አይሻ ሰይድ በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ ነዋሪ ናት። በአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች የደረሰባትን ግፍ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች ተናግራለች። "አሸባሪው ህወሓት በአካባቢያችን ላይ ድንገተኛ ወረራ በመፈጸም ያገኘውን ሁሉ መግደል ጀመረ። የአካባቢው ነዋሪም በመደናገጥ እግሩ ወደመራው ሸሸ። እኔም የ75 ዓመት አዛውንት የሆነችውን እናቴን ይዤ ለመሸሽ ሞከርኩ። ነገር ግን አቅሟ ደከመ ብዙም መጓዝ አልቻለችም። አውሬዎቹ የአሻባሪው ታጣቂዎች ደረሱብን። እናቴን መንገድ ላይ ገደሏት፤ እኔ እንደምንም ብዬ ነብሴን አተረፍኩ" ትላለች አይሻ "ሁሌም ሀዘኔ ከውስጤ እንዳይወጣ የሚያደርገኝ ነገር ቢሮር መተኪያ የሌላት እናቴን እንኳን መቅበር አለመቻሌ ነው" የምትለው አይሻ፤ የእናቷን አስከሬን ጅብ እንደበላው ትናገራለች። "... እናቴን … [Read more...] about “እናቴን ገድለው በጅብ አስበሏት”
tplf terrorist
ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ግድያ እና መፈናቀል መኖሩን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን /ኢሰመኮ/ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ግድያ እና መፈናቀል መኖሩን ከነዋሪዎች መረጃ የደረሰው መሆኑን አስታውቋል። ኮሚሽኑ በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ኪራሙ ወረዳ የሚገኙ ሲቪል ሰዎች ለደኅንነታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆናቸው የሚያሳስብ መሆኑን ነው ብሏል። በዚሁ ወረዳ፣ ቦቃ ቀበሌ መስከረም 7 እና 8 ቀን 2014 ዓ.ም በደረሱ ሦስት ተያያዥ ጥቃቶች በአጠቃላይ 18 ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን፣ እንዲሁም መስከረም 8 ቀን 2014 ዓ.ም በውልማይ ቀበሌ በተፈጸመ ሌላ ጥቃት 11 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለኮሚሽኑ አሳውቀዋል። በኪራሙ ወረዳ ባለው አሳሳቢ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ከተለያዩ የወረዳው አካባቢዎች ተፈናቅለው በኖሌ ቀበሌ፣ በሀሮ እና ኪራሙ ከተሞች ተጠልለው የሚገኙ ከ40 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ለወራት አስቸኳይ … [Read more...] about ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ግድያ እና መፈናቀል መኖሩን አስታወቀ
በሱዳን ለትህነግ ሊሰጥ የነበረ 260 ገጀራ እና 1 ሺህ 149 ሕገ ወጥ መታወቂያ ተያዘ
ከሱዳን ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ለነበረው የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን የተዘጋጀ ገጀራ እና የሐሰት መታወቂያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሽንፋ ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ከሱዳን በቲሀ በኩል ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ለነበረው እና በጀግናው የፀጥታ ኀይል ለተደመሰሰው የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን ሊሰጥ የነበረ 260 ገጀራ እና 1 ሺህ 149 ሕገ ወጥ መታወቂያ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሽንፋ ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ጉባይ ቀበሌ በቀድሞው የሰሜን ጎንደር ዞን ጉባይ ጀጀቢት ቀበሌ በሚል ስያሜ ተዘጋጅቶ ከሱዳን ሊገቡ ለነበሩ የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን አባላት ሊሰጥ የነበረ 1 ሺህ 149 ሕገ ወጥ መታወቂያ የቅማንት ጽንፈኛ ቡድን መሪ በሆነው አቶ ሻንቆ አየልኝ ቤት መገኘቱን የሽንፋ ንዑስ ወረዳ ፖሊስ … [Read more...] about በሱዳን ለትህነግ ሊሰጥ የነበረ 260 ገጀራ እና 1 ሺህ 149 ሕገ ወጥ መታወቂያ ተያዘ
