• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በጋምቤላ ክልል ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ይዘው ለማምለጥ በሞከሩ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

November 29, 2020 11:58 pm by Editor Leave a Comment

በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ከጸጥታ አካላት ለማምለጥ ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ኮማንደር ኡማን ኡጋላ ለኢዜአ እንዳሉት እርምጃው የተወሰደው ግለሰቦቹ ትናንት ምሽት አራት ስዓት ላይ ከኑዌር ዞን ወደ ኢታንግ ልዩ ወረዳ ጦር መሳሪያዎችን በሸክም ለማስገባት ሲሞከሩ ነው።

እነሱን ለመያዝ በተደረገው የተኩስ ልውውጥም ሁለት ጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች መሞታቸውንና አንዱ ደግሞ ቆስሎ መያዙን ተናግረዋል።

በግለሰቦቹ እጅ የነበሩት 19 ታጣፊና ዘጠኝ ባለሰደፍ በድምሩ 28 የክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።

ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች በእጃቸው ይዘዋቸው የነበሩትን ሌሎች መሳሪያዎች እየተታኩሱ ይዘው ማምለጣቸውን ጠቁመው “እነሱን ለመያዝ ፖሊስ አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ ነው” ብለዋል።

ቆስሎ በቁጥጥር ስር በዋለው ተጠርጣሪ ላይ በተደረገው ማጣራት ባመለጡት ግለሰቦች እጅ 48 የሚሆኑ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች እንደነበሩ ማረጋገጥ መቻሉንም ጠቁመዋል።

በወረዳው የጦር መሳሪያዎችን ይቀበላሉ ተብሎ የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና አስፈላጊው የማጣራት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።

በተለይም ክልሉ ከደቡብ ሱዳን ጋር ሰፊ የድንበር ወሰን ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ የጦር መሳሪያ በክልሉ በኩል አድርጎ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ይገባል ተብሎ እንደሚገመትም አስረድተዋል።

የጦር መሳሪያዎቹ ለሽብር ወንጀል ካልሆነ በስተቀር ለሌላ ተግባር ስለማይውሉ ዝውውሩን ለመግታት ለሚደረገው ጥረት መሳካት ህብረተሰቡ የጀመረውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል።

“የኢታንግ ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ኦኬሎ ኡቦንግ በወረዳው ህዝቡን በማሳታፍ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሩን ለማግታት እየተሰራ ነው” ብለዋል።

የተወሰደው እርምጃና የተገኘው ውጤት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማና ትብብር የተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። (ምንጭ፦ ኢዜአ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Right Column Tagged With: operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule