
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው።
ዛሬ የተሰበሰበው የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው በወንጀል የተጠረጠሩ የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።
በዚህም መሰረት፦
1. ደብረጸዮን ገብረሚካኤል
2. አስመላሽ ወልደሥላሴ
3. አባይ ፀሃዬ
4. አዲስ ዓለም ባሌማ (በቁጥጥር ሥር ውሏል)
5. ጌታቸው ረዳ
6. አፅበሃ አረጋዊ
7. ገብረ እግዚአብሄር አርአያ
እና ሌሎችም ላይ የቀረበው ያለመከሰስ መብት የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።
ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀሎችም ጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ፣ የሀገር መከላከያን በመውጋት እና በሌሎችም ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት ነው መሆኑ ታውቋል። (ኢፕድ)
ተጨማሪ
የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ 39 የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት የሆኑ የትግራይ ክልል ተወካዮች ያለመከሰስ መብታቸው እንደተነሳ መገለፁ ይታወቃል።
በምክር ቤቱ መቀመጫ ካላቸው 43 የሕውሃት ተወካዮች መካከል የ39 ያህሉ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የቀረበለትን ጥያቄ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል፡፡
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተወካዮቹ ፦
• ከፍ ያለ የሃገር ክህደት በመፈጸም ፣
• የጦር መሳሪያ ይዞ በመንቀሳቀስ፣
• በሽብር ጥቃት በመሳተፍ ፣
• የሃገር መከላከያ ሀይልን በመጉዳትና
በሌሎችም ወንጀሎች ጠርጥሯቸዋል ተብሏል፡፡
የጠቅላይ ዐቃቤ ህግን ጥያቄ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚ/ር ድኤታ አቶ ጫላ ለሚ እንዳሉት የምክር ቤቱ አባላት ወንበራቸውን ይዘው በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ ቢጠየቁም እንደ ፓርቲ ወስነው ከዚህ ወጥተዋል ብለዋል፡፡
በቅርቡ በመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈፀመውን ጥቃት የፈፀሙትም እንደ ፓርቲ ወስነው ስለሆነ ፓርቲው ተጠያቂ ነው ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው፡፡
ይሄ ማለት ግን ሁሉም የፓርቲው አባላት ተጠያቂ ይሆናሉ ማለት ሳይሆን ማስረጃና መረጃ የተገኘባቸው ብቻ ተለይው ሕግ ፊት እንደሚቀርቡ አስረድተዋል፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply