• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በአሸባሪው ቁንጮ ፃድቃን ገ/ትንሣይ የሚመራው የጠላት ኃይል ድባቅ ተመታ

August 20, 2021 09:54 am by Editor 1 Comment

በአሸባሪው ቁንጮ ፃድቃን ገ/ትንሣይ የሚመራው የጠላት ኃይል በሰሜን ወሎ ግንባር በተሰማራው የመከላከያ ሠራዊት መመታቱ ተገለጸ፡፡

ዓርሚ ሁለት የሚባልና በከሀዲው ሜ/ጄ/ል ዮሀንስ፣ በምክትሉ ከሀዲው ማዕሾ በየነ እና ከሀዲው ከበደ ፍቃዱ እንዲሁም በሜካናይዝድ አዛዡ ከሀዲው ኮ/ል ገ/ስላሴ የተመራው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ሀይል ድባቅ መመታቱ ተገልጿል፡፡

በግንባሩ የተሰማሩ ሁለት ክ/ጦር አዛዦ እንደተናገሩት፣ መንግስት የተናጠል የተኩሥ አቁም እርምጃውን ካነሳ በኋላ ከበላይ በተሠጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ጋሸናን ዋና ማዕከል በማድረግ ከዋድላ እስከ ላልይበላ መስመር ላይ የነበረውን የአሸባሪውን ሀይል መደምሠሳቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ጠላት በጀግኖቹ የሠራዊት አባላት፣ ልዩ ሀይል እንዲሁም የሚሊሻ አባላትና የአካባቢው አርሶ አደር ከበባ ውስጥ ሆኖ ይገኛል ነው የተባለው፡፡

ይህ የተዳከመ የጠላት ሀይል በጋሸና፣ መቄት፣ ሙጃ፣ በንፋሥ መውጫ አካባቢዎች እየተመታና እየተበተነ ይገኛል ብለዋል፡፡

በነዚህ አካባቢዎች በጠላት ላይ በተደረገ ጥቃት 3 ድሽቃ፣ 6 ሺህ የድሽቃ ጥይት፣ 87 የዕጅ ቦምብ፣ 229 ክላሽንኮቭ ነፍስ ወከፍ መሣሪያ፣ 5 ሺህ የክላሽ ጥይት፣ 1 የጦርሜዳ መነፅር ሲማረክ፣ በርካታ ቁጥር ያለው የሰው ኃይል እና ጠላት ይጠቀምባቸው የነበሩ 2 መድፎች እንዲሁም አንድ ዙ 23 መደምሰስ መቻሉን ዋና አዛዦቹ ገልፀዋል ሲል የመከላከያ ሰራዊት ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የፀረ ሽብርና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት በእነሌተናል ጀኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ መዝገብ የተሰከሰሱ ግለሰቦችን ፌዴራል ፖሊስ ከመከላከያ ጋር በመተባበር ይዞ እንዲያቀርባቸው ትእዘዝ ሰጥቷል።

ሌተናል ጀኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ፣ ብርጋዴሬ ጀነራል ምግባረ ኃይሌ እና ብርጋዴር ጄኔራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ 74 የጦር መኮንኖች የነበሩ ግለሰቦች ናቸው ክስ የተመሰረተባቸው።

አቃቤ ህግ ሁሉም ተከሳሾች የህወሓት የሽብር ቡድንን ተልእኮ በመቀበል  ህገወጥ ወታደራዊ ቡድን በማቋቋም የሰሜን እዝንና  የፌዴራል ፖሊስን ብሎም በአማራ እና በአፋር ክልሎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል በሚል በሽብር ወንጀል እንደከሰሳቸው ይታወቃል።

ችሎቱ በግለሰቦቹ ላይ ለዛሬ ክስ ለመመልከት ነበር ቀጠሮ ይዞ የነበረው::

ይሁን አንጂ ሶስቱ ተከሳሾች ከዳንሻና አዋሽ ማቆያ ሌሎችም ከቃሊቲ ማቆያ በመረጃ ልውውጥ  ስህተት  ሊቀርቡ አልቻሉም ተብሏል።

በዚሁ መሰረት የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ በትክክል ተተግብሮ በአካል የሚቀርቡ 20 ተከሳሾች ለጥቅምት 3 ቀን 2014 ዓ.ም ቀርበው ክስ እንዲነበብ ሲል ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

በዚሁ ቀን በእነ ሌተናል ጀኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ ጨምሮ ያልተያዙ 54 ተከሳሾች በፌዴራል ፖሊና በመከላከያ በትብብር ተይዘው እንዲቀርቡ ሲል ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ አስተላልፏል። (ዘጋቢ መብራቱ አራርሶ፤ ፎቶ ማርቆሥ አለሙ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist, tsadkan

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    August 24, 2021 11:07 am at 11:07 am

    የወያኔ እብዶች ሃገርና ወገን በሰላም እንዳይኖር ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም። ጊዜ ሲጥል ግን የሚያነሳ የለም። በወያኔ ላይ ጸሃይ እየጠለቀች ነው። የሚያሳዝነው ግን አሁንም ያው በማስፈራራትና በግድ የትግራይን ልጆች ልክ እንደ በፊቱ በውሸት ትርክት ለእሳት እየዳረጓቸው ነው። የወያኔ ታጣቂዎችም በየደረሱበት ያው የተካኑበትን የመከራ ዝናብ ማዝነብ ሙያ በህዝባችን ላይ እያዘነቡ ነው። የምዕራቡ የዜና አውታሮች የሚያናፍሱት ቅይጥና ውሸትን የተላበሰ ወሬ ለጊዜው ለወያኔ ጀሮ የሚስማማ ቢመስልም ሆን ተብሎ ከአሜሪካውና ከአረቡ የክፋት ኮሮጆ የተወሰደ በመሆኑ ጊዜ ወስዶ ይመራል። ምዕራቡ ዓለም ደንባራ ነው። እውነትን መስማትም ሆነ ማየት አይፈልጉም። ለዚህም ነው ለእርዳታ የገባው ብስኩት ለወያኔ ወራሪ ጦር ሲታደል ቆመው የሚያዪትና ተጨማሪ ስንቅና ትጥቅ የሚያቀብሉት። ጥቁር ለጥቁር ቢላተም ምን ተዳቸው። እኛ ግን እርጉሞች ነን። ወንድምና እህታችን፤ ልጅና አባታችን፤ እናታችን ገድለን የምንፎክር ሙታኖች። በዘር የሰከርን እውነት የማትታየን ጨለምተኛ ትውልዶች። የአረብና የነጭ አገልጋይ መሆን እንደ ትልቅ የህይወት ለውጥ የሚታየን። ለመኖር እህቶቻንና ወንድሞቻችን ገቢያ ላይ የምናወጣ ጉዶች። የሆነው እሱ ነው። ከአፍጋኒስታኑ ታልቫን የማትለየው ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ ግፍ እንድታደርስ የሚጎተጉቱት በዚያው የሚኖሩ የወያኔ ሸቀጥ ተሸካሚዎች ናቸው። የወያኔ ባለስልጣኖችና ጀሌዎቻቸው የሙሉ ጊዜ ሥራቸው ኢትዪጵያን ማጥላላት ነው። ትርፍ የለሽ ፓለቲካ፤ ሁሌ ተጨቆንኩ እያሉ ኡኡታ ማሰማት አይሰለችም? ራሱ በድሎ ራሱ የሚያለቅሰው ወያኔ ከሰው ዘር ያልተፈጠረ የድርቡሾች ስብስብ ነው። ይህን ለመረዳት ዘርና ቋንቋን ተገን ሳያረጉ ከበረሃ እስከ ከተማ ከዚያም ተመልሶ በረሃና አሁን እስካለው ነፍሴ አውጪኝ የወያኔን ሩጫ መርምሮ መረዳት ይገባል።
    ጊዜው ርቋል ግን ትዝታው አለ። አንድ የውጭ ሃገር የእርዳታ ሰጪ ስብስብ ሃይል በሱዳን በኩል ወደ ትግራይ በተክለወይን አሰፋ እየተመራ ገብቷል። ጊዜው ወያኔና ደርግ የትግራይን ህዝብ የሚቀራመቱበት ወራት ነበር። ደርግ ሰፈራ እያለ ወያኔ ደግሞ ሁሉም በሰፈራ ከተነሳ ለእኔ የሰው ድካፍ አነሰኝ በማለት ሰውን እንደ ከብት የሚጓተቱበት ዘመን ነበር። ታዲያ እርዳታ ሰጪዎቹ በሰጠናችሁ ገንዘብ ምን ገዛችሁ ሲሏቸው በቆሎና ስንዴ ገዝተናል የምንገዛውም ከዚህ ሰው ነው በማለት አሁን አውስትራሊያ ውስጥ የሚኖርን አንድ የወያኔ ሰው “ሃጂ መሃመድ” በማለት ያስተዋውቋቸዋል። ከፊት ለፊት በኩንታል ሞልቶ ከተከመረው ነገርዬ 90% በአሽዋና በአፈር የተሞላ ጆኒያ ነው። ከላይ ግን ጥቂት ስንዴና ማሽላ የያዙ ጆኒያዎች አሉ። ያንን በመነካካት ለወያኔ ሰብአዊ ጉዳይ አቀባዪች አሳይተው ገንዘቡን እንደተከፋፈሉት ዛሬ በህይወት ያሉ ሊመሰክሩ ይችላሉ። ወያኔ ለትግራይ ህዝብ ሲጀመር ጀምሮ ገዶት አያውቅም። በደርግ ውጊያ ከሞቱት ይልቅ ወያኔ ራሱ የገደላቸው የትግራይ ልጆች ይበልጣሉ። እነ ጻድቃንና ሌሎች የወያኔ የሩቅና የቅርብ የአሁኑ ጦርነት አፋላሚዎች በምንም ሂሳብ እንደማይሳካ ያውቁታል። ግን በባህሪያቸው በሰው ልጆች ላይ ሰቆቃ ማድረስ የቀን ስራቸው ስለሆነ አሁንም በአፋር፤ በአማራና በትግራይ ሰዎችን ያስለቅሳሉ፤ ንበረት ያወድማሉ፤ ሰውና እንስሳትን በጥይት ይቦድሳሉ። እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚሉት ይህ አይነቱን ተግባር ነው።
    ሮኬት ወደ አማራና ኤርትራ ያስወነጨፈው ወያኔ ዛሬ ሮኬቶች በእጅ ቢኖሩ ከተሞችን አመድ ማድረጉ አይቀሬ ነው። ስለሆንም ይህ ድርጅት ከስሩ ካልተቦደሰና የእሳት ማገዶ እስካልሆነ ድረስ ኢትዮጵያም ሆነ ጎረቤት ሃገሮች ሰላም አይኖራቸውም። አሁን የሚበላ የጠፋባት ይባስ ብሎ ደግሞ ባልታሰበ ጎርፍ የተጥለቀለቀችው ሱዳንና ወታደራዊ መሪዎቿ የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው። ለወያኔ መጠለያና ማሰልጠኛ ድሮም ዛሬም የሚሰጡት ለዚያ ነው። ለዚህም ይመስለኛል ወያኔ አፍቃሪው Martin Plaut በ71 ዓመቱ የወያኔ ቋሚ ጠበቃ በመሆን ጦርነቱ በተነሳ ማግስት “የውጊያውን ውጤት የሚወሰነው በሱዳን ነው” በማለት በቲዊተር ገጽ ላይ ያሰፈረው። ውሻ በበላበት ይጮሃል እንዲሉ ነው።
    ባጭሩ ትግራይን ከትህነግ ለማላቀቅ የሚቻለው የትግራይ ልጆች አንድ ሆነው ሲቆሙ ብቻ ነው። አሁን በዚህም በዚያም የተገደለና የተማረከው ከሁለቱም በኩል ሲሰላና ዘመድ ሲያውቀው የሚፈጥረውን ቁጣና ወያኔን የመፈንገል ቁርጠኝነት ምንም ዓይነት የወያኔ የፓከቲካ አሻጥር አያበርደውም። ያኔ የወያኔ መሪና ደጋፊዎች መግቢያቸው የት ይሆን? በሰፈሩት መስፈሪያ መሰፈራቸው አይቀሬ መሆኑ ከአሁኑ ገሃድ እየሆነ ነው። ጠብቀን እንይ። እስከዛው መዘናጋት ግን ለወያኔ ጉልበት መስጠት ነው። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዛሬ ‘ኃያል ነን’ የሚሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ በሚዲያ /በመረጃ/፣ በዲፕሎማሲ፣ በሳይበር እና በተልእኮ የተቀነባበረ ‘ግራጫ ጦርነት’ እያካሄዱባት ነው” ጠ/ሚ ዐቢይ July 7, 2022 10:03 am
  • የኦሮሞ ልሂቃንና ፖለቲከኞች በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን “የዘር ማጥፋት” ወንጀል እንዲያወግዙት አብን ጠየቀ July 6, 2022 01:38 pm
  • “አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ July 6, 2022 01:53 am
  • “በኢትዮጵያዊያን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሀገሪቱን ማተራመስ አለብን” አይማን አብድልአዚዝ ግብጻዊው ፖለቲከኛ July 5, 2022 12:57 pm
  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule