ከትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) ጋር አብሮ "የጠብ መንጃ ትግሉን ማጧጧፍ" በሚል ከውሳኔ የደረሱ ክፋይ የ"አማራ ነጻ አውጪ" ኃይሎች መኖራቸው ተሰማ። ለስምምነቱ ትሕነግ ምዕራብ ትግራይ የሚለውንና አሁን "ነጻ ወጥቷል" የሚባለውን ወልቃይት ተላልፎ እንዲሰጥ ፈቃደኝነት ያለበት እንደሆነ ተመልክቷል። ራሳቸውን በተለያዩ አካባቢያዊና አደረጃጀት ከሰየሙት መካከል አሁን አንድ ለመሆን እየሠሩ እንደሆነ የሚነገርላቸው በዝናቡ የሚመራው የጎጃም ዕዝና የዘመነ ካሴ ኃይል ነው ይህን ስምምነት ለማድረግ እየሠራ እንደሆነ የተሰማው። “ጊዜው አሁን ነው፤ ይህንን ጊዜ ልንጠቀምበት ይገባል” በሚል በገሃድ ወልቃይትን ዳግም በኃይል ለመያዝ ደብረጽዮን በቅርቡ መናገሩ ይታወሳል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከሕዝብ ጋር በተለያዩ ከተሞች ውይይት ያደረገው ጌታቸው ረዳም “እኛ ሥራችንን መሥራት … [Read more...] about ከትሕነግ ጋር ለማበር ወልቃይትን መስዋዕት የሚያደርጉ የ”አማራ ነጻ አውጪዎች”
Archives for January 2024
ፋኖና ኦነግ ሸኔ “ነውጠኛ ቡድኖች” በመባላቸው ለጥገኝነት ማመልከቻ ተቀባይ እንደማይሆኑ ተሰማ
ፋኖና ኦነግ ሸኔ በማጣቀስ በውጭ አገራት የሚቀርቡ የጥገኝነት መጠየቂያ ማመልከቻዎች ተቀባይነት እንደማያገኙ ይህንኑ ጉዳይ በማስፈጸም የሚሠሩ አንድ ባለሙያ ለጎልጉል ጥቆማ ሰጡ። ድርጅቶቹ “ነውጥ ቡድኖች" ወይም “violent group s” በሚል የተፈረጁበት አግባብ መኖሩንም አክለው ገልጸዋል። ከአገራቸው በተለያዩ ምክንያቶች ተሰድደው ጥገኝነት የሚጠይቁ ወገኖች ከለላ ለማግኘት በሚያስገቡት የስደተኝነት ማመልከቻ በአሁኑ ሰዓት እንደየብሔራቸው ወይም ብሔራቸውን በመቀየር በብዛት በማስረጃነት የሚጠቀሙት የፋኖና የኦነግ ሸኔን ትግል እንደሆነ ይታወቃል። “ለምሳሌ በካናዳ ድርጅቶቹ “violent groups” ተብለዋል" የሚሉት የሕግ ባለሙያ ይህን የተረዱት በሥራቸው አማካይነት የደንበኞቻቸውን ጉዳይ ሲከታተሉ ነው። ባለሙያው ከተሞቹን ለይተው በስም ባይጠሩም መረጃውን የሰሙት … [Read more...] about ፋኖና ኦነግ ሸኔ “ነውጠኛ ቡድኖች” በመባላቸው ለጥገኝነት ማመልከቻ ተቀባይ እንደማይሆኑ ተሰማ
“ዐቢይን ግንባሩን ብለህ ዳዊት ሁን” ያሉት አቡነ ሉቃስ ክስ ተመሰረተባቸው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን እንደ ጎልያድ በማስመሰል በአንድ ምሳሌያዊ ዳዊት እንዲግደሉ የሃይማኖታዊ ግድያ ጥሪ ያስተላለፉት አቡን ሉቃስ የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው። አቡነ ሉቃስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 እና 251 ድንጋጌ ተላልፈዋል በሚል ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ክሱ የቀረበባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ሕገመንግስታዊና በሕገመንግስት ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ነው። በአቡነ ሉቃስ ላይ ሁለት ክሶችን ያቀረበው የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ ነው፡፡ ይህም ተከሳሽ አቡነ ሉቃስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258(ሀ) ስር የተደነገገውን ድንጋጌ እንዲሁም የወንጀል ህግ አንቀጽ 251 (ሐ) እና አንቀጽ 258 ስር … [Read more...] about “ዐቢይን ግንባሩን ብለህ ዳዊት ሁን” ያሉት አቡነ ሉቃስ ክስ ተመሰረተባቸው
አል ሸባብ ሦስት የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ካምፖችን ተቆጣጠረ
አልሸባብ ጋልሙዱግ በሚባል ክልል ከሶማሌ ጦር ጋር ባደረገው ውጊያ ሶስት የሶማሊያ ጦር ካምፖችን በቁጥጥሩ ስር አድርጓል። አል ሸባብ ከሶማሊያ ጦር ጋር አምስት ሰዓታት ያህል የቆየ ከባድ ጦርነት ካካሄደ በኋላ ከጥቃቱ የተረፉ የሶማሌ ብሄራዊ ጦር የ"ጎርጎር ኮማንዶ" መኮንኖችና ወታደሮች እንደተናገሩት በውጊያው ከ230 በላይ የሶማሊያ ወታደሮች መሞታቸውን እንዳረጋገጡና ስፍር ቁጥር የሌላቸው መቁሰላቸውን ገልፀዋል። የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር በቦታው ያሰፈራቸው ወታደሮቹ 4 ሻለቃ የ"ጎርጎር ኮማንዶዎችን" ሲሆን 15 የአል ሸባብ አሸባሪዎች ጋር ባደረገው ውጊያ ከፍተኛ ሞትና የአካል ጉዳት አስተናግዷል።የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር በአል ሸባብ ከበባ ውስጥ ሆኖ ምንም ዓይነት የሽፋን ኃይል ማሰማራት አልተቻለውም ተብሏል።ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ በአል ሸባብ የሽብር ቡድን ላይ … [Read more...] about አል ሸባብ ሦስት የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ካምፖችን ተቆጣጠረ
የተዘቀዘቀ መስቀል?!
