ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ እና ሜ/ጀኔራል አለምሸት ደግፌ ከመከላከያ ሰራዊቱ በተለያየ ጊዜ “የመከላከያ ሪፎርም አደናቃፊ” በሚል ማዕረጋቸው ተገፍፎ የተሰናበቱ ወታደራዊ መኮንኖች ናቸው። ብ/ጀኔራል አሳምነው ጽጌ የቀድሞ የጦር ሠራዊት አባል የነበረና በ1978 ዓ.ም ኢህዴንን የተቀላቀለ ጀግና አዋጊ እንደሆነ የኢህዴን ጓዶቹ ሳይቀር ይመሰክሩለታል። ድህረ-ደርግ በሲቪል አስተዳዳሪነት የላስታ ወረዳ አስተዳደር ቀጥሎም የሰሜን ወሎ ዞን አመራር ሆኖ ሰርቷል። የባድመ ጦርነት መቀስቀስን ተከትሎ ወደ ወታደራዊ አመራርነት የተመለሰው አሳምነው ጽጌ፣ የቀደመ የትግል ልምዱን መነሻ በማድረግ ያለአንዳች ማዕረግ በጦርነቱ ውስጥ በባድመ የጦር ግንባር 22ኛ ክፍለ ጦርን እየመራ ተዋግቷል። ባድመ ላይ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ ከነበሩት ጥቂት አመራሮች አንዱ አሳምነው ጽጌ ይገኝበት … [Read more...] about ሁለቱ ጄኔራሎች