የሶማሊላንድና አሜሪካ የጦር ሰፈር ስምምነት ያደርጋሉ
ከሶማሊያ ራሷን ለይታ በራስ ገዝነት የምትተዳደረዋ ፑንትላንድ “ኢትዮጵያ የባህር ዳርቻዎቼን አልምታ መጠቀም ትችላለች፤ እኛ በየትኛውም ኢትዮጵያ ወጪ ገቢ ላይ ምንም ዓይነት ቀረጥ አንጥልም” ስትል በባለስልጣኗ አማካይነት መናገሯ ጫጫታ አስነሳ። የሶማሊላንድ መሪ ወደ አረብ ኢምሬትስና አሜሪካ አቅንተው ከፍተኛ የተባለ የጦር ሰፈር ግንባታ ውል እንደሚፈራረሙ ታውቋል።
ፑንትላንድ በምታሳያቸው እንቅስቃሴ ክፉኛ ያናደዳቸው የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ለፑንትላንድ መንግሥት የማስጠንቀቂያ መልዕክት ልከዋል። የሶማሌላንድንና የፑንትላንድን አካቶ ይቅርና መቀመጫቸውን ያለ ድጋፍ ማስተዳደር ያልቻሉት ሀሰን ሼክ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዛቻ ሲያሰሙ በርካቶችን እያስገረመ ነው።
የፑንትላንድ ፕሬዚዳንት ቀጣይ ሳምንት በሚያከብሩት በዓለ ሲመት ላይ እንዲገኙ ጠ/ሚ ዐቢይን መጋበዛቸው ይታወቃል።
ሀሰን ሼክ “ሉዓላዊነታቸን ተነካ” በሚል ዛቻ ማሰማት ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ ኢትዮጵያ ተመጣጣኝ መልስ ከመመልስ ተቆጥባ ብትቆይም ትዕግስቷ ምክንያት አዘል መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው። ወይም የሶማሊያን ዐቅመቢስነት የሚያሳይ ነው የሚሉም አስተያየቶች ሲሰጡ ይሰማል።
“ጉዳዩን ሊያውቁ የሚገባቸው ሁሉ አስቀድሞ እንዲያውቁት ተደርጓል” ሲሉ አቶ ሬድዋን ለተናገሩት ምላሽ ከሚሆኑ በርካታ መረጃዎች ውስጥ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት አረብ ኢምሬትስን ጎብኝተው “ስትራቴጂክ” ለተባለ ስምምነት አሜሪካ የማቅናታቸው ዜና ግንባር ቀደም ነው።
በሰበር ዜና የሶማሊላንድ መንግሥት ሚዲያዎች እንዳስታወቁት ፕሬዚዳንት ሙሳ አሜሪካ የሚሄዱት አሜሪካ በበርበራ ወደብ ለምትገነባው ወታደራዊ የጦር ሠፈር ስምምነት ለመፈጸም ነው።
አረብ ኤምሬትስ “ከኢትዮጵያ ጋር የጀመርኩትን ሥራ የሚያስቆም አንዳችም ኃይል የለም” ማለቷን ተከትሎ የወጣው ይህ ዜና፣ አሜሪካ “ለኔ ሲሆን ይቻላል፣ ለኢትዮጵያ ሲሆን አይቻልም” የሚል የሚጋጭ ፖለቲካ እንደማትከተል ማረጋገጫ እንደሆነ ተመልክቷል።
ኢትዮጵያና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ሰነዱን ከተፈራረሙ በኋላ ያነጋገርናቸው ምሁር “አሜሪካ ጉዳዩ ተቀብላዋለች፤ እየተጫወተች ያለችው የፖለቲካ ጨዋታ ነው” ማለታቸው አይዘነጋም። (ኢትዮ12)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Engida Daniel says
Hi
Engida Daniel says
My name is Engida Daniel