በአዲሱ መንግሥት ምስረታ ውስጥ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ከ7 እስከ 13 ሆኖ የሚደራጅ ሲሆን አባላቱም እንደየ ሙያቸው ዘርፎችን እንዲከታተሉ የሚደረግ መሆኑን አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ለመንግሥት ምስረታው እየተደረገ ያለውን ዝግጅት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ የመንግሥት ምስረታ የሚካሄድ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ገልጸዋል። አፈ-ጉባዔው በሕገ መንግስቱ መሰረት መስከረም መጨረሻ ባለው ሰኞ የመንግስት ምስረታው ይካሄዳል ብለዋል። የሕግ አወጣጥ ሂደቱን አስመልክቶ የተካሄደውን ጥናት መነሻ በማድረግ የሕግ አወጣጡን የሚያዘምን መመርያ ተዘጋጅቷል ብለዋል። ምክር ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓቱን ማዘመን የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ተዘርግቷል ያሉት … [Read more...] about መስከረም 24 አዲስ መንግሥት ይመሠረታል፤ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ከ7 እስከ 13 ሆኖ ይደራጃል
Archives for August 2021
በአዲስ አበባ ለትህነግ የሚሠሩ 284 የሽብር ተጠርጣሪዎች ተያዙ
አዲስ አበባን የሽብር ቀጠና ለማድረግ የአሸባሪው ህወሓት ቡድንን ዓላማ ለማሳካት ተንቀሳቅሰዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 284 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። 199 ሽጉጥ ከ2 ሺህ 453 ጥይት ጋር፣ 32 ክላሽንኮቭ ከ5 ሺህ ከሚልቅ ጥይት ጋር እንዲሁም 4 የጦር ሜዳ መነፅር ከተጠርጣሪዎቹ እጅ፣ ከስራ ቦታቸውና ከመኖሪያ ቤታቸው በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ ለኢቲቪ ተናግረዋል። ተጠርጣሪዎቹ ለአሸባሪው ህወሓት አገር የማፍረስ ተልዕኮ የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ እንዲያገለግል ያከማቹት ከአንድ ኪሎ ተኩል በላይ የወርቅ እንዲሁም 37 ሺህ 294 ነጥብ 8 ግራም የብር ጌጣጌጥም መያዙን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠርጣሪዎቹ ለሽብር ተግባር የሚጠቀሙባቸው የአዲስ አበባ … [Read more...] about በአዲስ አበባ ለትህነግ የሚሠሩ 284 የሽብር ተጠርጣሪዎች ተያዙ
በርካታ ዓይነት እና መጠን ያለው የብረት ክምችት ተያዘ
በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 7 አስተዳደር በርካታ ዓይነት እና መጠን ያለው የብረት ክምችት በኢኮኖሚ አሻጥር ቁጥጥር ግብረ-ኃይል መያዙን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ። የኢኮኖሚ አሻጥርን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተዋቀረው ግብረ-ኃይል ለግንባታ አገልግሎት ሊውሉ የሚገባቸው ፌሮ እና ብረታ ብረቶችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ነው የተገለጸው። ለጊዜው በገንዘብ ለመተመን ያልተቻለ ለረዥም ግዜ ሕገ-ወጥ በሆነ መልኩ የተከማቹ ፌሮ እና ብረታብረቶች በወቅቱ በገበያ ላይ ውለው ቢሆን ኖሮ አሁን ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ሚና ይኖራቸው ነበር ተብሏል። እንደነዚህ አይነት ተግባር ላይ የተሰማሩ አሻጥረኞች ላይ የሚደረገው ክትትል እና ቁጥጥር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የአቃቂ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ሙሉጌታ ገልጸዋል። በተመሳሳይ በክፍለ ከተማው ወረዳ 2 … [Read more...] about በርካታ ዓይነት እና መጠን ያለው የብረት ክምችት ተያዘ
የአሜሪካ ተራድኦ ደርጅት (USAID) መጋዘኖች በአሸባሪው ትህነግ መዘረፋቸው ተገለጸ
አሸባሪው ትህነግ የአሜሪካ ተራድኦ ደርጅት መጋዘኖችን እንደዘረፈ በኢትዮጵያ የድርጅቱ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ተናገሩ። የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ከኢቲቪው ሰለሞን ዳኜ ጋር በነበራቸው ቆይታ ትህነግ ሁኔታውን ያለአግባብ እየተጠቀመበት እንደሆነ እናምናለን ብለዋል። ከተረጂዎች ላይ እርዳታን በሃይል እየነጠቀ እንደሆነ ይሰማናል ያሉት ዳይሬከተሩ እርግጠኛ ሆነን መናገር የምንችለው ግን የአሸባሪው ትህነግ ቡድን አባላት ሰርገው በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ ያሉትን የእርዳታ መጋዘኖቻችንን ዘርፈዋል፤ ይህ የምናውቀው ሀቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል። አሁን በግልጽ የምናውቀው ነገር የትህነግ ወታደሮች በገቡባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሁሉ የእርዳታ መጋዘኖችን ዘርፈዋል፣ መኪኖችን ሰርቀዋል በየመንደሮቹ ብዙ ውድመትን … [Read more...] about የአሜሪካ ተራድኦ ደርጅት (USAID) መጋዘኖች በአሸባሪው ትህነግ መዘረፋቸው ተገለጸ
በትህነግ ሽብር ምክንያት ግማሸ ሚሊዮን ተፈናቅለዋል
4 ሚሊዮን ዜጎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ናቸው የህወሓት የሽብር ቡድን በሀይል በወረራቸው አካባቢዎች ግማሸ ሚሊየን ዜጎች ሲፋናቀሉ 4 ሚሊየን የሚደርሱት ደግሞ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለጹ። ኢብኮ እንደዘገበው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ከተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ማዕከል የኢትዮጵያ ሃላፊ አዴል ከድር ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ የህውሓት የሽብር ቡድን ወረራ በፈፀመባቸው በሰሜንና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም ዋግኸምራና ሰሜን ወሎ ዞኖች ግማሽ ሚሊዮን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን 4 ሚሊዮን ደግሞ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ብለዋል። የሽብር ቡድኑ ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች ማህበራዊ ተቋማት በተለይም ትምህርት ቤቶች እና ጤና ተቋማትን … [Read more...] about በትህነግ ሽብር ምክንያት ግማሸ ሚሊዮን ተፈናቅለዋል
ኬኒያ፤ ትህነግ አሸባሪ መባሉ በፓርላማው ሊነሳለት ይገባል አለች
ሐሙስ ዕለት የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በመከረበት ወቅት የኬኒያው ተወካይ ትህነግ አሸባሪ መባሉ ሊነሳለት ይገባል አሉ። ኢስቶኒያ፣ ፈረንሳይ፣ አየርላንድ፣ ኖርዌይ፣ ዩናይትድ ኪንግደምና አሜሪካ በጠሩት በዚህ ስብሰባ ላይ የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ንግግር አድርገው ነበር። ዋና ጸሃፊውም በሰሜኑ የኢትዮጵያ ያለው ግጭት ሊቆም እንደሚገባው በመጠቆም ንፁሀን እየተጎዱ ስለሆነ ሰብዓዊ ዕርዳታ ሊያገኙ የሚገባቸው ምቹ ሁኔታ ባለመፈጠሩ እንዳላገኙ አስረድተዋል። ከዋና ጸሃፊው ንግግር ቀጥሎ የስብሰባው ጠሪዎች በተከታታይ ተናግረዋል። እንቆምለታለን የሚሉትን ዴሞክራሲ በገሃድ መቀመቅ በመክተት ከኢስቶኒያ እስከ ሜክሲኮ ያሉት አገራት በአሜሪካና አውሮጳ የታዘዙትን እንደ በቀቀን በመድገም ሎሌነታቸውን በዓለምአቀፍ መድረክ … [Read more...] about ኬኒያ፤ ትህነግ አሸባሪ መባሉ በፓርላማው ሊነሳለት ይገባል አለች
በመከላከያ ውስጥ ለትህነግ ሲሰልሉ የነበሩ ጽኑ እስራት ቅጣት ተላለፈባቸው
ከትህነግ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ባላቸው የሰራዊት አባላት ላይ ከ8 ዓመት እስከ 18 ዓመት የሚደርስ የፅኑ እስራት ውሳኔ ተላለፈ። የደቡብ ዕዝ ቀዳማዊ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በተለያዩ ወንጀሎች ተሳትፎ በነበራችውና ከትህነግ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ባላቸው የሰራዊት አባላት ላይ ከ8 ዓመት እስከ 18 ዓመት በሚደርስ የፅኑ እስራት ውሳኔ ማስተላለፉ ተገለፀ። ነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም በዕዙ ጠቅላይ መምሪያ በዋለው ችሎት የተሰየመው የዳኞች ምድብ 8 የክስ መዝገቦችን መርምሮ ነው ውሳኔ የሰጠው። በዚህ መሰረት፣ በ1ኛ መዝገብ እነ ኮሎኔል ካህሱ ሀብቱ ፀልይ፣ ኮሎኔል ሀጎስ አሰፋ ወልደንጉሴ እና ሌተናል ኮሎኔል ሀይላይ ገብሩ ገብረተክላይ በ2ኛ መዝገብ ሻምበል ባሻ ክፍሌ ፍስሃ በ3ኛ መዝገብ ኮሎኔል ክፍሌ ፍስሃ በ4ኛ መዝገብ ሃምሳ አለቃ … [Read more...] about በመከላከያ ውስጥ ለትህነግ ሲሰልሉ የነበሩ ጽኑ እስራት ቅጣት ተላለፈባቸው
ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች ተያዙ
በ1,616 የንግድ ድርጅቶች ላይ ዕርምጃ መወሰዱን ፖሊስ አስታውቋል ከአሸባሪው ትህነግ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግሥቴ እንደገለጹት፣ ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ ሰዎችን በማደን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ እየተደረጉ ናቸው። እስካሁን ድረስ በተካሄደው የተቀናጀ ምርመራ ከትህነግ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች፣ በተለያዩ አካባቢዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ አስታውቀዋል። ከተጠረጠሩት ሰዎች በተጨማሪ ለትህነግ ቡድን ሕገወጥ ተልዕኮ መጠቀሚያ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ የንግድ ድርጅቶች ተዘግተው ምርምራ በመካሄድ ላይ እንደሆነ … [Read more...] about ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ 1,642 ሰዎች ተያዙ
“የጸጥታው ም/ቤት በተደጋገሚ ቀጠሮ የሚይዘው ቻርተሩን በመጣስ ነው”
የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክርቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ለመምከር ቀጠሮ የሚይዘውና ስብሰባ የሚቀመጠው የመተዳደሪያ ቻርተሩን በሚፃረር መልኩ የምዕራባውያንን ፍላጎት ለማስፈፀም እንደሆነ የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር አቶ ፀጋዬ ደመቀ አስታወቁ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክርቤት የትግራይን ጉዳይ ለማየት የጠራውን ስብሰባ አስመልክተው መምህር ፀጋዬ ደመቀ በተለይም ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ ስሙ እንደሚያመላካተው የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክርቤት ስብሰባ ሊጠራ እና ሊመክር የሚችለው የዓለምን ጸጥታና ደህንነት ችግር ላይ የሚጥል ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ ምክር ቤቱ በአገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደማያችል በቻርተሩ ላይ በግልጽ ተቀምጣል፡፡ ለዓለም አቀፍ የፀጥታ ስጋት ተብሎ ሊወሰድ የሚችለው ደግሞ በዋነኝነት በሁለት አገራት መካከል … [Read more...] about “የጸጥታው ም/ቤት በተደጋገሚ ቀጠሮ የሚይዘው ቻርተሩን በመጣስ ነው”
በሕገ-ወጡ ብረት ለገበያ እንዲቀርብ ተወሰነ፤ 400 ኩንታል ሲሚንቶና የቴሌ ኬብሎችን ሲያጓጉዙ የነበሩ ተያዙ
በተለያዩ ቦታዎች በሕገ-ወጦች አማካኝነት ተከማችቶ የተገኘ ብረት በሕጋዊ መንገድ ወደ ገበያ ገብቶ እንዲሸጥ እና ለመንግሥት ገቢ እንዲሆን መወሰኑን ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። በ13 የተለያዩ ቦታዎች በህገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘውና በዋጋ አረጋጊ ግብረ-ሀይል በቁጥጥር ስር የዋለው ከ1ሺ በላይ መኪና ብረት በህጋዊ የግብይት ስርዓቱ ውስጥ ገብቶ እንዲሸጥና ገቢው ለመንግስት እንዲገባ መወሰኑን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። በሌላ በኩል በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ሲሚንቶ እና የቴሌ ጥቅል ኬብል በመኪና ሲያጓጉዙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የክፍለ ከተማው የህዝብ ግንኙነት ቢሮ አስታውቋል። ተጠርጣሪዎቹ ትናንት ምሽት በወረዳው አደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ 400 ኩንታል ሲሚንቶ … [Read more...] about በሕገ-ወጡ ብረት ለገበያ እንዲቀርብ ተወሰነ፤ 400 ኩንታል ሲሚንቶና የቴሌ ኬብሎችን ሲያጓጉዙ የነበሩ ተያዙ