በህዳሴ ግድብ አካባቢ ሰርገው በመግባት ሽብር ለመፍጠር ያሰቡ ቡድኖች ላይ የተወሰደው ወታደራዊ እርምጃ የማያዳግምና ለቀጣይ ትምህርት የሰጠ እንደነበር ሌተና ጀነራል አስራት ዴኔሮ ገለፁ። መንግስት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ ያልተቀበሉ የጉምዝ ታጣቂዎችን ሽብርተኛው ህወሓት በሱዳን አሰልጥኖና አስታጥቆ በአልመሃል አቅጣጫ ጥቃት ለማድረስና የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ሙከራ አድርጎ እንደነበር የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ሀይል ኮማንድ ፖስት ዋና ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ገልፀዋል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትና በቀጣናው የተሰማሩ የክልል ልዩ ሀይሎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአሸባሪው ተላላኪዎች ላይ በወሰዱት እርምጃ ሀገር እና ህዝብን የሚያኮራ ጀብዱ መፈፀማቸውን ተናግረዋል። በሽፍቶቹ ላይ በተወሰደው የማያዳግም እርምጃ የሰራዊቱ ጀግንነትና ፅናት ጎልቶ … [Read more...] about ከትህነግ ጋር በመሆን በአባይ ግድብ ላይ ጥቃት ሊያደርሱ የነበሩ ተደመሰሱ
Archives for August 2021
ወደ ኮምቦልቻ ሊገባ የነበረ 49 ሺህ 300 የአሜሪካ ዶላር ተያዘ
በኮምቦልቻ ከተማ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኬላ ኮድ3 የሰሌዳ ቁጥር 89654 የሆነ መኪና መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ወደ ኮምቦልቻ ሊገባ ሲል በብሔራዊ ደኅንነት፣ በፓሊስ እና ኬላ በሚጠብቁ ወጣቶች ትብብር በቁጥጥር ሥር መዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ገልጿል። የጽ/ቤቱ የታክቲክና ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር አሊ ለአሚኮ እንደገለፁት ተጠርጣሪው ከምሽቱ 2:40 ሰዓት ላይ አሽከርካሪ በኬላው ላይ በነበረ ፍተሻ ከነዶላሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ወጣቶች በኬላ ፍተሻ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት ኮማንደር አሊ ወጣቶች እየሠሩ ያሉትን አካባቢን በንቃት የመከታተል ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። በኬላ ጥበቃ ላይ አሚኮ ያነጋገረው በጎ ፈቃደኛ ወጣት ሐሰን እንድሪስ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ለመቅበር በግንባር … [Read more...] about ወደ ኮምቦልቻ ሊገባ የነበረ 49 ሺህ 300 የአሜሪካ ዶላር ተያዘ
ከኢንዱስትሪ ፓርኮች የወጪ ንግድ በሐምሌ ወር 16.41 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ
በ2014 በጀት ዓመት በሐምሌ ወር የኢንደስትሪ ፓርኮች የወጪ ንግድ 23 ነጥብ 88 ሚሊዮን የአሜካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 16 ነጥብ 41 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በዚህም የእቅዱን 69 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል። የተገኘው ገቢ ከባለፋው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ7 ነጥብ 47 ሚሊዮን የአሜካን ዶላር ወይንም ወይንም የ14 ነጥብ 20 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ የተገለፀ ሲሆን ይህም ጭማሪ አዳዲስ አምራቾች ወደ ስራ በመግባታቸዉ የተገኘ መሆኑ ታውቋል፡፡ ደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ በሐምሌ ወር ወደ ወጪ ከላከው ምርት የዕቅዱን 633 በመቶኛ ገቢ በመፈፀም ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል፡፡ በመቀጠልም ድሬደዋ እና ኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደቅደምተከተላቸው … [Read more...] about ከኢንዱስትሪ ፓርኮች የወጪ ንግድ በሐምሌ ወር 16.41 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ
በባሌ ዞን የአሸባሪው ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
በባሌ ዞን ሐረና ቡሉቅ ወረዳ ሦስት የአሸባሪው ሸኔ አባላት በኅብረተሰቡ ተሳትፎ እና በፀጥታ አካላት የተቀናጀ ሥራ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና በሕዝቡ ላይ በመተኮስ ጉዳት ለማድረስ በሞከሩ ሁለቱ ላይ ደግሞ እርምጃ መወሰዱን የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። የአሸባሪው ሸኔ አባላት በተደጋጋሚ ወደ ዞኑ ለመግባት ሙከራ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዳይሬክተር ኮማንደር ጄይላን አሚን ተናግረዋል። በቁጥጥር ስር የዋሉት የሽብር ቡድኑ አባላት፣ “የኦሮሞን ሕዝብ ትክክለኛ ፍላጎት እንዳልተረዳን ያወቅነው ሕዝቡ በአንድነት ወጥቶ ቁጥጥር ስር ሲያውለን ነው” ብለዋል። “ሌሎች የተቀሩት ወጣቶችም ይህንኑ ሐቅ ሊረዱ ይገባል” ሲሉ መናገራቸውን ኦቢኤን ዘግቧል። የሐረና ቡሉቅ ወረዳ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የኦሮሞን ሕዝብ ለ27 ዓመታት ሲገድል፣ ሲያኮላሽ እና … [Read more...] about በባሌ ዞን የአሸባሪው ሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
የ360 ሤራ “ተንታኞች” መከፋፈል – “ጅብ ደም ከታየበት በጅቦች ይበላል”
ቁጭ ብዬ ናሽናል ጂኦግራፊክ ስመለከት ጅቦች አየሁ። አንድ ጎረምሳ አንበሳ ይተናኮላሉ። አንበሳው እየገላመጠ መንጋጋውን እያጓራ ያሳያቸዋል። ራሱን ለመከላከል ብዙም ያልተጨነቀው አንበሳ እየተቆጣና እየተገላመጠ ሲራመድ ጅቦቹ የልብ ልብ ተሰማቸው። ጅቦች አንበሳን ሊበሉ ቋመጡ። በመካከሉ አንዱ ጅብ ዘልቆ ሲገባ አንበሳው ተወናጭፎ መቀመጫው አካባቢ ነከሰው። ይህኔ የተነከሰው ጅብ ጩኸቱን አምባረቀ። አንበሳው በጣም ተናዶ ጉልበቱን ማሳየት ሲጀምር ጅቦች አፈገፈጉ። ይህን ጊዜ የተነከሰውን ጅብ መቀመጫ የማየት ዕድል የገጠማቸው ጅቦች አንበሳውን ትተው “ወንድማቸውን” ያሳድዱ ጀመር። አባረው ያዙት። አንበሳው በነከሰው በኩል የሚፈሰውን ደም ተከትለው በደቦ በሉት። ጅብ ሌላው ጅብ ላይ ደም ካየ አይምርም። ደም ሲደማ ሆዱ እንደሚሞላ ስለሚያውቅ ማድማት ወይም በደማው በኩል ገብቶ … [Read more...] about የ360 ሤራ “ተንታኞች” መከፋፈል – “ጅብ ደም ከታየበት በጅቦች ይበላል”
በአሸባሪው ቁንጮ ፃድቃን ገ/ትንሣይ የሚመራው የጠላት ኃይል ድባቅ ተመታ
በአሸባሪው ቁንጮ ፃድቃን ገ/ትንሣይ የሚመራው የጠላት ኃይል በሰሜን ወሎ ግንባር በተሰማራው የመከላከያ ሠራዊት መመታቱ ተገለጸ፡፡ ዓርሚ ሁለት የሚባልና በከሀዲው ሜ/ጄ/ል ዮሀንስ፣ በምክትሉ ከሀዲው ማዕሾ በየነ እና ከሀዲው ከበደ ፍቃዱ እንዲሁም በሜካናይዝድ አዛዡ ከሀዲው ኮ/ል ገ/ስላሴ የተመራው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ሀይል ድባቅ መመታቱ ተገልጿል፡፡ በግንባሩ የተሰማሩ ሁለት ክ/ጦር አዛዦ እንደተናገሩት፣ መንግስት የተናጠል የተኩሥ አቁም እርምጃውን ካነሳ በኋላ ከበላይ በተሠጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ጋሸናን ዋና ማዕከል በማድረግ ከዋድላ እስከ ላልይበላ መስመር ላይ የነበረውን የአሸባሪውን ሀይል መደምሠሳቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጠላት በጀግኖቹ የሠራዊት አባላት፣ ልዩ ሀይል እንዲሁም የሚሊሻ አባላትና የአካባቢው አርሶ አደር ከበባ ውስጥ ሆኖ ይገኛል ነው … [Read more...] about በአሸባሪው ቁንጮ ፃድቃን ገ/ትንሣይ የሚመራው የጠላት ኃይል ድባቅ ተመታ
መርካቶ አካባቢ ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ከ10 ሺህ በላይ ገጀራ ተያዘ
ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ከ10ሺ በላይ ገጀራ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የመርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታወቀ፡፡ በትላንትናው እለት ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ከማህበረሰቡ የተሰጠውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ መርካቶ ውስጥ ጣና የገበያ ማዕከል ጎን በሚገኝ አድማስ ህንፃ ውስጥ፤ አዲሱን የጦር መሳሪያ ቁጥጥር አዋጅ በሚፃረር መልኩ ተከማችቶ የተገኘው ከ10ሺ በላይ ገጀራ በቁጥጥር ስር በማዋል ጠቅላላ ምርመራ እያካሄደበት እንደሆነ የመርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኢኒስፔክተር ብርሃኑ አለሙ ተናግረዋል፡፡ የጦር መሳሪያውን ክምችት በመጠቆም ረገድ የህብረተሰቡ ትብብር ከፍተኛ ነበር ያሉት ምክትል ኢኒስፔክተር ብርሃኑ የብሄራዊ ደህንነት ባለሙያዎችና የፖሊስ አባሎቻችንም ድርሻም የጎላ እንደነበር … [Read more...] about መርካቶ አካባቢ ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ከ10 ሺህ በላይ ገጀራ ተያዘ
ኢትዮጵያ በትህነግ ላይ ለምትወስደው እርምጃ ልትደገፍ ይገባታል፤ የሩሲያ መንግሥት
የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት እና ክልሉ ወደ ሰላም ተመልሶ የተረጋጋ ሕይወት እንዲቀጥል ለማድረግ የወሰደውን እርምጃ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ እና በቀጠናው የሚገኙ ተቋማት እንዲደግፉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል። የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሪቫ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ በዛሬው ዕለት በሰጡ መግለጫ፣ ሩሲያ ወዳጅ ሀገር በሆነችው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወነ ስላለው ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለች ነው ብለዋል። ኢትዮጵያውያን የውስጥ ችግሮቻቸውን ለመፍታት በአፍሪካውያን ወንድሞቻቸው ድጋፍ የራሳቸውን ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ የሩሲያ እምነት መሆኑንም ገልጸዋል። አሸባሪው ህወሓት የኢትዮ-ጂቡቲ ኮሪደርን ለመያዝ ባደረገው ሙከራ የሰብአዊ ቀውስን ማባባሱን እና የስደተኞች እና የሀገር ውስጥ … [Read more...] about ኢትዮጵያ በትህነግ ላይ ለምትወስደው እርምጃ ልትደገፍ ይገባታል፤ የሩሲያ መንግሥት
ከወልዲያ አምልጦ የመጣው የትህነግ ኃይል እንዳይመለስ ተደረገ
በአማራ ክልል ሰርጎ የገባውን የአሸባሪውን ህወሓት ሀይል በመደምሰስ ላይ መሆኑን በሰሜን ወሎ ግንባር የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊቱ ክፍል አስታወቋል ። ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ዋድላ ወረዳ ፣ ኮን ከተማ እንዲሁም በጋሸና አካባቢ የሚገኘውን የአሸባሪው የህወሓት ቡድን በመምታት አኩሪ የጀግንነት ተግባር መፈጸሙን አዛዡ አረጋግጠዋል። ጀግኖቹ የሰራዊት አባላት በአካባቢው የሚገኝ የጠላት ፣ የሰውና የመሳሪያ ሀይል በየትኛውም አቅጣጫ እንዳይወጣ በማድረግና በመደምሰስ ከዋድላ ወረዳ እስከ ጋሸና ከተማ በመቆጣጠር ድል መቀዳጀታቸውን አመልክተዋል ። ሠራዊቱ ከወልዲያ አምልጦ የመጣውን ጠላት በመከታተል ፣ በዋድላ ወረዳና አካባቢ የመሸገውን የጠላት ሀይል እና መሳሪያ በመደምሰስ ጋሸና ከተማን መቆጣጠሩን የመከላከያ ሠራዊት አስታውቋል። (ኢብኮ-ፎቶ ማርቆሥ አለሙ) ጎልጉል … [Read more...] about ከወልዲያ አምልጦ የመጣው የትህነግ ኃይል እንዳይመለስ ተደረገ
ለትህነግና ሸኔ ገንዘብ ሲያስተላልፉና ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ሲፈጽሙ የነበሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ
ለአሸባሪዎቹ የህወሓትና ሸኔ ቡድኖች በተለያዩ ህገወጥ መንገዶች ገንዘብ ሲያሰባስቡና ሲያስተላልፉ የነበሩ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ አሻጥር በመፈጸም ህብረተሰቡን ለአመጽ ለማነሳሳት ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ በአዲስ አበባ 51 እንዲሁም በአፋር ክልል 6 በድምሩ 57 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡ ግብረሃይሉ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች ተሰማርተው ከአሸባሪዎቹ ህወህትና ሸኔ ቡድን ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት በመፍጠር በህገወጥ መንገድ ገንዘብ ሲያሰባስቡና ሲያስተላልፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ ማስረጃዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ አንድ አንድ ተጠርጣሪዎች በህግ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በመሰማራት ለሸብርተኛው … [Read more...] about ለትህነግና ሸኔ ገንዘብ ሲያስተላልፉና ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ሲፈጽሙ የነበሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