
በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 7 አስተዳደር በርካታ ዓይነት እና መጠን ያለው የብረት ክምችት በኢኮኖሚ አሻጥር ቁጥጥር ግብረ-ኃይል መያዙን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።
የኢኮኖሚ አሻጥርን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተዋቀረው ግብረ-ኃይል ለግንባታ አገልግሎት ሊውሉ የሚገባቸው ፌሮ እና ብረታ ብረቶችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ነው የተገለጸው።
ለጊዜው በገንዘብ ለመተመን ያልተቻለ ለረዥም ግዜ ሕገ-ወጥ በሆነ መልኩ የተከማቹ ፌሮ እና ብረታብረቶች በወቅቱ በገበያ ላይ ውለው ቢሆን ኖሮ አሁን ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ሚና ይኖራቸው ነበር ተብሏል።
እንደነዚህ አይነት ተግባር ላይ የተሰማሩ አሻጥረኞች ላይ የሚደረገው ክትትል እና ቁጥጥር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የአቃቂ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ሙሉጌታ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በክፍለ ከተማው ወረዳ 2 አስተዳደር ከግለሰብ ግቢ ውስጥ ተከማችተው የነበሩ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በቁጥጥር ስር ውለው ለኅብረተሰቡ በሸማች ኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል እንዲሰራጭ መደረጉም ተገልጿል።
ገንዘቡ በአ.አ ፋይናንስ አካውንት ገቢ እንዲሆን ግብረ-ኃይሉ ወስኗል።
የኢኮኖሚ አሻጥር ግብረ-ኃይሉ በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ምርቶች ውስጥ መኮሮኒ፣ ሩዝ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ምስር እና ሌሎች ምርቶች የሚገኙበት ሲሆን በአጠቃላይ ከ860 ኩንታል በላይ የሚገመት ምርቶች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
እንደ አዲስ አበባ ከተማ እስካሁን በተደረገ ክትትልና ቁጥጥር እጅግ ከፍተኛ የሆነ የብረታ ብረት ዓይነቶችና በቢሊዮን ብር የሚገመት ዋጋ ያላቸውን የብረታ ብረት ውጤቶች መያዝ ተችሏል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply