በሰበታ ከተማ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ በቤት ውስጥ የተከማቸ ከ3 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ እና የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ተያዙ። የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቀነኒሳ ዳዲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት የተያዘው ገንዘብ 3 ሚሊየን 751 ሺህ 830 የኢትዮጵያ ብር፣ 2 ሺህ 950 የአሜሪካ ዶላር እና የዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት፣ የፓኪስታንና የኦማን ገንዘቦች ናቸው። በከተማው የ3ኛ ክፍለ ከተማ የፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ታደሰ ሁሪሳ ገንዘቡ በግለሰብ ቤት ውስጥ አልጋ ስር ተከማችቶ የተያዘው በህብረተሰቡ ጥቆማና በፀጥታ መዋቅር ክትትል ነው ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ ወደ ፊትም ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አቶ ቀነኒሳ ዳዲ … [Read more...] about ከ3.7 ሚሊዮን ብር በላይ በሰበታ ተያዘ
Right Column
የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮችን በእስር እንዲቆዩ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጠ
የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ የቀድሞ የወላይታ ዞን አመራሮች የነበሩ ግለሰቦችን ጨምሮ 20 ተጠርጣሪዎች በወላይታ ሶዶ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ፤ ለተጠርጣሪዎች ተፈቅዶ በነበረው ዋስትና ላይ ፖሊስ የመልስ መልስ ይዞ እንዲቀርብ ለመጪው ሳምንት ማክሰኞ መስከረም 19 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃ ተመስገን ዋጃና ለ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ተናግረዋል። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የተጠርጣሪዎችን አቆያየት በተመለከተ በትላንትናው ዕለት ከሰዓት ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም በጠዋት ችሎት ቀርበው የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች አልተገኙም በሚል ብይኑን ለዛሬ ማሳደሩን ጠበቃው ገልጸዋል። እስከ ምሽት አንድ ሰዓት ድረስ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ሲጠብቁ የቆዩ ሰባት ተጠርጣሪዎችም በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሐዋሳ ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ … [Read more...] about የወላይታ ዞን የቀድሞ አመራሮችን በእስር እንዲቆዩ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጠ
ራሳችንን ከሐሰት መረጃ ፈብራኪዎች እንከላከል
በኢትዮጵያና በውጪ በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ የሃሰት መረጃ በማሰራጨትና የበርካታ ሰዎችን ትኩረት በመሳብ በርካታ ገቢ የሚያስገኝ ተከታታይ መሰብሰብ ያልተለመደ ተግባር አይደለም። በተለይ ግን ብዙ ተከታይ አለን በሚሉ ዘንድ ይህ በተደጋጋሚ ሲከሰት መስተዋሉ የሞራልም የስብዕናንም መዝቀጥ በጉልህ የሚያሳይ ነው። ህወሓት በአገራችን ሕዝብ ላይ ካደረሰው የግብረገብነት ዝቅጠት ወደ ተሻለ መንገድ ለመሄድ ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት በሃሰት መረጃ የሰዎችን ቀልብ በመሳብ እና ክሊክ በማግኘት ይህም ደግሞ የሚያስገኘውን ተራ ጥቅም ብቻ በማየት ለዚህ ዓይነት ርካሽ ሥራ መሠማራት ውርደት ነው። በኢትዮጵያ የሚወጡትን የሐሰት መረጃዎች እያነፈነፈ የሚያጋልጠው Ethiopia Check “ዘሐበሻ” እና “Ethiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ” የተባሉ “በሚዲያ” ስም የሚጠሩ ማክሰኞ … [Read more...] about ራሳችንን ከሐሰት መረጃ ፈብራኪዎች እንከላከል
የእምቦጭ አረምን በ30 ቀናት ማጥፋት የሚችል መድኃኒት ተገኘ
የእምቦጭ አረምን በ30 ቀናት ውስጥ ሊያጠፋ የሚችል መድኃኒት ማግኘቱን የእጸ ህይወት ጥናትና ምርምር ማዕከል ባለቤት ገልጸዋል። መድኃኒቱን ለማግኘት ለ7 አመታት የፈጀ ምርምር ማድረጋቸውን የማዕከሉ ባለቤት መርጌታ በላይ አዳሙ ተናግረዋል። የእምቦጩ ማጥፊያው በዱቄት መልክ የተዘጋጀ ሲሆን ለአምስት ዓመት ሳይበላሽ መቆየት እንደሚችል ተገልጿል። የጸረ-እምቦጭ መድኃኒቱ በበጋ ወራት ወይም ዝናባም ባልሆነ ወቅት ቢረጭ ውጤታማ ይሆናል። መድሃኒቱ በአእምሮአዊ ንብረት እውቅና የተሰጠውና በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የታየ መሆኑን የፈጠራው ባለቤት ገልጸዋል። አልዓይን አማርኛ … [Read more...] about የእምቦጭ አረምን በ30 ቀናት ማጥፋት የሚችል መድኃኒት ተገኘ
አማርኛ ቋንቋ በቻይና መሰጠት ተጀመረ፤ የመጀመሪያው የሕግ መዝገበቃላት በአማርኛ ሊዘጋጅ ነው
ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ልታስተምር እንደሆነ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ። ትምህርቱ መሰጠት የጀመረበትን ይፋዊ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት የተመለከተ መረጃን በማኅበራዊ ገጹ ያጋራው ኤምባሲው ትምህርቱ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) መሰጠት እንደጀመረ ገልጿል። በሥነ ስርዓቱ የኤምባሲው የሚኒስትር አማካሪ አቶ ሳሙዔል ፍጹም ብርሃን እና የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጂያን ውንጂን ንግግር አድርገዋል። (አል አይን) ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሕግ መዝገበ ቃላት ለማዘጋጀት የሚያስችል ሥምምነት መፈረሙን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። ሥምምነቱን የተፈራረሙት የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ጀስቲስ ፎር ኦል የተባለው ግብረ ሠናይ ድርጅት ናቸው።መዝገበ … [Read more...] about አማርኛ ቋንቋ በቻይና መሰጠት ተጀመረ፤ የመጀመሪያው የሕግ መዝገበቃላት በአማርኛ ሊዘጋጅ ነው
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል በኢትዮጵያ ተከፈተ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልን ዛሬ (እሁድ) መርቀው ከፍተዋል። ማዕከሉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጪነት በ2012 ዓ.ም የተቋቋመ ነው። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማሽኖች ሰው ሰራሽ የሆነ የማሰብ ክህሎትን በተለያዩ የስራ መስኮች የሚያሰማራ ቴክኖሎጂ ነው። ሙሉ ለሙሉ ራሳቸውን ችለው ለሰው ልጅ አድካሚ የሆኑ ተግባራትን በፍጥነት ማከናወን ያስችላል በማት ኢዜአ ዘግቧል። በኢትዮጵያም የተቋቋመው ማዕከል ለግብርና፣ የትምህርት፣ ጤና እንዲሁም ለህብረተሰብ ጥበቃና ደህንነት አገልግሎቶች ይውላል። ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆነውም አሁን ላይ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተደገፉ የጡት ካንሰርና የጭንቅላት ዕጢ መለየት በሚያስችሉ መተግበሪያዎች እየሰራ ይገኛል። ጎልጉል የድገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል በኢትዮጵያ ተከፈተ
እነ ጃዋር ይከሰሳሉ – ዐቃቤ ሕግ
በእነ ጃዋር ሲራጅ መሃመድ ላይ ተከፍቷል ከተባለው የክስ መዝገብ ጋር በተያያዘ በመጪው ሳምንት መግለጫ እንደሚሰጥ ዐቃቤሕግ አስታወቀ። ጃዋር ሲራጅ መሀመድን ጨምሮ በአጠቃላይ በ24 ሰዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 260215 በ10 ተደራራቢ ክሶች ማስከፈቱን ያስታወቀው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩን በማስመልከት በመጪው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት መግለጫ እንደሚሰጥ ተገለፀ። “ክስ መመሥረት ባለበት ጊዜ ውስጥ ባለመመሥረቱ ተከሳሾቹ ከሰኞ ጀምሮ ከእሥር ሊለቀቁ ነው የሚል ወሬ በሕዝብ ዘንድ ተሰራጭቷል” መግለጫው ዐቃቤ ሕግ ተቋሙ እየሰራ ያለውን ሥራ ማኅበረሰቡ እንዲያውቀው ለማድረግ የሚሰጥ ነው ብለዋል። የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ መከፈቱን በተመለከተ ዛሬ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አጭር ጥቅል መረጃን ሰበር በሚል ርዕስ ሰጥቷል። “ፍርድ ቤት ራሱ ክሱ በዝርዝር … [Read more...] about እነ ጃዋር ይከሰሳሉ – ዐቃቤ ሕግ
በ3 ቀናት በአዲስ አበባ ሕገወጥ 100 ሺህ ዶላርና 6.6 ሚሊዮን ብር ተያዘ
ኢትዮጵያ አዲስ የብር ኖቶችን ማስተዋወቋን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝዉዉር እየተስተዋለ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የብር ኖት ለዉጥ መደረጉን ተከትሎ ባደረገዉ የኦፕሬሽን እና የድንገተኛ ፍተሻ ስራ በርካታ ቁጥር ያለዉ ገንዘብ በቁጥጥር ስር አዉሏል፡፡ በጥቁር ገበያ ሲንቀሳቀስ የነበረ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም በየኬላዎች በተደረገዉ ድንገተኛ ፍተሻ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 1.6 ሚሊዮን ብርን ጨምሮ 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በድምሩ 10.6 ሚሊዮን የኢትጵያ ብር በላይ በቁጥጥር ስር ማዋሉን በኮሚሽኑ የሙስና፣ ገቢዎች እና ልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክተር ኮማንደር ግርማ ተሰማ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽኑ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝዉዉሩን … [Read more...] about በ3 ቀናት በአዲስ አበባ ሕገወጥ 100 ሺህ ዶላርና 6.6 ሚሊዮን ብር ተያዘ
በገንዘብ ዝውውር የተከሰሰ በ10 ዓመት ጽኑ እሥራት ይቀጣል
በሕገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ ያዘዋወረ፣ በዝውውሩ የተሳተፈና ለአዘዋዋሪዎች ሽፋን የሰጠ 10 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቀው የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታወቀ። ባለፉት ሁለት ዓመታት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በሕግ አስከባሪ አካላት ቁጥጥር ስር እየዋለ መሆኑ በአገሪቱ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚዘዋወር ገንዘብ የመኖሩ አንድ ማሳያ ነው። በመሆኑም በዚሁ የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተግባር ላይ ተሳታፊ የሆነ ማንኛውም አካል በወንጀል ሕግ ከመጠየቅ እንደማይድንም ጠቅላይ አቃቤ ግህ ጠቁሟል። በኢትዮጵያ በ1996 ዓም በወጣው የወንጀል ሕግ መሰረት በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ ተሳትፎ የተገኝ ማንኛውም አካል እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በገንዘብ ዝውውር የተከሰሰ በ10 ዓመት ጽኑ እሥራት ይቀጣል
ብር የመለወጡ ቀጥተኛ ጥቅም
ብዙ ሰዎች በተደጋገሚ ብሩ በመለወጡ በቀጥታ ኢኮኖሚው ላይ የሚመጣውን ጥቅም ንገረን ብለው ጠይቀውኛል! ብር በመለወጡ የሚገኙት የአጭር ግዜ እና የረጅም ግዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች የሚከተሉት ናቸው! የአጭር ግዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች፡- በሀገራችን ከ113ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ከፋይናንስ ገበያው ቁጥጥር ውጪ አለ! ስለዚህ የገንዘብ ለውጡ ይህንን ገንዘብ ወደ ብሄራዊ ባንክ የመለወጥ እድል ይፈጥራል! ለምሳሌ፡- ምንጩ ያልታወቀ በመሆኑ ወደ ባንክ ሳይመጣ ከሚበላሸው፤ ከሀገር ውጪ በጎረቤት ሀገር በመሸሹ ከማይመለሰው፤ የመቀየሪያ ወቅቱ ከሚያልፍበት፤ በጎርፍ፤ በቃጠሎ፤ ወዘተ ከወደመው ውጪ 100 ቢሊዮን ብር እንኳን ወደ ህጋዊ የባንክ ስርዓት ቢመጣ ከፍተኛ ገንዘብ ከገበያ የመሰብሰብ እድል ስለሚፈጠር የዋጋ ንረት በሚታይ መልኩ የመቀነስ አቅም ይኖረዋል! ምንጩ … [Read more...] about ብር የመለወጡ ቀጥተኛ ጥቅም