አርሶ አደር ፈንታዬ አበረ ተወልደው ያደጉት በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ቀበሌ 32 ነው። እንደአካባቢያቸው ማኅበረሰብ ሁሉ እሳቸውም በደግነታቸው፣ በታታሪነታቸውና በጀግንነታቸው ይታወቃሉ። በግብርና ሥራም ቢሆን የተዋጣላቸው አርሶ አደር ናቸው። በእንግድነት ለመጣባቸውም አልጋቸውን ይለቃሉ፣ የሚበላ የሚጠጣ ቤት ያፈራውን ሁሉ ያቀርባሉ። ዛሬ ግን ወደ አርሶ አደሩ ቀዬ ብቅ ያለው ተናፋቂ እንግዳ አይደለም፣ ወይም አረምን በማረም አርሶ አደሩን ለመርዳት የመጣ አይደለም፣ ቀማኛ፣ ወራሪ፣ አሸባሪ እና ዘራፊ ቡድን እንጂ። አርሶ አደሩ ለዚህ ወራሪ እንደ እንግዳ ተቀባይነታቸው አላስተናገዱትም ከልጃቸው ጋር በመሆን የጀግንነት ክንዳቸውን አቀመሱት እንጅ። እሳቸውም ሆነ ልጃቸው የመተኮስ ልምዱ ቢኖራቸውም የጦር መሳሪያ ግን የላቸውም። የነበራቸው ጀግንነትና ልበ ሙሉነት ነበር። ከልጃቸው ጌጡ … [Read more...] about ጠላትን በዱላ በመምታት ጀብዱ የፈጸሙ አባትና ልጅ