በአገር መከላከያ ሰራዊትና በአማራ ክልል ልዩ ሀይል ጥምረት በከሀዲው የህወሓት ጁንታ ላይ እየተወሰደ ባለው ህግ የማስከበር ስራ ላይ ኦነግ ሸኔ ከከሀዲው ቡድን ጋር በመሆን በውጊያው እየተሳተፈ መሆኑ ተገለጸ።
ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት፤ በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ክህደት የፈጸመውና ለመናገር የሚከብድ ዘግናኝ ግፍ በፈጸመው የህወሓት ዘራፊ ቡድን ላይ እየተወሰደ ባለው ህግ የማስከበር ስራ ላይ የኦነግ ባንዲራን የያዙ የሸኔ አባላት በጦርነቱ እየተሳተፉ መሆናቸው ተረጋግጧል።
ሀገሩንና ህዝቡን በማገልገል ላይ በለው ሰራዊት ላይ ከሀዲው ቡድን ከኦነግ ሸኔ ጋር አብሮ በውጊያው ላይ መሳተፉ እንዳስገረማቸውም ነው ሌተናል ጄኔራል ባጫ የገለጹት።
የኦነግ ሸኔ አባላት በሁሉም ቦታዎች ላይ የሚታወቀውን የኦነግን ባንዲራ በመያዝ ከከሃዲው የህወሓት ቡድን ጋር በመሆን በሽራሮ፣ በራማ፣ በፆረና፣ እና በዛላንበሳ በኩል ውጊያ መግጠማቸውን ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ አስታውቀዋል።
ከሁለት አመት በፊት ጀምሮ በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች በንጹሀን ላይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶች ጀርባ ዘራፊው የህወሓት ቡድን እና ኦነግ ሸኔ እጃቸው አለበት ሲል መንግስት በተደጋጋሚ ማስታወቁ ይታወሳል። (ኢፕድ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply