ታጣቂው ህወሓት ልዩ ኃይል በሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይልና በሚሊሻ አባላት እየተደመሰሰ ይገኛል።
በዚህ ታላቅ ጀብድ ሰራዊቱ የህወሓት ስግብግብ ኃይል ለጦርነት እየተጠቀመባቸው የነበሩ ከ230 በላይ ክላሽንኮቭ፣ ከ1 ሺህ በላይ የእጅ ቦምብና ሌሎች ተተኳሽ መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ዕዝ የሰው ሐብት ልማትና የሚዲያ አስተባባሪ ኮሎኔል ደጀኔ ጸጋዬ ተናግረዋል።
እየተካሄደ ባለው ህግ የማስከበር ለህልውና ዘመቻ የአማራ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት በተሰጣቸው ቀጣና በጠላት ላይ ከባድ ወታደራዊ ጥቃት በመፈጸምና በመደምስስ ግዳጃቸውን በብቃት እየፈጸሙ መሆኑንም ማመላከታቸውን ፋና ዘግቧል።
በሌላ በኩል በጋምቤላ ከልል ዲማ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 5 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያና አንድ F1 የእጅ ቦንብ ከስድስት ተጠርጣሪ ጋር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።
የጦር መሳሪያው ሰሞኑን ከደቡብ ሱዳን ድንበር ወደ ዲማ ወረዳ በማስገባት ሊሸጥ ሲል ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።
ከጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት (ህዳር 7/2013 ዓ.ም) የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ፈጥኖ ዋና ሳጂን ጋዲሳ ቶሎሳ እንዳሉት በወረዳው በተለያዩ ጊዜያት ህገወጥ የጦር መሳሪያ እንደሚያዝ አስታውሰው በዚህ ድርጊት የሚሳተፉ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ገልፀዋል።
ሰሞኑን በቁጥጥር ስር የዋለው የጦር መሳሪያ ከደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ ወደ ዲማ ሊገባ ሲል በህብረተሰብ ጥቆማ መያዙን አስታውቀዋል።
የክልሉንና የሃገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ አካላት አላማቸውን ለማሳካት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሊያካሂዱ ስለሚችሉ ሁሉም አካባቢውን ነቅቶ መጠበቅ እንደሚኖርበት ማመልታቸውን የፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤቱ አስታውቋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply