ጉዳዩ፦ በቂሊንጦ እሳት ሰበብ ስለታሰሩት ሰዎች የተደረገውን ምርመራ በተመለከተ እንደሚታወቀው ኢሰመኮ በቀን 20 ጥቅምት 2010፣ በደብዳቤ ቁጥር ሰመኮ/2.1/29/2010 እንደገለጸው ነሐሴ 1/2008 አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት (ቂሊንጦ) ግቢ ውስጥ የተነሳውን እሳት መንስዔ ለማጣራት በተደረገው ምርመራ አሰቃቂ የመብቶች ጥሰቶች ተፈፅመዋል። በእነ መቶ ዐለቃ ማስረሻ ሰጤ መዝገብ (38 ተከሳሾችን) በተመለከተ መንግሥት ባለበት አገር ይፈፀማሉ ተብለው የማይጠበቁ የጥፍር መንቀል፣ በሚስማር ሰውነት የመብሳት፣ ግርፋት እና የመሳሰሉት አካላዊ ጉዳት የሚያደርሱ፣ ሰብኣዊ ክብርን የሚያዋርዱ የጭካኔ ተግባራት በተያዙ ሰዎች ላይ ተፈፅሞባቸዋል። ይሄ ሁሉ የሆነው ፍርድ ቤት በአደራ እንዲጠብቃቸው ያስረከበው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ ነው። ሆኖም፣ ዋነኞቹ የምርመራው (ወይም … [Read more...] about ግልጽ ደብዳቤ፦ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)