“አርቲስት ቴዲ አፍሮ የጥምቀት በዓልን ወደ አደባባይ ወጥቶ ማክበሩን የሚያሳይ ፎቶ ተለቋል” ሲሉ ነው በርካቶች ባሰራጩት አስተያየት “ነገሩ ምንድን ነው?” ሲሉ ግራ በመጋባት ማብራሪያ የጠየቁ ቢበዙም፣ ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽመው የነበሩ አካላት ላይ ውግዘት መድረሱን ያስታወሱም አልታጡም። የሚያደርገውን በማወቅ፣ ጊዜና ሰዓት በማስላት በሚያከናውናቸው ተግባሮቹ ስኬት የለኩት “ቴዲ ሳያውቅ ይህን ለበሰ ለማለት ያስቸግራል” ሲሉም ተድምጠዋል። የዲዛይን ችሎታ አካታ እንዳያዘች የሚነገርላት ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ በጥንቃቄ እንደምትሞሽረው የሚያውቁ “ይህን እንደ ስህተት መቀበል ያዳግታል” ሲሉ አስቸኳይ ማብራሪያ እንደሚሹ አመልክተዋል። ፎቶውን በማጋራት ሰፋ ያለ አስተያት ከጻፉት መካከል ቶማስ ጃጃው በቴሌግራም ገጹ “እንደ ማንኛውም በብርሃነ ጥምቀቱ እንደሚያምን … [Read more...] about የተዘቀዘቀ መስቀል?!
ፑንትላንድ ለኢትዮጵያ ወደብ በነጻ እሰጣለሁ አለች
የሶማሊላንድና አሜሪካ የጦር ሰፈር ስምምነት ያደርጋሉ ከሶማሊያ ራሷን ለይታ በራስ ገዝነት የምትተዳደረዋ ፑንትላንድ “ኢትዮጵያ የባህር ዳርቻዎቼን አልምታ መጠቀም ትችላለች፤ እኛ በየትኛውም ኢትዮጵያ ወጪ ገቢ ላይ ምንም ዓይነት ቀረጥ አንጥልም” ስትል በባለስልጣኗ አማካይነት መናገሯ ጫጫታ አስነሳ። የሶማሊላንድ መሪ ወደ አረብ ኢምሬትስና አሜሪካ አቅንተው ከፍተኛ የተባለ የጦር ሰፈር ግንባታ ውል እንደሚፈራረሙ ታውቋል። ፑንትላንድ በምታሳያቸው እንቅስቃሴ ክፉኛ ያናደዳቸው የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ለፑንትላንድ መንግሥት የማስጠንቀቂያ መልዕክት ልከዋል። የሶማሌላንድንና የፑንትላንድን አካቶ ይቅርና መቀመጫቸውን ያለ ድጋፍ ማስተዳደር ያልቻሉት ሀሰን ሼክ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዛቻ ሲያሰሙ በርካቶችን እያስገረመ ነው። የፑንትላንድ ፕሬዚዳንት ቀጣይ ሳምንት በሚያከብሩት በዓለ … [Read more...] about ፑንትላንድ ለኢትዮጵያ ወደብ በነጻ እሰጣለሁ አለች
የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ ለማምከን በሶማሊያ የተዘጋጀ ስትራቴጂክ ሰነድ
ሶማሊያ በኢትዮጵያ ላይ በወታደራዊ፣ በዲፕሎማሲ እና በሌሎችም ዘመቻዎች የምትከተለውን ስትራቴጂ የተመለከተው ሰነድ ሚስጥራዊ ማስታወሻ ለ፡ ሐሰን ሼክ ሞሃሙ፣ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት A confidential Memorandum To: HE. Hassan Sheikh Mohamoud President of the Somali Federal Republic ከ፡ ሙክታር አይናሼ፣ የሶማሊያ መንግሰት የፀጥታ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝና አማካሪ፣ የሶማሊያ ዜጋ --ግልባጭ፡ -ሃምዛ ባሬ፣ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር -አብዲ ሃሺ አብዱላሂ፣ የላዕላይ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ -አደም መሀመድ ኑር ማዶቤ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፤ እና -ለሁሉም የፌዴራል አባል ክልሎች ፕሬዚዳንቶች ቀን፡ … [Read more...] about የኢትዮጵያን የወደብ ጥያቄ ለማምከን በሶማሊያ የተዘጋጀ ስትራቴጂክ ሰነድ