በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ 25 የህወሓት ተልዕኮ ተቀብለው የጥፋት ሴራቸውን በንፁሃን ላይ ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የጥፋት ኃይሎቹ በነዋሪዎች እና በፀጥታ ኃይሉ የጋራ ጥረት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወልዲያ ከተማ የህዝብ ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ትዕዛዙ ጫኔ አስታውቀዋል።
ኢንስፔክተሩ ግለሰቦቹ በተያዙበት ወቅት የተለያዩ መታወቂያዎች መያዛቸውን ነው የተናገሩት።
እንዲሁም ከአንድ ሰው ላይ እስከ ዘጠኝ የተለያዩ የባንክ ደብተሮች በውስጣቸውም እስከ 400 ሺህ ብር ድረስ ተገኝቶባቸዋል ነው ያሉት።
ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ አስፈላጊውን ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝም ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።©ፋና
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply