• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሓት እነ ዓቢይን ለመገምገም ኢህወዴግን ስብሰባ ጠራች

June 13, 2018 12:26 pm by Editor 2 Comments

ላለፉት ሁለት ቀናት መቀሌ መሽጋ ስትንጫጫ የቆየችው ህወሓት እነ ዓቢይ አህመድን ለመገምገም ስብሰባ ይጠራልኝ ብላ መግለጫ አውጥታለች። የዛሬውን አያድርገውና ዱሮ በፈለገችው ጊዜና ሰዓት ስብሰባ ስትጠራ የኖረችው ህወሓት ለዚህ መብቃቷ ክስረቷን ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

ህወሓት ይህንን ስትጠይቅ የሚከተሉትን መሠረታዊ ውሳኔዎች በመቀበል ነው፤

ኢትዮጵያ ህዝብታት ወያናይ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህወዴግ) ወይም በአማርኛ ኢህአዴግ፤

  • “የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ለመሸጥ ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎች” እንደምትቀበል፤
  • “የኢትዮ ኤርትራን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔና የአልጄርሱ ውይይት በሚመለከት የተላለፈውም ውሳኔ ከአገሪቱ የሰላም ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ በመሆኑ ተገቢና ወቅታዊ ነው”

ካለች በኋላ ነው ህወሓት እነ ዓቢይ ይገምገሙልኝ ስትልት ስብሰባ እንዲጠራላት በአክብሮት የጠየቀችው። ከዚህም ሌላ ህወሓት በኢህወዴግም ውስጥ ይሁን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረኝ ሥልጣኔ ተሸርሽሯል፤ ከፍቶኛል ብላለች። የሪፖርተሩ ብሩክ አብዱ የዘገበው እንዲህ ይነበባል፤

የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ረቡዕ ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ለመሠረታዊ የኢኮኖሚ ችግር ጊዜያዊ መፍትሔ ላይ ከማተኮር ይልቅ ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጥ ይገባ ነበር ሲል ወቀሰ።

ሕወሓት በመግለጫው፣ “የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ማየት የነበረበት መሠረታዊ ጉዳይ አሁን ገጥሞን ላለው የኢኮኖሚ ችግር ዘላቂ መፍትሔ ማፈላለግ መሆን ሲገባዉ፣ ችግሩ ባስከተላቸው ውጤቶችና ለጊዚያዊ መፍትሔዎች ቅድሚያ መስጠቱ አንድ ጉድለት እንደሆነና፣ ዘላቂው መፍትሔ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመራችን በግልጽ የለያቸውን የልማት አቅሞቻችን፣ ማለትም መላው ሕዝባችን፣ መንግሥትና የግል ባለሀብቱን በማደራጀት ርብርብ እንዲያደርጉ ትኩረት መስጠት አልቻለም፤” ብሏል።

ድርጅቱ ለሁለት ቀናት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባም የኢሕአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ትላልቅ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ለመሸጥ ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎች እንደሚቀበል፣ ነገር ግን አፈጻጸሙ ላይ ውይይትና ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አስታውቋል።

የኢትዮ ኤርትራን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔና የአልጄርሱ ውይይት በሚመለከት የተላለፈውም ውሳኔ ከአገሪቱ የሰላም ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ በመሆኑ ተገቢና ወቅታዊ ነው ብሏል። “አፈጻጸሙን በሚመለከት ግን አገራችን ከሌሎች ጎረቤት አገሮች ጋር ካሏት የአዋሳኝ ድንበር ጉዳዮች አንፃር ጭምር እጅግ ከፍ ያለ ትርጉም ያለዉ በመሆኑ፣ በከፍተኛ ጥንቃቄ ሊታይ እንደሚገባዉ አፅንኦት ሰጥቶ ተወያይቷል፤” ሲል አስታውቋል።

ይሁንና ማዕከላዊ ኮሚቴው፣ “በኢትዮ ኤርትራ ዘላቂ ሰላም ጉዳይም ሆነ ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጋር በተያያዘ የተወሰኑ ውሳኔዎች ወደ ኢሕአዴግ ምክር ቤት ሳይቀርቡ፣ አጋር ድርጅቶች ሳይሳተፉበትና የሚመልከታቸው አካላት በዝርዝር ሳይወያዩበት እንደመጨረሻ ውሳኔ ተወስዶ ለሕዝብ ይፋ መደረጉ አንድ ጉድለት እንደሆነ ማዕከላዊ ኮሚቴዉ ደምድሟ፤” ሲል በመግለጫው አትቷል።

ድርጅቱ አክሎም፣ “በአሁኑ ወቅት በኢሕአዴግ ደረጃ እየተደረጉ ያሉ የኢሕአዴግን ሕገ ደንብና ተቋማዊ አሠራር ያልተከተሉ የአመራር ምደባዎች እንዲታረሙ የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ይጠይቃል፤” በማለት፣ “ወቅታዊ ሁኔታውን በፍጥነት ለማየትና ለመገምገም የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ምክር ቤት አስቸኳይ ሰብሰባ እንዲጠራ የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ይጠይቃል፤” ብሏል።

****

የህወሓት ውሳኔ ይህ ቢሆንም ባድመን ለኤርትራ ተላልፋ እንድሠጥ ያደረገውን እና ሕዝብን የዋሸውን ስዩም መስፍንን፤ ስምምነቱን በፈቃዱ ሄዶ የፈረመውን መለስ ዜናዊን እንዲሁም ይህንን በማስፈጸም እነዚህንና መሰል የአገር ክህደት ከፍተኛ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችን ከነድርጅቱ ለፍርድ ማቅረብ የትግራይ ሕዝብ ቀዳሚ ኃላፊነት እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: eprdf, Full Width Top, Middle Column, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Ezira says

    June 14, 2018 12:05 am at 12:05 am

    ውነት ነው! በመጀመሪያ አገር የሸጠውና የለወጠው የትግሬ ወያኔ ለፍርድ ይቅረብ። አገር ሻጭና ለዋጭ ምን የሞራል ብቃት አለው ዶ/ር አብይን ሰበሰባ እንዲጥራ የሚጠይቀው …? መጀመሪያ ትግሬ ወያኔ የሸጥውን ባድመን ከእነ ወለዱ ክፈል።

    Reply
  2. በለው ! says

    June 14, 2018 10:48 am at 10:48 am

    ኢትዮጵያ እንደ አንድ ሉዓላዊ አገር ድንበር የላትም!
    እንደ ሕገ መንግሥቱ ባድመም ጾረናም የትግራይ ክልል ጉዳይ ብቻ ነው፡፡
    (ውብሸት ሙላት)
    የፌደራሉ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ ሁለት ላይ እንደተገለጸው የአገሪቱ የግዛት ወሰን (ድንበር) የክልሎቹ ወሰን ነው፡፡ ሕገ-መንግሥቱ ሲረቀቅ ይሄም አንቀጽ በዚህ መልኩ መደንገግ እንደሌለበት፣ኢትዮጵያም እንደሌሎች ሉዓላዊ አገራት ሁሉ፣ የራሷ የሆነ ዳር ድንበርና አዋሳኞች ሊኖሯት እንደሚገባ ክርክር እንደነበር ከተለያዩ ሰነዶች መረዳት ይቻላል፡፡
    የኢትዮጵያ ድንበር ሳይቀር የሚወሰነው በክልሎች ሕግጋተ መንግሥት ነው እንደማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ሁሉም ክልሎች አዋሳኞቻቸውን ብሎም ድንበራቸውን የደነገጉ ቢሆንም የደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ሕገ መንግሥት ግን የክልሉ ወሰን የዞኖቹ እና የወረዳዎቹ ነው በማለት ደንግጓል፡፡
    ይሁን እንጂ እንኳንስ ወረዳ እና ዞን ይቅርና ከልሎችም ከሌሎች ሉዓላዊ አገራት ጋር ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መዋዋል ስለማይችሉ ይህ ዓይነቱ በክልል፣በዞን እና በወረዳ የኢትዮጵያን የግዛት ወሰን በተለይም ከሌሎች ሉዓላዊ አገራት ጋር የምትዋሰንባቸውን ድንበሮች መለየት ለአፈጻጸምም አስቸጋሪ ነው፡፡
    ክልሎቹ ከሉዓላዊ አገራት እና ከሌሎች ክልሎች ጋር ይዋሰናሉ፡፡ ከሌሎች አገራት ጋር በሚዋሰኑበት ጊዜ ጉዳዩ ዓለማ አቀፍ ሲሆን፣ ከሌላ ክልል ጋር በሚዋሰኑበት ድንበር ምክንያት የሚነሱት ጉዳዮች ደግሞ የፌደራል ይሆናሉ፡፡ ከዚህ በተቃራኒው፣ ድንበርን በተመለከተ ጥቅልል አድርጎ የክልል ማድረግ ተጠየቃዊ አይደለም፡፡
    ኢትዮጵያ እንደ ፌደሬሽን ግዛቷ (territory) የክልሎቹ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን፣ የግዛት ወሰኗ ደግሞ በጥቅሉ የክልሎቹ ሳይሆን ክልሎቹ ከሌሎች ሉዓላዊ አገራት ጋር ያላቸው ድንበር (border or boundary) ነው፡፡ ስለሆነም፣ ክልሎቹ ከሌሎች አገራት ጋር የሚዋሰኑበትን የድንበር አከላለል እና ተያያዥ ጉዳዮች በፌደራሉ መንግሥት ሥልጣን ሥር እስካልሆኑ ድረስ ሁኔታዎቹን የበለጠ ውስብስብ ያደርጋቸዋል፡፡
    የፌደራሉ ሕገ መንግሥቱ ላይም ይሁን የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ላይ እንደተገለጸው ከሆነ የባድመም ይሁን በጾረናና ሌሎች የትግራይ ክልል ከኤርትራ ጋር የሚዋሰኑባቸው አካባቢዎችን የሚመለከተው ክልሉንና ኤርትራን ብቻ ነው እንደማለት ነው፡፡ ወለፈንድ (absurd) የድንበር ሕግ!!!!
    እንደዚህ ዓይነቶቹ የሕገመንግሥት አንቀጾች ካልተሻሻሉ ወደፊት በርካታ ውስብስ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሊያስከትል የሚችላቸውን መዘዞች ለጊዜው እንተወው፡፡ ቢያንስ ግን ለአገራዊ ግንባታ ደንቀራ ነው፡፡ መሻሻል ይገባዋል፡፡

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule