ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ ከጥቅት ደቂቃዎች በፊት በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ይፋ እንዳደረጉት ምዕራባዊ የትግራይ ክልል ነጻ መውጣቱን ተናግረዋል፡፡
ሆኖም የበረሃ ወንበዴዎቹ ስብስብ በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ዘግናኝ ግፍ ነጻ በወጡ ከተሞች እየታየ እንደሆነ በመልዕክታቸው በመግለጽ “ሙት ይዞን እንዳይሞት” በማት ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል። መልዕክታቸው እንዲህ ይነበባል፤
“ለስግብግቡ ጁንታ ግፍ እስትንፋሱ፣ ጭካኔ ነፍሱ ነው። ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ሽራሮን ሲቆጣጠር፣ እጅና እግራቸውን የፊጥኝ ታሥረው የተረሸኑ የመከላከያ አባላትን አግኝቷል። ጭካኔው ልብ ሰባሪ ነበር። ዓላማው ኢትዮጵያን መስበር ነው። አላወቁም ከአልማዝ የጠነከረች መሆኗን። ዓላማው ሠራዊታችንንና ሕዝቡን አስቆጥቶ ለበቀል ርምጃ ማነሣሣት ነው። አላወቁም ልበ ሰፊ ሕዝብና ሠራዊት እንዳለን።
“በየቦታው ስንደርስ ከዚህ የከፋ ጭካኔና ግፍ ሊገጥመን ይችላል። ይህ ግን ለዚህ ጁንታ የመጨረሻው ነው። ጥንቃቄያችን ‘ሙት ይዞን እንዳይሞት’ ነው። መፍጠን አለብን፤ የተረፉትን ለመታደግና ግፍ የተፈጸመባቸውንም ለዓለም ለማጋለጥ።
“የምዕራቡን የትግራይ ክልል ቀጣና ነጻ ወጥቷል። በዚያ ቀጣና ሠራዊቱ ሰብአዊ ርዳታና አገልግሎት እየሰጠ ነው። ነጻ ባወጣቸው አካባቢዎች ሕዝቡን እየመገበ፣ እያከመና እየተከባከበ ነው”።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
tadesse gebregiorgis says
Tangible Report , Thank you
tadesse gebregiorgis says
THANK YOU