
ለአሸባሪዎቹ የህወሓትና ሸኔ ቡድኖች በተለያዩ ህገወጥ መንገዶች ገንዘብ ሲያሰባስቡና ሲያስተላልፉ የነበሩ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ አሻጥር በመፈጸም ህብረተሰቡን ለአመጽ ለማነሳሳት ሙከራ ሲያደርጉ የነበሩ በአዲስ አበባ 51 እንዲሁም በአፋር ክልል 6 በድምሩ 57 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

ግብረሃይሉ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ክፍለ ከተማዎች ተሰማርተው ከአሸባሪዎቹ ህወህትና ሸኔ ቡድን ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት በመፍጠር በህገወጥ መንገድ ገንዘብ ሲያሰባስቡና ሲያስተላልፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ ማስረጃዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ አንድ አንድ ተጠርጣሪዎች በህግ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በመሰማራት ለሸብርተኛው የህወሓት ቡድን መረጃዎችን በመሰብሰብ በሚስጥር ለመስጠት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ እንዲሁም ለሽብር ቡድኑ የፋይናንስ ምንጭና የሎጀስቲክስ ድጋፎችን ለማድረግ በህቡእ ሲንቀሳቀሱ በተደረገው ክትትል መታወቁን ያመለከተው የጋራ ግብረ ሃይሉ መግለጫ፤ በቅርቡም ከአሜሪካና ከሌሎች የጁንታው ተባባሪዎች የተላከላቸውን መጠኑ በርከት ያለ ገንዘብ ለሽብር ቡድኑ አፈቀላጤ ለጌታቸው ረዳ እና ለሌሎችም የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች በድብቅ ወደ መቀሌ ለመላክ ሙከራ እያደረጉ እያለ በተደረገባቸው ጥብቅና ሚስጥራዊ ክትትል መያዛቸውን አስታውቋል፡፡ (ኢብኮ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ሰማነው! አየነው! ኦነግ ሸኔ ማለት ኦሮሞንም ሆ ሌላውን ህዝብ የማይወክል አሳፋሪና አሸባሪ ቡድን ነው! ያለምንም ይቅርታ ግብአተ መሬቱ መረጋገጥ አለበት! አስተባበሪዎቹን ተመልከት ከየት ናቸውና ነው ማንን ነጻ የሚያወጣው!