መላ ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል፤ ከንፈሩ ደርቋል። ለሁለት ቀናት ምግብ አላገኘም። ድንጋጤ አለቀቀውም። ከማይካድራ ግድያ አምልጦ ሁመራ ከተማ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በር ላይ ያገኘነው ወጣት ዳንኤል ማሚን። የደቡብ ክልል የቴፒ ተወላጅ ነው፤ አገር ሰላም ብሎ በማይካድራ ልብስ እየነገደ መኖር ከጀመረ 13 ዓመት ሆኖታል። በዚች ከተማ ይህን ያህል ሲኖር የከፋ አይደለም፤ ቀለል ያለ ችግርም አጋጥሞት አያውቅም። በሚኖርባትና ህይወቱን ለማሻሻል በሚደክምባት ከተማ ቤትና ንብረትም አፍርቷል። ከሰባት ቀናት በፊት ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ በማይካድራ ከተማ በአማራና በሌሎች ብሄሮች ተወላጆች ላይ ያልታሰበ፣ አስደንጋጭና ዘግናኝ ግድያ ሲፈጸም በዓይኑ ተመልክቷል፤ እሱም ከዚህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ አምልጦ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ወደ ዋለችው ሁመራ ከተማ መምጣቱን ይናገራል። የትግራይ ልዩ … [Read more...] about “እየደበደቡ፤ በሳንጃ አንገታቸውን እየቀሉ ሲገሏቸው ተመልክቻለሁ” – የማይካድራው ጭፍጨፋ የዓይን እማኝ
Archives for November 2020
የትግራይ ክልል መዋቅር ዳግም ይደራጃል
የትግራይ ጊዜአዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ በጊዜአዊ አስተዳደሩ የሚሰሩ ስራዎችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። ዶ/ር ሙሉ በመግለጫቸው የትግራይ ክልል መዋቅር ዳግም እንደሚደራጅ ተናግረዋል። የክልሉ ካቢኔና የዞን አስተዳደርም እንደአዲስ እንደሚዋቀርም የተናገሩት ዶ/ር ሙሉ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች እንዳሉ ይቀጥላሉ ብለዋል። መንግስት የጀመረውን የህግ ማስከበር እርምጃ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ይሰራልም ብለዋል። ከፅንፈኛው ህወሓት ቡድን ነፃ የወጡ አካባቢዎች ላይ መዋቅሮችን በመዘርጋት ህዝቡ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው እንዲመለስ እንደሚሰራም ተናግረዋል። የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን ላለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል በክልሉ ምንም አይነት የልማት ስራ አልተሰራም ያሉት ዶክተር ሙሉ ህግ የማስከበሩ ስራ … [Read more...] about የትግራይ ክልል መዋቅር ዳግም ይደራጃል
“በዚህ ውጊያ አላምንበትም” አብረኸት
አብረኸት የጁንታው ታጣቂ የነበረችና እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት ከሰጡ ውስጥ አንዷ ነች። ገና የ21 ዓመት ወጣት ናት። ወጣቷ በ2011 ዓ.ም የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል በብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ስልጠና ወስዳለች። የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊት አባል ሁና ነገሌ ቦረና ተመድባም ግዳጇን እየተወጣች ሳለ በጠና ታምማ ከውትድርናው ዓለም ተሰናብታ ወደ ቤተሰቦቿ መመለሷን በስፍራው ተገኝቶ ላነጋገራት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅይ ዘጋቢ ገልጻለች። የአብረኸት ህመም መጥናት ከምትወደው መከላከያ ቢለያትም ከጁንታው ዕይታ ግን መሰወር አልቻለችም። በጠላ ንግድ የሚተዳደሩትን እናቷን እያገዘች ኑሮን ብትቀጥልም፤ የጁንታው አባላት የአብረኸትን ወታደርነት ያውቁ ነበርና የጁንታውን ታጣቂ እንድትቀላቀል በእናቷ በኩል ግፊት ማድረግ ጀመሩ። ጁንታው የአብረኸትን እናት ሌት ተቀን … [Read more...] about “በዚህ ውጊያ አላምንበትም” አብረኸት
ጃዋር “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ”
በቅርቡ ጃዋር መሐመድን ማረሚያ ቤት ድረስ ሄደው ከጎበኙ መካከል አንደኛው ከጃዋር አንደበት የሰሙትን ማመን እንዳቃታቸው ይገልጻሉ። ጃዋር ያለፈበትን መንገድ እያሰላ በጸጸት ውስጥ ያለ ይመስላል። በአጭር ጉብኝታቸው “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ” በማለት ቅዝዝ ብሎ የነገራቸው ጠያቂው እሱን ከተሰናበቱ በኋላ ነበር ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ሁኔታውን ያጫወቱት። ለተለያዩ ሚዲያዎችና በጃዋር ዙሪያ ለነበሩ እንቅስቃሴዎች እንግዳ ያልሆኑት እኚሁ ሰው ለጎልጉል ዘጋቢ መነሻ ሃሳብ ከሰጡ በኋላ ዘጋቢያችን በርካታ መረጃዎችን አሰባስቦ የሚከተለውን ሪፖርት አዘጋጅቷል። በሪፖርቱ አስቀድሞ የተሰባሰቡና ጊዜ ሲጠብቁ የነበሩ መረጃዎች ተካተዋል። ሪፖርቱ አንባቢያን የራሳቸውን ስሌት እንዲያሰሉና አቅም ያላቸው ይበልጥ ጉዳዩን እንዲያጠኑት የሚያነሳሳ ይሆናል። ጃዋርና “የአንድነት ኃይሎች” የት፣ … [Read more...] about ጃዋር “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ”
34 የወንበዴው ትህነግ የፋይናንስ ተቋማት ታገዱ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወንበዴው ህወሃት/ትህነግ አገር ለማፍረስ ዓላማ ሲጠቀምባቸው የነበሩት 34 የፋይናንስ ተቋቱን ማገዱን ይፋ አድርጓል። እንደ ኢቲቪ ዘገባ ከታገዱት የበረኻ ወንበዴዎቹ ድርጅቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፤ ሜጋ ማተሚያ፣ ሱር ኮንስትራክሽን፣ ጉና የንግድ ሥራዎች፣ ኢፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ፣ ሠላም የህዝብ ማመላለሻ ማህበር፣ ኢፈርት ኃ/የተ/የግ ማህበር እገዳው ከተላለፈባቸው መካከል ናቸው። ጎልጉልን ጨምሮ የተለያዩ የሚዲያ አውታሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ወዘተ ለትህነግ የፋይናንስ ምንጭ የሆነው ኤፈርት ወደ ሕዝብ ሃብትነት እንዲመለስ ሲወተውቱ መቆየታቸው ይታወሳል። ስብሃት ነጋና ቤተሰቡ የተቆጣጠረው ኤፈርት ግብር … [Read more...] about 34 የወንበዴው ትህነግ የፋይናንስ ተቋማት ታገዱ
መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ በበርሜል ወድቆ ተገኘ
በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ስሙ ኢንፎኔት ኮሌጅ አካባቢ አንድ በርሜል ገንዘብ ወድቆ ተገኘ። በዚህ ስፍራ በአንድ በርሜል ተጠቅጥቆ መገኘቱን የኢትዮ ኤፍ ኤም ሪፖርተር በአካል ተገኝቶ አረጋግጧል። የተገኘው ገንዘብ የኢትዮጵያ ብር እና ዶላር ሲሆን ገንዘቡን ማን እንደጣለው ያልተተረጋገጠ ሲሆን የአካባቢው ፖሊስ በመኪና ጭኖ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰደውም ሪፖርተራችን አረጋግጧል። በተያያዘ ዜና በዚሁ ወረዳ ጣልያን ሰፈር ልዩ ስሙ ጉሊት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ አዛውንት ቤት ቁጥሩ እስካሁን ያልተረጋገጠ ገንዘብ በማዳበሪያ እና በመዘፍዘፊያ አስቀምጠው ተይዘዋል። አዛውንቷ ለረጅም አመታት በልመና ስራ የሚተዳደሩ ናቸው የተባለ ሲሆን የገንዘቡን መጠን ለማወቅ የአካባቢው ወጣቶች እና ፖሊስ በጋራ ቆጠራ እየተካሄደ መሆኑን ሰምተናል። አዛውንቷ … [Read more...] about መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ በበርሜል ወድቆ ተገኘ
“የትግራይ ተወላጅ የፖሊስ አባላት አፈሙዝ ወደ እኛ በማዞር የፈጸሙብን ክህደት በጣም አሳዝኖናል”
በትግራይ ክልል መቀሌ ሀራ ገበያ ዓዲ ጉደም ምድር ባቡር ፕሮጀክት በሚጠብቁት ላይ ከተፈጸመ ጥቃት የተረፉት ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት አዲስ አበባ ከተማ ገብተዋል። የህዝብና መንግስት መሰረተ ልማቶችን በመጠበቅ ከ10 ዓመታት በላይ መቆየታቸውን የገለጸው ዋና ሳጅን ድረስ ስንሻው የተለመደዉን መደበኛ የጥበቃ ስራችን እያከናወን በነበርንበት ወቅት በፕሮጀክቱ ባሉ ሳይቶች ላይ የነበሩ የስራ ባልደረቦቻችንን ትጥቅ በማስፈታት፣ አፍነውና እጃቸውን በካቴና አስረው ወደ መቀሌ ሲወስዷቸው እጃችንን ከምንሰጥ ብለን ወደ ጫካ በመግባት ለሚተኮስብን ተኩስ ምላሽ በመስጠት ለማምለጥ ችለናል ብለዋል። እኛ ለአንድ ብሔር የቆምን ሳይሆን ከሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ የተውጣጣንና ሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድነት ስንጠብቅ የኖርን በመሆኑ እንደዚህ አይነት የሀገር ክህደት ይፈጸምብናል ብለን አልጠበቅንም … [Read more...] about “የትግራይ ተወላጅ የፖሊስ አባላት አፈሙዝ ወደ እኛ በማዞር የፈጸሙብን ክህደት በጣም አሳዝኖናል”
በርካታ ቁጥር ያለው የህወሓት የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ሥር ዋለ
ታጣቂው ህወሓት ልዩ ኃይል በሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይልና በሚሊሻ አባላት እየተደመሰሰ ይገኛል። በዚህ ታላቅ ጀብድ ሰራዊቱ የህወሓት ስግብግብ ኃይል ለጦርነት እየተጠቀመባቸው የነበሩ ከ230 በላይ ክላሽንኮቭ፣ ከ1 ሺህ በላይ የእጅ ቦምብና ሌሎች ተተኳሽ መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ዕዝ የሰው ሐብት ልማትና የሚዲያ አስተባባሪ ኮሎኔል ደጀኔ ጸጋዬ ተናግረዋል። እየተካሄደ ባለው ህግ የማስከበር ለህልውና ዘመቻ የአማራ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት በተሰጣቸው ቀጣና በጠላት ላይ ከባድ ወታደራዊ ጥቃት በመፈጸምና በመደምስስ ግዳጃቸውን በብቃት እየፈጸሙ መሆኑንም ማመላከታቸውን ፋና ዘግቧል። በሌላ በኩል በጋምቤላ ከልል ዲማ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 5 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያና አንድ F1 የእጅ ቦንብ ከስድስት ተጠርጣሪ ጋር መያዙን … [Read more...] about በርካታ ቁጥር ያለው የህወሓት የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ሥር ዋለ
ህወሃትን ያገለግሉ የነበሩ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች እንዲታገዱ ተወሰነ!
በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸውን የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች እንዲታገዱ መወሰኑን ፌዴራል ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎቹ በቀጠሯቸው የጥበቃ አባላትና ተባባሪዎቻቸው ባንኮችንና የተለያዩ ድርጅቶችን ሲዘርፉ እና ሲያዘርፉ ነበርም ብሏል። በተጨማሪም 'የህወሓትን ተልዕኮ ለመፈፀም የተለያዩ ግለሰቦችን ወደ ኤጀንሲዎቹ አስርገው በማስገባት እና የጦር መሣሪያ በማስታጠቅ በኅብረተሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እያሴሩ ነበር' ሲል አስታውቋል። በዚህም:- 1. ንስር የሰው ሃይል እና የጥበቃ አገ/ሃ/የተ/የግ/ማ 2. አጋር የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ 3. ስብኃቱና ልጆቹ የንብረት አስ/ጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ 4. ሰላም ሴኩሪቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማ 5. ኃይሌ ተክላይ … [Read more...] about ህወሃትን ያገለግሉ የነበሩ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች እንዲታገዱ ተወሰነ!
በወጋገን ባንክ በርካታ የጦር መሠሪያ፤ በሱር ኮንስትራክሽን ደግሞ የሬዲዮ መገናኛ ተገኘ
በወጋገን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ለጥበቃ አገልግሎት ከሚያስፈልገው ውጭ የጦር መሠሪያ ተከማችቶ መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ለሸገር ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡ ከተገኙት መሣሪያዎች አንዳንዱ በፀጥታ ኃይሉ እጅ የሌሉ ጭምር መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡ በተያያዘ ዜናም 97 የእጅ ሬድዮ 23 የረጅም እርቀት የትከሻ መገናኛ ሬድዮ ከሱር ኮንስትራክሽን በብርበራ መያዙን ትላንት በተሰጠ መግለጫ ተጠቅሷል፡፡ በከተማው የተያዙ ባለሀብቶችም እንዳሉ ይሰማል ይህስ በምን መስፈርት ነው ሲል ሸገር ላቀረበላቸው ጥያቄ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው የሕወሓትን ቡድን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የደገፉ ባለሀብቶች በማስረጃ ስለመያዛቸው ለጣቢያው ገልጸዋል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በወጋገን ባንክ በርካታ የጦር መሠሪያ፤ በሱር ኮንስትራክሽን ደግሞ የሬዲዮ መገናኛ ተገኘ