ጠላትን በዱላ በመምታት ጀብዱ የፈጸሙ አባትና ልጅ
አርሶ አደር ፈንታዬ አበረ ተወልደው ያደጉት በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ቀበሌ 32 ነው። እንደአካባቢያቸው ማኅበረሰብ ሁሉ እሳቸውም በደግነታቸው፣ በታታሪነታቸውና በጀግንነታቸው ይታወቃሉ። በግብርና ሥራም ቢሆን የተዋጣላቸው አርሶ አደር ናቸው። በእንግድነት ለመጣባቸውም አልጋቸውን ይለቃሉ፣ የሚበላ የሚጠጣ ቤት ያፈራውን ሁሉ ያቀርባሉ። ዛሬ ግን ወደ አርሶ አደሩ ቀዬ ብቅ ያለው ተናፋቂ እንግዳ አይደለም፣ ወይም አረምን በማረም አርሶ አደሩን ለመርዳት የመጣ አይደለም፣ ቀማኛ፣ ወራሪ፣ አሸባሪ እና ዘራፊ ቡድን እንጂ። አርሶ አደሩ ለዚህ ወራሪ እንደ እንግዳ ተቀባይነታቸው አላስተናገዱትም ከልጃቸው ጋር በመሆን የጀግንነት ክንዳቸውን አቀመሱት እንጅ። እሳቸውም ሆነ ልጃቸው የመተኮስ ልምዱ ቢኖራቸውም የጦር መሳሪያ ግን የላቸውም። የነበራቸው ጀግንነትና ልበ ሙሉነት ነበር። ከልጃቸው ጌጡ … [Read more...] about ጠላትን በዱላ በመምታት ጀብዱ የፈጸሙ አባትና ልጅ
ከልጅ እጅ ጠብቀው፥ ከሚያገኙት ቀንሰው ለወገን ጦር ድጋፍ የቸሩ እናት
ወ/ሮ ውዴ በለጠ ይባላሉ። ነዋሪነታቸው ጎንደር ከተማ ቀበሌ 17 ነው። ሀገሬ በችግር ውስጥ ሆና እኔ በድሎት አልኖርም በማለት ልጆቻቸው ለቀለብ ብለው ከሚሰጧቸው ጥቂት ገንዘብ እየቆጠቡ ለሰራዊት አባላት በግላቸው ስንቅ አዘጋጅተው አቅርበዋል። ወ/ሮ ውዴ የልጆቻቸውን እጅ ጠብቀው የሚኖሩ እናት ቢሆኑም ለህልውና ዘመቻ የሀገርን ክብርና የወገንን ህልውና ለማስጠበቅ ግንባር ለተሰለፉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የአማራ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ይሁንልኝ ሲሉ 3 ኩንታል በሶ አዘጋጅተው ድጋፍ አበርክተዋል። ግለሰቧ “ከዚህ በፊትም ልጆቼ በቻሉት አቅም ግንባር ለዘመቱ ወገኖቻቸው ድጋፍ አድርገዋል” ይላሉ። “አሁን ደግሞ የኔ ተራ ነው፤ ከወር ቀለቤ እየቀነስኩ በሰበሰብኳትና ልጆቼ በሰጡኝ ጥቂት ገንዘብ ይህንን አድርጌያለሁ” አሉ። እኔ በሰላም ወጥቼ እንዲገባ እነሱ ህይወታቸውን … [Read more...] about ከልጅ እጅ ጠብቀው፥ ከሚያገኙት ቀንሰው ለወገን ጦር ድጋፍ የቸሩ እናት
ከ20 ቤተሰብ የመጡ 40 ወንድማማቾችና እህትማማቾች በአንድ ላይ ዘመቱ
አሸባሪውን ህወሓት የፈጸመውን ወረራ በመቀልበስ ኢትዮጵያን ለማዳን ከ20 የተለያዩ ቤተሰቦች 40 ወንድማማቾችና እህትማማቾች በአንድ ላይ ዘምተዋል። እነዚህ የኢትዮጵያ ዘማቾች ያለፈው ረቡዕ መስከረም 12፤2014ዓም ከደሴ ከተማ ወደ ስልጠና ማዕከል ሽኝት ተደርጎላቸዋል። (ኢፕድ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከ20 ቤተሰብ የመጡ 40 ወንድማማቾችና እህትማማቾች በአንድ ላይ ዘመቱ
በስልኩ ብቻ 15 የጁንታ ታጣቂዎችን ማርኮ፤ 40ዎቹን እንዲደመሰሱ ያደረገው ጀግና
ሰፊው በቀለ ናደው ይባላል። በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ ቀበሌ 03 ነዋሪ ሲሆን፤ ውልደትና እድገቱ ምንጭ ውሃ በሚባል አካባቢ ነው። ጁንታው ከነ ጀሌዎቹ ወደ ሥፍራው በመጣ ጊዜ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ለአማራ ልዩ ኃይሉ ስንቅና ትጥቅ በማቀበል ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ብዙ ተጋድሎም ፈጽሟል። አባቱ ሻምበል በቀለ ናደው የቀድሞ ሰራዊት አባል ሲሆኑ፣ አያቱም ታሪክ እንዳላቸውና የእነርሱን ታሪክ ለመድገም ቆርጦ መነሳቱን ያስታውሳል። በዚህም ያለ ጥይትና ያለ ክላሽ በያዛት ስልክ ብቻ ጠላቱን እንደተዋጋ ይናገራል። ኦፕሬሽኑን ለሚመሩት አካላት ጠላትን እየተከታተለ መረጃ በመስጠት ትልቅ ጀብዱ ፈጽሟል። ሰፊው የሹፍርና ሙያ ያለው ሲሆን፣ ጁንታዎች በመንገድ ቢያገኙት መታወቂያውን አይተው መኪና ሊያስነዱት እንደሚችሉ በማመኑ በመታወቂያው ላይ “ሹፌር” የሚለውን … [Read more...] about በስልኩ ብቻ 15 የጁንታ ታጣቂዎችን ማርኮ፤ 40ዎቹን እንዲደመሰሱ ያደረገው ጀግና
“የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ሲተኩስ ከአንገት በላይ መምታት እንዳለበት አምኖ ነው”
በጋሸና ግንባር የሚገኙ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በጠላት ላይ የላቀ የበላይነት እያገኙ እንደሆነ አባላቱና መሪዎቹ ተናግረዋል። ሳጅን ካሳዬ ወርቁ በጋይንት ግንባር ያለው የአማራ ልዩ ኃይል ተጋድሎ አኩሪ እንደነበረ ተናግሯል። ልዩ ኃይሉ ከጋሳይ ጀምሮ እስከ ደብረ ዘቢጥ ጀብድ ፈጽሟል ብሏል። የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ልዩ ኃይሉ አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድንን በተቀናጀ መልኩ እንደደመሰሱት ገልጿል። ጠላት ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ለማስረከብ እንደተገደደም አስረድቷል። ኮንስታብል አሳልፍ ተመሰለው ልዩ ኃይሉ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት የአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድንን እንደደመሰሱት ተናግሯል። የአማራ ብሎም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድን ነፃ እስኪሆኑ ድረስ ተጋድሏቸውን እንደሚቀጥሉ ነው … [Read more...] about “የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ሲተኩስ ከአንገት በላይ መምታት እንዳለበት አምኖ ነው”
ልደቱ ትህነግን ለማዳን ጥሪ አቀረበ፤ አማራ የኅልውና ችግር አልገጠመውም
“አማራውም ሆነ አፋሩ ምንም ዓይነት የኅልውና አደጋ አላጋጠመውም፤ ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም በትህነግ የደረሰበት ችግር የለም፤ አማራውም ሆነ አፋሩ በትህነግ በጅምላ አልተጨፈጨፈም፤ ማይካድራ፣ ጭና፣ አጋምሳ፣ ጋሊኮማ፣ ወዘተ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የተፈጸመ ጭፍጨፋ ነው እንጂ በዲሲፒሊን የታነጸው ትህነግ እንዲህ ዓይነት ግፍ አይፈጽምም፣ በአጠቃላይ “ሒሳብ እናወራርድብሃለን” የተባለው የአማራው ሕዝብ በትህነግ ምንም ግፍ አልደረሰበትም፤ ወልቃይት የምዕራብ ትግራይ አካል ነው፣ ራያም የትግራይ ነው፤ ወዘተ። ስለዚህ ትህነግ ሳትሞት በሽግግር መንግሥት ምሥረታ የአፍ ለአፍ ትንፋሽ እንስጣትና እንታደጋት”።ልደቱ አያሌው ትህነግ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ሲገባ ለመታደግ ከሚረባረቡት “ቅምጥ” ቡድኖች መካከል በቀዳሚነት የሚሰለፈው ልደቱ አያሌው ነው። ከእርሱ ሌላ የቀድሞ የትህነግ … [Read more...] about ልደቱ ትህነግን ለማዳን ጥሪ አቀረበ፤ አማራ የኅልውና ችግር አልገጠመውም
ልደቱ አያሌውን ስድስት ነገሮች ሆነው ይሆናል በሉት
አቶ ልደቱ አያሌው የፖለቲካ ህይወቱን አሀዱ ብሎ የጀመረው 1983ዓ.ም. ህወሃት/ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ የከተማዋን ወጣቶች የማደራጀት ስራ ላይ ከተሰማሩ ወጣቶች አንዱ ሆኖ ነው። በዚያ ወቅት ወጣቱ ልደቱ ለወያኔ መንግስት የመወገን ጫና በነበረበት የወጣት ማህበር ምስረታ ሂደት ንቁ ተዋናይ ነበረ። በመሆኑም የማህበሩ ሊቀመንበር የመሆን ፍላጎት እንደነበረው በወቅቱ አብረውት የነበሩ የመሰከሩት ነገር ነው። ነገር ግን በ1990 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በይፋ ሲመሰረት ወጣቱን በማደራጀት ምንም ተሳትፎ ያልነበረው የዳዊት ዮሃንስ (አፈጉባዔ የነበረ) ሚስት ወንድም የሆነው ወጣት ታጠቅ ካሳ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ። ይሄኔ ነው እንግድህ የልደቱ የመጀመሪያው የፖለቲካ አቋም እጥፋት የተጀመረው። የታጠቅን በሊቀመንበርነት መመረጥ አሚን ብሎ መቀበል አልፈለገም። … [Read more...] about ልደቱ አያሌውን ስድስት ነገሮች ሆነው ይሆናል በሉት










