የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የጁንታው ሕወሓት ቡድን ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የጥፋት ቡድኑ አባላት ከኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች ፀረ-ሰላም ሃይሎች ጋር በመቀናጀትም ከተለያዩ ክልሎች አገርን የማፍረስ ተልዕኮ ያላቸውን ኃይሎች በመመልመል ትግራይ ክልል ድረስ በመውሰድ ለእኩይ ተልዕኮቸው ስኬት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎችን በማድረግ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ብሄርን ከብሄር በማጋጨት እና በሃይማኖት ሽፋን ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በማድረግ በርካታ ንፅሁን ዜጎች እንዲገደሉ፣ በአካልና በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በላከው መግለጫ አመልክቷል፡፡ እነዚህ የሀገር ህልውናን አደጋ ላይ በመጣል እንዲሁም ህገ-መንግስቱንና … [Read more...] about በ96 የህወሃት ወንበዴዎች ላይ የፍርድ ቤት ማዘዣ ወጣባቸው
Archives for November 2020
የማይካድራ ዕልቂት
በምዕራባዊ ትግራይ ሁመራ አቅራቢያ «ማይካድራ» በተባለው አካባቢ የትግራይ ልዩ ኃይል ባልታጠቁ የአማራ ተወላጆች ላይ በሌሊት አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙን ከሞት ያመለጠ የዐይን እማኝ ገለፀ። ጥቃቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲል ደግሞ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ዐስታውቋል። በምዕራባዊ ትግራይ ሁመራ አቅራቢያ «ማይካድራ» በተባለው አካባቢ የትግራይ ልዩ ኃይል ባልታጠቁ የአማራ ተወላጆች ላይ በሌሊት አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙን ከሞት ያመለጠ የዐይን እማኝ ገለፀ። ጥቃቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲል ደግሞ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ዐስታውቋል። ድርጊቱ የተጀመረውን ሕግ የማስከበር ሂደት ህወሓት ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲቀየር የዘየደው መላ ነውም ብሎታል። አንዳንድ የአማራ ክልል ነዋሪዎች የህወሓት የተስፋ መቊረጥ ስሜት ነው፤ ኅብረተሰቡ ህወሓት በዘየደው የብቀላ ሂደት … [Read more...] about የማይካድራ ዕልቂት
የበረኻ ወንበዴዎቹ ያለከመከሰስ መብት ተነሳ
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። ዛሬ የተሰበሰበው የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው በወንጀል የተጠረጠሩ የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል። በዚህም መሰረት፦ 1. ደብረጸዮን ገብረሚካኤል 2. አስመላሽ … [Read more...] about የበረኻ ወንበዴዎቹ ያለከመከሰስ መብት ተነሳ
በወልዲያ ከተማ የወንበዴዎቹን ተልዕኮ ሊያስፈጽሙ የነበሩ 25 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ 25 የህወሓት ተልዕኮ ተቀብለው የጥፋት ሴራቸውን በንፁሃን ላይ ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ውለዋል። የጥፋት ኃይሎቹ በነዋሪዎች እና በፀጥታ ኃይሉ የጋራ ጥረት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወልዲያ ከተማ የህዝብ ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ትዕዛዙ ጫኔ አስታውቀዋል። ኢንስፔክተሩ ግለሰቦቹ በተያዙበት ወቅት የተለያዩ መታወቂያዎች መያዛቸውን ነው የተናገሩት። እንዲሁም ከአንድ ሰው ላይ እስከ ዘጠኝ የተለያዩ የባንክ ደብተሮች በውስጣቸውም እስከ 400 ሺህ ብር ድረስ ተገኝቶባቸዋል ነው ያሉት። ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ አስፈላጊውን ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝም ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።©ፋና ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በወልዲያ ከተማ የወንበዴዎቹን ተልዕኮ ሊያስፈጽሙ የነበሩ 25 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
“ምዕራብ የትግራይ ክልል ነጻ ወጥቷል” የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ ከጥቅት ደቂቃዎች በፊት በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ይፋ እንዳደረጉት ምዕራባዊ የትግራይ ክልል ነጻ መውጣቱን ተናግረዋል፡፡ ሆኖም የበረሃ ወንበዴዎቹ ስብስብ በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ዘግናኝ ግፍ ነጻ በወጡ ከተሞች እየታየ እንደሆነ በመልዕክታቸው በመግለጽ “ሙት ይዞን እንዳይሞት” በማት ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል። መልዕክታቸው እንዲህ ይነበባል፤ “ለስግብግቡ ጁንታ ግፍ እስትንፋሱ፣ ጭካኔ ነፍሱ ነው። ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ሽራሮን ሲቆጣጠር፣ እጅና እግራቸውን የፊጥኝ ታሥረው የተረሸኑ የመከላከያ አባላትን አግኝቷል። ጭካኔው ልብ ሰባሪ ነበር። ዓላማው ኢትዮጵያን መስበር ነው። አላወቁም ከአልማዝ የጠነከረች መሆኗን። ዓላማው ሠራዊታችንንና ሕዝቡን አስቆጥቶ ለበቀል ርምጃ ማነሣሣት ነው። አላወቁም … [Read more...] about “ምዕራብ የትግራይ ክልል ነጻ ወጥቷል” የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ
የፈረሰውን የክልል መስተዳድር በፈረሰው ስሙ መጥራት ሕገወጥነት ነው
ያለፈው ሳምንት መጨረሻ አካባቢ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በህወሃት የሚመራውን የትግራይ ክልል መስተዳድር አፍርሶታል። ምክር ቤቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የትግራይ ክልል በክልሉ በሚገኘው እና በአገር መከላከያ ሰራዊት ስር ባለው በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነው ብሏል። ምክር ቤቱ ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ውሳኔ አሳልፏል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ያከናውናቸዋል ተብሎ ከተሰጡት ስራዎች መካከልም ሀ) አስፈፃሚ አካሉን ይመራል፣ ያስተባብራል፤ ለ) የጊዜያዊ አስተዳደሩን ኃላፊዎች ይመድባል፤ ሐ) ሕግና ሥርዓት መከበሩን … [Read more...] about የፈረሰውን የክልል መስተዳድር በፈረሰው ስሙ መጥራት ሕገወጥነት ነው
በጉጂ ዞን በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ
በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት መደምሰሳቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ኡዶ ተናግረዋል። በተጨማሪም በእርምጃው 17 የኦነግ ሸኔ አባላት መቁሰላቸውን እና የቡድኑ 13 አባላት ደግሞ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልፀዋል። እርምጃው የተወሰደው የፀጥታ አካላት እና ህብረተሰቡ በጥምረት በሰሩት ስራ እንደሆነ መናገራቸውን ከኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ከአጥፊው ህወሓት ቡድን ተላላኪዎች በተለያዩ አካካባዎች የሽብር ጥቃት ለማድረስ ተልዕኮ ወስደው በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ሰር መዋላቸውን ደግሞ የጉጂ ዞን የፀጥታና አስተዳዳር ቢሮ ኃላፊ አቶ ዋሌ ዱንጎ ተናግረዋል። የዞኑ የፀጥታ አካላት በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ወረዳዎች እና ከተሞች እስካሁን ባደረጉት … [Read more...] about በጉጂ ዞን በተወሰደ እርምጃ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ
ከወንበዴው ጥቃት ያመለጡ 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ደባርቅ ገብተዋል
ህወሐት ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል መቀሌ ላይ ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በጠገዴ አርማጭሆ በኩል ደግሞ በአማራ ልዩ ኃይል አባላትና ገበሬዎች ላይ የወረራ ሙከራ እንዲሁም በተከዜ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ጥበቃ ላይ በነበሩ የፌደራል ፖሊሰ አባላት ጥቃት መሰንዘሩ ይታወሳል። ከጥቃቱ የተረፉት 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ህዳር 01/2013 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን መቀመጫ ደባርቅ ከተማ ገብተዋል። ጥቃቱ እንዴት እንደተፈጸመ የሰሜን ጎንደር ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አናግሯቸዋል። ካነጋገራቸዉ የፖሊስ አባላት መካከል ዋና ሳጅን ወልደሰንበት ካፊሶ እንዲህ ይላል። ምንም ይፈጠራል ብለን ባላሰብነዉና ባልጠበቅነዉ ሁኔታ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም 4፡15 ከ250 እስከ 300 የሚሆኑ የትግራይ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት በብሬንና … [Read more...] about ከወንበዴው ጥቃት ያመለጡ 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ደባርቅ ገብተዋል
የሶስቱ ቀናት ፈታኝ ተጋድሎ በብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም አንደበት
ዳንሻ ከተማ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ አምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር ካምፕ ጊቢ ውስጥ የመከላከያ መኪናዎች በጥይት ተበሳስተው ይታያሉ። መስታወታቸው ረግፏል፤ ዛፎቹም የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፤ መጥረቢያ እንጂ የጥይት ውርጅብኝ የቆረጣቸው አይመስሉም። የግንብና ቆርቆሮ ቤቶች እንደ ወንፊት ተበሳስተዋል። የጥይቶች ቀላሃ እንደ ጠጠር ተብትኗል። ዕለተ ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2013ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት አካባቢ በዳንሻ ከተማ ያልተጠበቀ፣ አሳዛኝ፣ አስደጋጭ ድርጊት ነው የተፈጸመው። በከተማዋ የሚገኘው የሰሜን ዕዝ የአምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር የተደገሰለትን ጥቃት አያውቅም። በመካናይዝድ ክፍለ ጦሩ ስታፍ ውስጥ የሚሰሩት መደበኛ ስራቸውን ከውነው እንቅልፍ ላይ ናቸው። በዚህ ምሽት ግን የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ወደ ካምፑ ዘለቁ፤ ብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም አድማሱን … [Read more...] about የሶስቱ ቀናት ፈታኝ ተጋድሎ በብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም አንደበት
ኦነግ ሸኔ ከበረኻ ወንበዴዎቹ ጋር በመሆን በውጊያው ላይ እየተሳተፈ መሆኑ ተገለፀ
በአገር መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ክልል ልዩ ሀይል ጥምረት በከሀዲው የህወሓት ጁንታ ላይ እየተወሰደ ባለው ህግ የማስከበር ስራ ላይ ኦነግ ሸኔ ከከሀዲው ቡድን ጋር በመሆን በውጊያው እየተሳተፈ መሆኑ ተገለጸ። ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት፤ በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ክህደት የፈጸመውና ለመናገር የሚከብድ ዘግናኝ ግፍ በፈጸመው የህወሓት ዘራፊ ቡድን ላይ እየተወሰደ ባለው ህግ የማስከበር ስራ ላይ የኦነግ ባንዲራን የያዙ የሸኔ አባላት በጦርነቱ እየተሳተፉ መሆናቸው ተረጋግጧል። ሀገሩንና ህዝቡን በማገልገል ላይ በለው ሰራዊት ላይ ከሀዲው ቡድን ከኦነግ ሸኔ ጋር አብሮ በውጊያው ላይ መሳተፉ እንዳስገረማቸውም ነው ሌተናል ጄኔራል ባጫ የገለጹት። የኦነግ ሸኔ አባላት በሁሉም ቦታዎች ላይ የሚታወቀውን የኦነግን ባንዲራ በመያዝ ከከሃዲው የህወሓት ቡድን … [Read more...] about ኦነግ ሸኔ ከበረኻ ወንበዴዎቹ ጋር በመሆን በውጊያው ላይ እየተሳተፈ መሆኑ ተገለፀ