የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ በአዲስ አበባ እየተደረገ ነው ያለውን የመሬት ወረራና ህገ-ወጥ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላ በተመለከተ ሊሰጠው የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ለሁለተኛ ጊዜ ተከለከለ፡፡ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ እንዳሉት ጋዜጣዊ መግለጫው የተከለከለው መግለጫ የሚሰጥበት ቦታ የሆነው ራስ ሆቴል ከሰላም ሚኒስቴር የተፃፈ ደብዳቤ ስጡኝ በማለቱ፤ የሰላም ሚኒስትር ደግሞ ደብዳቤ ለመፃፍ ባለመፍቀዱ ነው ሲሉ ነግረውናል፡፡ ፓርቲው ለሁለተኛ ጊዜ መግለጫ እንዳይሰጥ ስለተከለከለ፣ መግለጫውን በፅ/ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚሰጥ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ነግረውናል፡፡ ሸገር ይህንኑ ጉዳይ ለማጣራት ወደ ሰላም ሚኒስትር ቢሮ ደውዬ ተነገረኝ እንዳለው፣ የሚኒስትሯ ፅህፈት ቤት ፈቃዱን የሚሰጠው አካል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚኒስትሮች … [Read more...] about ፈራሚዋ ሚኒስትር የሉም በሚል ኢዜማ መግለጫ እንዳይሰጥ በድጋሚ ተከለከለ
Right Column
108 ሕገወጥ ማኅተሞች ተያዙ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጎተራ አካባቢ በሚገኝ አንድ የጋራ መኖሪያ ቤት ውስጥ 108 ህገወጥ ማህተሞች መያዙን አስታወቀ። በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወርዳ 4 ጎተራ ኮንዶሚኒየም ውስጥ 108 ማህተሞች እና የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ለተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባራት ሲጠቀሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሰር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል። በከተማችን አዲስ አበባ በተለያዩ ጊዚያት ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባር ሲፈፅሙ በፖሊስ ቁጥጥር ውለው በህግ አግባብ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸውን ግለሰቦች የወንጀል ድርጊት መረጃ በመስጠት ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክቶችን ማስተላለፋችን ይታወሳል። አሁንም በአንዳንድ አካባቢ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሲፈጸሙ ይስተዋላል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወርዳ 4 ጎተራ ኮንዶሚኒየም ውስጥ ሀምሌ 1ቀን 2012ዓ.ም. ሁለት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር … [Read more...] about 108 ሕገወጥ ማኅተሞች ተያዙ
የጃዋር፣ የበቀለና የእስክንድር የፍርድ ቤት ውሎ
“የመናገር መብት ከሌለን ለምን እንመጣለን?” ተጠርጣሪ በቀለ ገርባ “በጠበቆቻችሁ አማካይነት በቂ ጊዜ ተሰጥቷችሁ ተናግራችኋል” ፍርድ ቤት በተጠረጠሩበት የእርስ በርስ ግጭት በማነሳሳትና በሌሎች የወንጀል ድርጊቶች ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች፣ የጊዜ ቀጠሮ ምርመራ መዝገባቸው ተዘግቶ በአንድ የምርመራ መዝገብ ተጠቃለው በተከፈተባቸው የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ ላይ ያቀረቡት ተቃውሞ ውድቅ ተደረገ። ተጠርጣሪዎቹ ያቀረቡትን ተቃውሞ ውድቅ ያደረገው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ልደታ ማስቻያ አንደኛ ወንጀል ችሎት ሲሆን፣ ከፌዴራል ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ ምርመራ ቡድን የምርመራ መዝገቡን ተረክቦ፣ ቀዳሚ ምርመራ በተመሳሳይ ፍርድ ቤት መክፈቱንና ምስክሮችን ለማሰማት ትዕዛዝ … [Read more...] about የጃዋር፣ የበቀለና የእስክንድር የፍርድ ቤት ውሎ
ከትግራይ ክልል የከዱ 30 የፀረ ሽምቅ እና የልዩ ኃይል አባላት አማራ ክልል ገቡ
ከትግራይ ክልል የከዱ የፀረ ሽምቅ እና የልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል መግባታቸው ታውቋል። ከሰሞኑ ወደ ክልሉ የገቡ የፀረ ሽምቅ እና የልዩ ኃይል አባላት 30 ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ 20ዎቹ 17 ክላሽ ሸንኮቭ እና ሦስት ሽጉጦችን እንደያዙ በደባርቅ በኩል መግባታቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ለምለሙ ለአብመድ አረጋግጠዋል። ተጨማሪ የጸረ ሽምቅና የልዩ ኃይል አባላትም እየከዱ እየገቡ መሆኑ ተመላክቷል። አስሩ ደግሞ በጠገዴ በኩል ነው ወደ አማራ ክልል የገቡት። ከእነዚህ መካከል ዘጠኙ ከነሙሉ ትጥቃቸው፣ አንዱ ያለ ጦር መሳሪያ እንደገቡ ነው የተገለጸው። የጸጥታ አባላቱ ሕዝቡ ሀሳቡን በነጻነት ማራመድ አለመቻሉን እና በክልሉ እየተካሄደ ያለውን የጦርነት ቅስቀሳ መቃወማቸውን ለመክዳታቸው በምክንያትነት አቅርበዋል ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው። “ምርጫ … [Read more...] about ከትግራይ ክልል የከዱ 30 የፀረ ሽምቅ እና የልዩ ኃይል አባላት አማራ ክልል ገቡ
ከሚገድለኝ ሰይጣን ይልቅ የሚሰድበኝ ባለስልጣን ይሻለኛል! ሽመልስ የተናገረው በወቅቱ ትክክል ነው‼️
አቶ ሽመልስ አብዲሳ “በትላንትናው እለት የተናገረው ነው” ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከሰባት ወር በፊት የብልፅግና ፓርቲ ገና በምስረታ ሂደት ላይ እያለ የተናገረው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በወቅቱ የድርጅቱን አባላትና አመራሮች በኦቦ ለማ መገርሳ፣ ወ/ሮ ጠይባ እና በዶ/ር ሚልኬሳ ከሚመራው ብሔርተኛ ቡድን ለመነጠልና በድርጅቱ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው የኃይል ሹኩቻ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በሚደረግ ጥረት የተናገረው እንደሆነ ተረጋግጧል። አቶ ሽመልስ የተናገረበት ግዜና ቦታ ምን ያህል የተለያየ ቢሆንም አዲስ አበባን አስመልክቶ የተናገረው ነገር መቼም፥ እንዴትም ትክክል አይሆንም። ይሁን እንጂ በወቅቱ ድርጅቱ ውስጥ የጃዋር መሃመድ ጉዳይ አስፈፃሚ የነበሩት ከላይ የተጠቀሱት የኦዴፓ አመራሮች ከኮዬ_ፈቼ ኮኖደሚኒዬም ጋር በተያያዘ ሲያራምዱት የነበረው አቋምና ጉዳዩ በብሔርተኞቹ ዘንድ … [Read more...] about ከሚገድለኝ ሰይጣን ይልቅ የሚሰድበኝ ባለስልጣን ይሻለኛል! ሽመልስ የተናገረው በወቅቱ ትክክል ነው‼️
የሀጫሉ አስከሬን ወደ አምቦ እንዳይሄድ አድርገዋል በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ ቀን ተፈቀደ
የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የወንጀል ችሎት የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ አስከሬን ወደ አምቦ እንዳይሄድ ከእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ጋር በጋራ ተንቀሳቅሰዋል በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ ከጠየቀው 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ለመጨረሻ ጊዜ በማለት 12 ቀናት ፈቀደ። ተጠርጣሪዎች አዲሱ ቶሎሳ፣ ደስታ ሽኩር ፣ጥላሁን ለታ፣ አበራ ሁንዴ፣ ሙስተዋሪድ አደም፣ አረፋት አቡበከር፣ አማን ቃሎ፣ ሱልጣን በድያ፣ ውቢ ቡርቃ፣ ሀቢቢ ሳፈው፣ ጉቱ ሙሊሳ፣ ሲሳይ በቀለ፣ ሮባ አዳነ እና ጉልማ ከፈና ናቸው። እንደ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ ሁሉም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት የሟች አስከሬን ወደ አምቦ ሳይደርስ አዲስ አበባ ተመልሶ ወደ ኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ይዘው ሲገቡ የተገኙ ናቸው። ከእነ አቶ ጃዋር ጋር በመሆን አስከሬኑ ወደ … [Read more...] about የሀጫሉ አስከሬን ወደ አምቦ እንዳይሄድ አድርገዋል በተባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ ቀን ተፈቀደ
“ውጭ ቁጭ ብለው መንገድ ዝጉ” የሚሉ “ከህወሃት በምንም አይሻሉም” የአርሲ ወጣት
* “በተማረ ጭንቅላት ብቻ ታግለን ማሸነፍ አለብን እንጂ መንገድ በመዝጋት (የለብንም)” የአርሲ ወጣት ሃገርን ለማፈራረስ የሚሰሩ የጸረ-ሰላም ኃይሎችን ሴራ በማክሸፍ የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ የአርሲ ዞን ወጣቶች ገለጹ። ከአርሲ ዞን 26 ወረዳዎችና የአሰላ ከተማን ጨምሮ ከሶስት የከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ወጣቶች የተሳተፉበት የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ ዛሬ በአሰላ ከተማ ተካሒዷል። ከኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች መካከል ወጣት ከማል ንጉሴ “ሀገሪቷን ለማስቀጠል እኛ ወጣቶች በአንድነት ሆነን የጥፋት ሃይሎችን እንታገላለን ” ብሏል። “ወጣቶች በስሜት ተነሳስተን ጥፋት በማስከተል ሳይሆን በተማረ ጭንቅላት ብቻ ታግለን ማሸነፍ አለብን እንጂ መንገድ በመዝጋት፣ የዜጎችን ህይወት በማጥፋትና ንብረት በማውደም አንድም ለውጥ አይመጣም” ብሏል። ለመንግስት … [Read more...] about “ውጭ ቁጭ ብለው መንገድ ዝጉ” የሚሉ “ከህወሃት በምንም አይሻሉም” የአርሲ ወጣት
“የፌዴራል መንግሥት በትግራይ የሆነ ዕርምጃ እወስዳለሁ ካለ ራሱ ያደርገዋል”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት በፋና ቴሌቪዥን በትግርኛ ቋንቋ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። ከተነሱት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ለውጡና የትግራይ ክልል ሁኔታ፣ የድምፂ ወያነና የትግራይ ቴሌቪዥን መዘጋት፣ ምርጫን በተመለከተ፣ የኤርትራ ጉዳይና የፌዴራል መንግሥት ትግራይን ሊያጠቃ ነው ስለመባሉ ይገኙበታል። በማብራሪያቸው የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች እንደሚከተለው ተጠናቅረዋል። ለውጡና የትግራይ ክልል ሁኔታ “የትግራይ ሕዝብ የማይሳተፍበት ፖለቲካ በኢትዮጵያ ይኖራል የሚል እምነት የለኝም። ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ በአሁኑ ወቅት ሦስት ችግሮች አሉ። እነዚህ ሦስት ችግሮችን በግልጽ መገንዘብ ያስፈልጋል። የመጀመርያው ችግር ከለውጥ ጋር የተያያዘ ነው። አገራችን ከለውጥ ጋር በተያያዘ ፈተና ውስጥ ነው … [Read more...] about “የፌዴራል መንግሥት በትግራይ የሆነ ዕርምጃ እወስዳለሁ ካለ ራሱ ያደርገዋል”
በሁለት ሪዞርቶች ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ውድመት
ሐይሌ ሪዞርት በዝዋይ እና በሻሸመኔ ከተሞች ለወደመበት ኢንቨስትመንት መንግስት ድጋፍ ካደረገ ወደ ስራው እንደሚመለስ አስታውቋል። የድርጅቱ ባለቤት አትሌት ሃይሌገብረስላሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አንዳለው የድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞትን ተከትሎ በዝዋይ እና ሻሸመኔ ከተሞች በስራ ላይ የነበሩት ሆቴሎች ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል። አትሌት ሃይሌ ከዚህ በፊት በነዚህ ከተሞች የነበረውን ኢንቨስትመንት ማቋረጡን ያስታወቀ ቢሆንም አሁን ግን መንግስት ለወደመበት ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንት ድጋፍ ካደረገለት ወደ ስራ እንደሚመለስ ገልጿል። የዝዋዩን ሪዞርት ወደ ስራ ለመመለስ ከአንድ ዓመት በላይ የጥገና ጊዜ የሚፈጅ ሲሆን የሻሸመኔው ሀይሌ ሪዞርት ቅርንጫፍ ግን የግድ እንደ አዲስ መገንባት ስለሚጠይቅ ወደ ስራ ለመመለስ በትንሹ ሶስት አመታትን እንሚፈጅ አትሌት ሀይሌ … [Read more...] about በሁለት ሪዞርቶች ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ውድመት
በሀገራችን የመጀመሪያዎቹ ፈቃድ ያገኙት ድሮኖች!
በኢትዮጵያዊው ወጣት ናኦል ዳባ የተሰሩ ሁለት ድሮንና (ፀረ-አረም መድሃኒት መርጫና ከርቀት ሆኖ ለማኅበረሰቡ መልክዕት ማድረስ የሚያስችሉ) አንድ የኮሮና ቫይረስ ሙቀት መለኪያ የፈጠራ ውጤቶች ይፋ ሆነዋል። ለጸረ-አረም መርጫ የሚያገለግለው ድሮን 10 ሊትር የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን በአንድ ጊዜ 65 ሄክታር መሬት መርጨት ያስችላል። በቀጣይ በሞዴሉ እስከ 500 ሊትር የመያዝ አቅም የሚኖረው ይሆናል። የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው እስካሁን በድሮውን ዘርፍ ፈቃድ የሚሰጥበት አሰራር እንዳልነበረ አውስተዋል። አሁን አሰራሩን የሚፈቅድ ህግ በመርቀቁ የፈጠራ ባለቤቱ ወጣት ናኦልና ሌሎች መስፈርቱን አሟልተው ሲገኙ ፈቃድ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል። (ምንጭ፤ ኢፕድ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በሀገራችን የመጀመሪያዎቹ ፈቃድ ያገኙት ድሮኖች!