ለኢህአዴግ ሊቀመንበርነትና ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የህወሓት እጩ በመሆን የቀረበውና በህወሓት ሙሉ ድምጽ የተሰጠው ሽፈራው ሽጉጤ ከደቡብ ሕዝብ ሊቀመንበርነቱ ለቀቀ። ሽፈራው ሽጉጤ ራሱ እንደተናገረው ከሆነ “ከሥልጣኔ ለቅቄአለሁ” ቢልም አፍቃሪ ህወሓት የሆኑና እርሱ በኢህአዴግ ሊቀመንበርነት እንዲመረጥ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ሲሠሩ የነበሩ ሰውየው “ተገፍቶ ነው” የወጣው በማለት አቅጣጫ የማስቀየር ሙከራ ሲያደርጉ ተስተውለዋል። በቅርቡ በሃዋሳ በደረሰው ግጭት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የሚመለከታቸው አመራሮች በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ ቢሆኑም ባይሆኑም ይህ ዓይነቱ ግጭት እየተፈጠረ በኃላፊነት መቀጠል እንደሌለባቸውና ከሥልጣናቸው በፈቃዳቸው መልቀቅ እንዳለባቸው ሃሳብ ሰጥተው ነበር። ይህንንም ተከትሎ ከወላይታ ዞን አራት አመራሮች በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን … [Read more...] about በደቡብ የህወሓት ኅልውና እያከተመ ነው
Middle Column
የአዲስ ኢትዮጵያ ብስራት!
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የተመሠረተባቸው አዕማዶች ሁለት ናቸው። እነዚህም ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ! እና ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም! የሚሉት ናቸው። እነዚህን ግዙፍ መርሆዎች ተግባራዊ ለማድረግ የሚጠቀምባቸው ስልቶች ደግሞ ዓመጽ፣ ጥላቻ፣ ክፋት፣ ምቀኝነት፣ ዘረኝነት፣ ወገንተኝነት፣ ወዘተ ሳይሆን ሰብዓዊ ዘርን ከልዩነት በጸዳ ጽኑ ፍቅር በማክበር፣ በመውደድና ለሌላው ሰው ከልብ በመነጨ ቅንነት በሚያስብ አመለካከት ላይ በመመሥረት ነው። የእነዚህ ተግባራት መዳረሻ ደግሞ በአገራችን ላይ ፍቅር፣ ሰላም፣ ኅብረት፣ ዕርቅና ፍትሕ ማስፈን ነው። ከላይ የጠቀስናቸው መርሆዎች በተባለው አካሄድ ተፈጻሚ ይሆኑ ዘንድ የጋራ ንቅናቄያችን ለበርካታ ዓመታት ያለመታከት ሲሠራ ቆይቷል። ለዚህም ነው ኢትዮጵያውያን በቡድንም ይሁን … [Read more...] about የአዲስ ኢትዮጵያ ብስራት!
የጌታቸው አሰፋ ሌጋሲ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች!
የህወሓት ነባር ታጋይ የሆነው ጌታቸው አሰፋ የመረጃና ደህንነት ዳይሬክተር ሆኖ የተሾመው 1993 ዓ.ም ላይ ነበር። ክንፈ ገ/መድህንን የተካው ጌታቸው አሰፋ ከቀደመው የመረጃና የደኅንነት ሰው ፍጹም የተለየ ባህሪ እንዳለው የመረጃ ምንጮቻችን ይጠቁማሉ። ከሸራተን ሆቴል ውጭ እምብዛም የማይዝናናው ጥንቁቁ የመረጃ ሰው ሲበዛ ተጠራጣሪና ደመቀዝቃዛ እንደሆነ ይነገርለታል። በኤምባሲዎች ራት ግብዣ ላይ እንኳን ለመገኘት ከኤምባሲ ኤምባሲ፣ ከአምባሳደርም አምባሳደር የሚያማርጠው የደህንነቱ ቁንጮ፣ በህይወት እያለ ምሽት ላይ ከቦሌ ወሎ ሰፈር ግሮሰሪዎች በአንዱ ከማይታጣው ክንፈ ገ/መድህን አኳያ የተለየ ባህርይ ብቻ ሳይሆን የረቀቀ የአፈና መዋቅር በአገር ውስጥም ሆነ በቀጠናው ላይ መዘርጋት የሚችል ሰው መሆኑ ከቀደመው የመረጃ ሰው እንደሚለየው ይነገርለታል። ሰውየው ራሱን እንደመንፈስ … [Read more...] about የጌታቸው አሰፋ ሌጋሲ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች!
“የጥላቻና የምቀኝነት አስተሳሰብ መገረዝ አለበት፤ አደገኛ በሽታ ነው”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የአስፈጻሚውን አካል የሥራ ክንውን በተመለከተ ያቀረቡት ሪፖርትና ለጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ። ሙሉውን ለመመልከት የቪዲዮው ምስል ላይ ይጫኑ። … [Read more...] about “የጥላቻና የምቀኝነት አስተሳሰብ መገረዝ አለበት፤ አደገኛ በሽታ ነው”
“ጄኔራል” አደም መሐመድ፤ ከሬዲዮ ኦፕሬተርነት እስከ መረጃና ደኅንነት ዳይሬክተርነት
ወሎ-አምባሰል የተወለደው አደም መሐመድ በ1975 ዓ.ም ኢህዴንን የተቀላቀለ ነባር ታጋይ ነው። በትጥቅ ትግሉ ወቅት በዋናነት የአዲሱ ለገሰ ሬዲዮ ኦፕሬተር ሆኖ ሰርቷል። አንዳንዶች በሰውየው ላይ ሲቀልዱ “የአዲሱ ለገሰ ሻሂ አፍይ” ይሉት ነበር። አደም መሐመድ ለአዲሱ ለገሰ ለአምልኮ የቀረበ ፍቅር ያለው በመሆኑ በሬዲዮ የሚተላለፉ መልዕክቶችን በጽሁፍ ከመገልበጥና መረጃዎችን ከማድረስ ባሻገር ለሰውየው ማሸርገድ ይወድ ነበር የሚሉት የእርሱ ዘመን ጓዶች፣ አድርባይነቱን ያለ ልዩነት ይስማሙበታል። ከኢህአዴግ ምስረታ በኋላ በነበሩ አውደ ውጊያዎች በ“ዘመቻ ዋለልኝ” እና “ኢህአዴግ ፋና” በተሰኙ ዘመቻዎች ላይ ተሳትፏል። በትጥቅ ትግሉ ወቅት እንደ ድርጅት “መስመር ማጥራት” በሚል በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱ ሴሚናሮች፣ ኮንፍረንሶች እና በሁለቱም ድርጅታዊ ጉባዔዎች (1976 እና 1981ዓ.ም) … [Read more...] about “ጄኔራል” አደም መሐመድ፤ ከሬዲዮ ኦፕሬተርነት እስከ መረጃና ደኅንነት ዳይሬክተርነት
“አባ ነቅንቅ” – ኦባንግ ሜቶ ሊሞሸር ነው!!
ከኢትዮጵያውያን ጋር ሁሉ የማይሰበር የጽናት ጋብቻ እንደመሠረተ ያምናል። ከሞት ወዲያ ሳይሆን ለሞት ወዲህ ስላለው ታላቅ አገራዊ ክብር ይጨነቃል። በሁሉም ስፍራ፣ በየትኛውም አጋጣሚ ለሚፈልጉት ሁሉ “አለሁ” የሚል ኢትዮጵያዊ ነው። ዘረኝነትን፥ ዘውገኝነትን፥ ጎሠኝነትን፥ አጥብቆ ይዋጋል፤ ይጸየፋል። ከዘር ቆጠራና ከቂም የጸዳች ኢትዮጵያን ማየት ህልሙ ነው። የመጨረሻው ግብ!! ፍቅርን የሚሰብክ በመሆኑ አፍቃሪዎቹ ከልብ ይወዱታል። ለእሱ ያላቸው ፍቅርም ሲሞቅ በማንኪያ የሚሉት ዓይነት አይደለም። በቅርቡ የመኪና አደጋ ባጋጠመው ወቅት ለአደጋ የዳረገችውን ሴት ከሞት ተርፎ ሲያጽናናት የተመለከተች እናት እንባ እያነቃት አድናቆቷን ችራዋለች። ኦባንግ ሜቶ!! ዛሬ በሁለት አዳዲስ የህይወት ጅማሮ ላይ ነው። “ማኅተቤ” የሚላት አገሩ ተስፋ ሰጪ በሆነ ሽግግር ላይ ናት ብሎ ያምናል። በዚህም … [Read more...] about “አባ ነቅንቅ” – ኦባንግ ሜቶ ሊሞሸር ነው!!
ህወሓት እነ ዓቢይን ለመገምገም ኢህወዴግን ስብሰባ ጠራች
ላለፉት ሁለት ቀናት መቀሌ መሽጋ ስትንጫጫ የቆየችው ህወሓት እነ ዓቢይ አህመድን ለመገምገም ስብሰባ ይጠራልኝ ብላ መግለጫ አውጥታለች። የዛሬውን አያድርገውና ዱሮ በፈለገችው ጊዜና ሰዓት ስብሰባ ስትጠራ የኖረችው ህወሓት ለዚህ መብቃቷ ክስረቷን ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። ህወሓት ይህንን ስትጠይቅ የሚከተሉትን መሠረታዊ ውሳኔዎች በመቀበል ነው፤ ኢትዮጵያ ህዝብታት ወያናይ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህወዴግ) ወይም በአማርኛ ኢህአዴግ፤ "የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ለመሸጥ ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎች" እንደምትቀበል፤ "የኢትዮ ኤርትራን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔና የአልጄርሱ ውይይት በሚመለከት የተላለፈውም ውሳኔ ከአገሪቱ የሰላም ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ በመሆኑ ተገቢና ወቅታዊ ነው" ካለች በኋላ ነው ህወሓት እነ ዓቢይ ይገምገሙልኝ ስትልት ስብሰባ … [Read more...] about ህወሓት እነ ዓቢይን ለመገምገም ኢህወዴግን ስብሰባ ጠራች
ሁለቱ ጄኔራሎች
ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ እና ሜ/ጀኔራል አለምሸት ደግፌ ከመከላከያ ሰራዊቱ በተለያየ ጊዜ “የመከላከያ ሪፎርም አደናቃፊ” በሚል ማዕረጋቸው ተገፍፎ የተሰናበቱ ወታደራዊ መኮንኖች ናቸው። ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ የቀድሞ የጦር ሠራዊት አባል የነበረና በ1978 ዓ.ም ኢህዴንን የተቀላቀለ ጀግና አዋጊ እንደሆነ የኢህዴን ጓዶቹ ሳይቀር ይመሰክሩለታል። ድህረ-ደርግ በሲቪል አስተዳዳሪነት የላስታ ወረዳ አስተዳደር ቀጥሎም የሰሜን ወሎ ዞን አመራር ሆኖ ሰርቷል። የባድመ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ ወደ ወታደራዊ አመራርነት የተመለሰው አሳምነው ጽጌ፣ የቀደመ የትግል ልምዱን መነሻ በማድረግ ያለአንዳች ማዕረግ በጦርነቱ ውስጥ በባድመ የጦር ግንባር 22ኛ ክፍለ ጦርን እየመራ ተዋግቷል። ባድመ ላይ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ ከነበሩት ጥቂት አመራሮች አንዱ አሳምነው ጽጌ ይገኝበት … [Read more...] about ሁለቱ ጄኔራሎች
የሱሪ ረዥሙ “ፕሮፌሰር ጄኔራል” ሳሞራ የኑስ ስንብትና የሳዕረ መኮንን መንገሥ
ግንቦት 30/2010 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ማምሻውን ከወደ ታችኛው ቤተ-መንግሥት የተሰማው ዜና የኢትዮጵያዊያንና የዓለምአቀፉን ሚዲያ ትኩረት የሳበ ነበር። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (መከላከያ በአዲሱ አወቃቀር በኮሚቴ (ወታደራዊ ካዉንስል) ሊመራ ነው) በሚል ርዕስ ከሦስት ሳምንት በፊት መከላከያ ሠራዊት እንደተቋም በአመራሩ ላይ ብወዛ ሊያደርግ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ወደአንባቢያን አድርሶ ነበር። በወቅቱ ወደ አንባቢያን ባደረስነው መረጃ ላይ፡- መከላከያ ሠራዊት ሪፎርም ሊያደርግ እንደሆነ፣ በአገሪቱ “ሕገ-መንግሥት” ላይ የሌለ ቢሆንም ሦስት ምክትል ኤታማዦሮች መሾማቸውን፣ የ“ኤታማዦር ኮሚቴ” በሚል የቡድን አመራር መከላከያ ሠራዊት ሊመራ እንደሆነ፣ የመከላከያ ሠራዊት “ወታደራዊ ካውንስል” እንደ አዲስ ሊደራጅ እንደሆነ፣ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ … [Read more...] about የሱሪ ረዥሙ “ፕሮፌሰር ጄኔራል” ሳሞራ የኑስ ስንብትና የሳዕረ መኮንን መንገሥ
ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”
እንደ ህወሓት ያለ አስገራሚ የፖለቲካ ቡድን ያለ አይመስለኝም። በጣም ገራሚ ነው። ከአመታት በፊት ያስቀመጥከው ቦታ ቁጭ ብሎ ይጠብቅሃል። በራሱ ምንም ዓይነት ለውጥ እንዲመጣ አይሻም። ከራሱ ባለፈ በሌሎች ዘንድ ምንም ዓይነት ለውጥና መሻሻል እንዲኖር አይፈቅድም። ከሁለት አመት በፊት ህወሓት “ቆሞ-ቀር” እንደሆነ የሚገልፅ ፅሁፍ አውጥቼ ነበር። ዛሬም ቢሆን ከነበረበት ቦታ ንቅንቅ አላለም። ህወሓት ፀረ-ለውጥ ድርጅት ከመሆኑ በተጨማሪ ሥር የሰደደ የአመራር ችግር አለበት። በመሆኑም ህወሓት ራሱን ለለውጥ ማንቀሳቀስ ሆነ መምራት አይችልም። በተለይ የመለስ ዜናዊ ህልፈትን ተከትሎ ህወሓት “በቁሙ መሞት” ጀምሯል። ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት አባይ ወልዱ ናቸው። ሰውዬው እንደ መለስ ዜናዊ ሸርና አሻጥር መጎንጎን አልቻሉበትም። በመሆኑም የመለስ ዜናዊ የነፍስ አባት … [Read more...] about ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”










