅ ማስገጠማቸውን ጠቅሷል። በመሣሪያው የታዋቂ ሰዎችን ስልክ በመጥለፍ ሚስጥራዊ ንግግራቸውን ያዳምጡ እንደነበር ማስረጃ ሰብስቢያለሁ ብሏል።አቶ ጃዋር ጋር የተገኙት … [Read more...] about ፖሊስ፤ “(ጃዋር) የታዋቂ ሰዎችን ስልክ” ጠልፎ ነበር
Archives for July 2020
ፖሊስ፤ በቀለ ከጳውሎስ ሆ/ል እስከ ቡራዩ ኬላ የአመፅ ጥሪ በስልክና በአካል አስተላልፏል
በቀለ፤ የታሰርኩበት ቦታ ቴሌቪዥን ስለሌለ እንዲፈቀድልኝ ፍርድቤቱ ትዕዛዝ ይስጥልኝ “እንድታሰር የተደረገው ፖለቲከኛ በመሆኔ በምርጫ እንዳልወዳደር ነው” ተጠርጣሪ አቶ በቀለ ገርባ“መንግሥት የተፈጠረን ወንጀል ያጣራል እንጂ ወንጀል ፈጥሮ አያስርም” የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መርማሪ ቡድን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን አቶ በቀለ ገርባ በድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ሽኝት ወቅት ከጳውሎስ ሆስፒታል እስከ ቡራዩ ኬላ ድረስ አብረው እንደነበሩ፣ የአመፅ ጥሪ በስልክና በአካል ሲያስተላልፉ እንደነበር በማስረጃ ማረጋገጡን ለፍርድ ቤት አስታወቀ። በሁከቱ በደረሰው የሰዎች ሞትና የንብረት ውድመት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኦፌኮ አመራር አቶ በቀለ ገርባ ግን፣ “መርማሪ ቡድኑ አንድ ጊዜ በስልክ ትዕዛዝ ሰጠ ይላል። በሌላ ጊዜ ደግሞ በአካልና በስልክ የአመፅ ጥሪ … [Read more...] about ፖሊስ፤ በቀለ ከጳውሎስ ሆ/ል እስከ ቡራዩ ኬላ የአመፅ ጥሪ በስልክና በአካል አስተላልፏል
ችሎት! ሃምዛ፣ የህወሓት አመራሮች፣ ይልቃልና እስክንድር
በወንጀል ተጠርጣሪ ሃምዛ ቦረና በአቶ ሃምዛ ቦረና መዝገብ የተካተቱ 9 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። መርማሪ ፖሊስ የሰራውን ተጨማሪ የምርመራ ስራ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከዘጠኙ ተጠርጣሪዎች መካከል ስምንቱ የአቶ ጃዋር መሃመድ ጠባቂዎች ሲሆኑ በፖሊስ ምርመራ ላይ መቃወሚያ አቅርበዋል። መርማሪ ፖሊስ ሌሎች በርካታ የሰዎች እና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሳብ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ ብሎ ጠይቋል። ፍርድ ቤት ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን ጊዜ ውስጥ 8 ቀን ፈቅዶ ተለዋጭ ቀጠሮ ለሃምሌ 29/2012 ዓ/ም ሰጥቷል። መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 11 ቀናት፤ በተጠርጣሪዎች ላይ የተያዙ መሳሪያዎችን ምርመራ አድርጓል፤ 10 የተከሳሽ ፤ 20 የምስክር ቃል ተቀብሏል።አንደኛ ተጠርጣሪ አቶ ሃምዛ ቦረና የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ብሄርን ከብሄርና የሃይማኖት ግጭት … [Read more...] about ችሎት! ሃምዛ፣ የህወሓት አመራሮች፣ ይልቃልና እስክንድር
የሕገወጥነት ጽንፍ ሰለባዎች
ዕለተ ዓርብ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም. በቃሊቲ አውቶቡስ መናኸሪያ የተገኘነው ማልደን ነበር። መናኸሪያው እንደ ወትሮው ግርግር አይታይበትም። አለፍ አለፍ እያሉ ወደ መናኸሪያው የሚገቡ ሰዎችም በቀጭን ገመድ ራሳቸውን ከልለው የኮሮና ሙቀት በሚለኩ ሰዎች እየተፈተሹ ይገባሉ። ምንም ዓይነት የቅድመ ጥንቃቄ የምክር አገልግሎት ሲሰጥ ግን አላየንም። አውቶቡሱ ከመነሳቱ በፊት ረዳቱ በር ላይ የተለካውን የሰውነት የሙቀት ልኬት የተነገረንን ውጤት እየመዘገበ ወደ ውስጥ ማስገባት ጀመረ። ባስ ውስጥ ሦስት ሰዎች ሳይመረመሩ ገብተው ነበረና በግምት ሲሞላ በማየታችን ሁኔታው ትክክል እንዳልሆነ አስረድተን ተሳፋሪዎቹ ሙቀታቸውን እንዲለኩ በማድረግ ጉዞዋችንን ጀመርን። የባስ ውስጥ አቀማመጣችን ያው እንደ ከተማው ትራንስፖርት በወንበር አንድ ሰው ነው። ከእኔ በስተቀኝ ከተቀመጡት … [Read more...] about የሕገወጥነት ጽንፍ ሰለባዎች
የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም የጣራና የማጠቃለያ ግንባታ በይፋ ተጀመረ
በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ገርጂ አካባቢ በቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ስራ ተቋራጭነት በMH ኢንጅነሪንግ አማካሪነት እየተገነባ የሚገኘው ብሔራዊ ስታዲየም በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተገነባ ይገኛል። የስታዲየሙን የጣራ እና የማጠቃለያ ግንባታ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እንዳሉት በሀገራችን የነበረው ብቸኛው ስታዲየም የአዲስ አበባ ስታዲየም እንደነበር ጠቁመው በአሁኑ ሰዓት በሁሉም የሀገራችን ክልሎች ከ12 በላይ ስታዲየሞች በመገንባት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል። እነዚህ ስታዲየሞች ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም መንግስት ለስፖርት ሴክተር በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በከፍተኛ … [Read more...] about የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም የጣራና የማጠቃለያ ግንባታ በይፋ ተጀመረ
“የፌዴራል መንግሥት በትግራይ የሆነ ዕርምጃ እወስዳለሁ ካለ ራሱ ያደርገዋል”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት በፋና ቴሌቪዥን በትግርኛ ቋንቋ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። ከተነሱት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ለውጡና የትግራይ ክልል ሁኔታ፣ የድምፂ ወያነና የትግራይ ቴሌቪዥን መዘጋት፣ ምርጫን በተመለከተ፣ የኤርትራ ጉዳይና የፌዴራል መንግሥት ትግራይን ሊያጠቃ ነው ስለመባሉ ይገኙበታል። በማብራሪያቸው የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች እንደሚከተለው ተጠናቅረዋል። ለውጡና የትግራይ ክልል ሁኔታ “የትግራይ ሕዝብ የማይሳተፍበት ፖለቲካ በኢትዮጵያ ይኖራል የሚል እምነት የለኝም። ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ በአሁኑ ወቅት ሦስት ችግሮች አሉ። እነዚህ ሦስት ችግሮችን በግልጽ መገንዘብ ያስፈልጋል። የመጀመርያው ችግር ከለውጥ ጋር የተያያዘ ነው። አገራችን ከለውጥ ጋር በተያያዘ ፈተና ውስጥ ነው … [Read more...] about “የፌዴራል መንግሥት በትግራይ የሆነ ዕርምጃ እወስዳለሁ ካለ ራሱ ያደርገዋል”
ዶ/ር ዐቢይ፤ ህወሃት ሚሊዮኖች ለምርጫ ከሚያባክን የውሃ ጉድጓድ ለምን አይቆፍርም?
የትግራይ ህዝብ የማይሳተፍበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ አይኖርም❗️ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በትግርኛ ቋንቋ በነበራቸው ቆይታ፥ “በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የፌዴራል መንግስት ይሁን እኔ በበኩሌ የትግራይ ህዝብ የማይሳተፍበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ይኖራል ብለን በፍፁም አናስብም” ብለዋል። “የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ምስረታ ጀምሮ እስከሁን ድረስ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ቆይቷል አሁንም እየተጫወተ ነው” ሲሉም ገልፀዋል። “ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ አሁን ባለንበት ወቅት ሶስት ችግሮች አሉ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ ከእነዚህም የመጀመሪያው ከለውጥ ጋር የተያያዘ ችግር ነው፣ ሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲና ህወሐት ካላቸው ግንኙነት ጋር የተያያዘ ነው፣ ሶስተኛው ደግሞ ልዩነት ማስፋት የሚፈልጉ አካላት የሚፈጥሩት … [Read more...] about ዶ/ር ዐቢይ፤ ህወሃት ሚሊዮኖች ለምርጫ ከሚያባክን የውሃ ጉድጓድ ለምን አይቆፍርም?
የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን ማጣራት እና ስለ ታሳሪዎች አያያዝ
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን አሳዛኝ ግድያ ተከትሎ በተለይ በኦሮሚያ ክልል፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና ሌሎችም አንዳንድ ቦታዎች የተከሰተውን መጠነ ሰፊ የጸጥታ ችግር ፣ የሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት በሚመለከት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከመነሻው ጀምሮ በቅርብ መከታተሉን የቀጠለ ሲሆን፤ እስከ አሁን የተካሄዱትና በመካሄድ ላይ ያሉት ዋና ዋና ሥራዎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡- 1. የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን በፈጣን ምርመራ ማጣራትና መዘገብ ምንም እንኳን የደረሰውን አደጋ በተመለከተ በተወሰነ መጠን በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃንና ድርጅቶች እንዲሁም የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የተዘገበ ቢሆንም፤ ኢሰመኮ በሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የምርመራ ስልት ላይ የተመሰረተና በበቂ ማስረጃዎች የተደገፈ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አይነት በተገቢው መጠን የሚያጣራና የሚመዘግብ … [Read more...] about የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን ማጣራት እና ስለ ታሳሪዎች አያያዝ
ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚና አብዲ አለማየሁ ፍርድ ቤት ቀረቡ
አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በከሰአት በኋላ በነበረው ችሎትም የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በቡራዩና አዲስ አበባ በተፈጠረ አመጽና ሁከት በደረሰ የሰውና የንብረት ጉዳት የተጠረጠሩ 8 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በጠዋቱ ችሎት በቀዳሚነት የቀረቡት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ላይ መርማሪ ፖሊስ የሰራውን የምርመራ ስራ ይፋ አድርጓል። በዚህም የምስክር ቃል መቀበሉን፣ ወንጀሉ የተፈጸመበት ስፍራን በቴክኒክ ማስረጃ ማረጋገጡን፣ ግብረ አበሮቻቸውን በቁጠጥር ስር አውሎ ምርመራ እየሰራ መሆኑን፣ አርቲስት ሃጫሉ የተገደለበትን ሽጉጥ ከተጠርጣሪዎች ቤት ከተቀበረበት ጓሮ ማውጣቱን እና በምርመራ ማረጋገጡን አስረድቷል፡፡ ከዚህ ባለፈም በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ስልካቸውን … [Read more...] about ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚና አብዲ አለማየሁ ፍርድ ቤት ቀረቡ
አብይን የምደግፈው ለራሴ ስል ነው!
አብይን የምደግፈው አዎ ለራሴ ስል ነው! ከፀፀት ለመዳን፤ ከህሊና ወቀሳ ለመትረፍ ስል! ዶክተር አምባቸው መኮንን ከተገደለ በኋላ የተሰማኝን ስሜት እኔ ነኝ የማውቀው። የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆኖ በሀላፊነት በቆየባቸው ሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ በውጥረት ተከቦ በርካታ በጎ ስራዎችን አከናውኗል። ጥሩ ስራ ሲሰራ አንድም በጎ ቃል ትንፍሽ አላልኩም ነበር።ኦሮሚያ ክልል ሄዶ ስለልዩ ጥቅም አወራ ሲባል ግን እሱን ለመተቸት ማንም አልቀደመኝም። አሁን የአምባቸውን ምስል ፌስቡክ ላይ ባየሁ ቁጥር ፀፀቱ ይገርፈኛል። እሱን ተችቼ የፃፍኩትን ፅሁፍ ከፌስቡክ ገፄ አጥፍቸዋለሁ። የጥፋተኝነት ስሜቱ ግን ከህሊናየ ሊጠፋ አልቻለም። ይህ ፀፀቴ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዲደገም አልፈልግም። ዶክተር አብይ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ ተዘርዝረው የማያልቁ በርካታ ለውጦችን ያመጡ ቢሆንም ከምስጋና ይልቅ … [Read more...] about አብይን የምደግፈው ለራሴ ስል ነው!