በ2014 በጀት ዓመት በሐምሌ ወር የኢንደስትሪ ፓርኮች የወጪ ንግድ 23 ነጥብ 88 ሚሊዮን የአሜካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 16 ነጥብ 41 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በዚህም የእቅዱን 69 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል። የተገኘው ገቢ ከባለፋው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ7 ነጥብ 47 ሚሊዮን የአሜካን ዶላር ወይንም ወይንም የ14 ነጥብ 20 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ የተገለፀ ሲሆን ይህም ጭማሪ አዳዲስ አምራቾች ወደ ስራ በመግባታቸዉ የተገኘ መሆኑ ታውቋል፡፡ ደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ በሐምሌ ወር ወደ ወጪ ከላከው ምርት የዕቅዱን 633 በመቶኛ ገቢ በመፈፀም ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል፡፡ በመቀጠልም ድሬደዋ እና ኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደቅደምተከተላቸው … [Read more...] about ከኢንዱስትሪ ፓርኮች የወጪ ንግድ በሐምሌ ወር 16.41 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