የዛሬውን የመቀሌ ውሎ አስመልክቶ ግርማይ ገብሩ እንደዘገበው በከተማዋ ያለው እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንደሆነ የጠቀሰ ሲሆን ባንኮች፣ መስሪያ ቤቶች እና ቴሌ ግን ዝግ ሆነው ነው የዋሉት። በሌላ በኩል አሸባሪው የበረኻ ወንበዴዎች ስብስብ የሆነው ህወሃት ሲመካበት የነበረው ነፍጥ ታጣቂ በሺህ የሚቆጠር እየሆነ ከነመሣሪያው እጁን በመስጠት ላይ ይገኛል። Eritrean Press በፌስቡክ ገጹ እንደዘገበው በርካታ ሺህ የሚሆኑ ልዩ ታጣቂዎች በጎንደር በኩል እጃቸውን እየሰጡ እንደሚገኙ ገልጿል። የነዋሪዎች መደበኛ ህይወት እንደወትሮው ሁሉ ሰላም ነው። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about መቀሌ በዛሬው ዕለት ሰላም ውላለች፤ የትግራይ ልዩ ኃይል እየከዳ ነው ተባለ
Archives for November 2020
በአሶሳ ከተማ ከአሸባሪው ህወሃት ጋር በመሆን በድብቅ ጥቃት ሊፈጽሙ የነበሩ 20 ግለሰቦች ተያዙ
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት ከህወሃት ጋር ድብቅ ግንኙነት በመፍጠር በአሶሳ ከተማ ጥፋት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ እንደሆኑ የተጠረጠሩ 20 ግለሰቦች ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱላዚዝ መሐመድ ተናገሩ። ኮሚሽነሩ ለኢዜአ እንዳሉት፤ግለሰቦቹ በአሶሳ ከተማ ኢንቨስትመንትን ሽፋን በማድረግ ጥፋት ለመፈጸም ከህወሃት ድብቅ ትልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው። ከዚህ ቀደም በክልሉ መተከል ዞን የተፈጸመውን ጥቃት ያስታወሱት ኮሚሽነሩ ግለሰቦቹ ይህንን ጥፋት ዳግም ማስቀጠል ዋነኛ ግባቸው … [Read more...] about በአሶሳ ከተማ ከአሸባሪው ህወሃት ጋር በመሆን በድብቅ ጥቃት ሊፈጽሙ የነበሩ 20 ግለሰቦች ተያዙ
ህወሓትና ተላላኪዎቹ በአሸባሪነት እንዲሰየሙ ተጠየቀ
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። ለአብነት ያህል፤ በአዲስ አበባ በሚኒባስ የፈነዳ ቦምብ በኦነግና በኤርትራ ላይ የተሳበበ መሆኑን የሚያስታውሱ ወገኖች ህወሓት ያኔ የፈጸመውን የአሸባሪነት ተግባር ላሁኑ እንደ ግብዓት ያነሳሉ። ሆኖም ቆየት ብሎ የታተመው የዊኪሊክስ (ሹልክ ዓምድ) ዘገባ ፍንዳታውን አቀነባብሮ ያከናወነው ህወሓት ስለመሆኑ እዚህ ላይ በዝርዝር አስረድቷል። ከበረሃ ጀምሮ ማሸበር ሙያው የሆነው ህወሓት ሥልጣን ይዞም ይህንኑ በደም የተነከረ … [Read more...] about ህወሓትና ተላላኪዎቹ በአሸባሪነት እንዲሰየሙ ተጠየቀ
ትህነግ የኤርትራን ወታደራዊ ዩኒፎርሞች አልሜዳ በማሰፋት ሻዕቢያ ወረርህ ለማስባል ተዘጋጅቷል
የትህነግን ትንኮሳ ቀልብሶ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ሥራ መጀመሩን ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ አስታወቁ። ትህነግ በትግራይ ክልል በሚገኘው የሀገር መከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ መንግሥት የማያዳግም ርምጃ በመውሰድ ላይ መሆኑን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ አስታወቁ። ይህንን ኃይል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ በሚደረገው ርምጃ ሕዝቡ ከመንግሥት ጎን ቆሞ ሊያግዝና አካባቢውን ነቅቶ ሊጠብቅ እንደሚገባም አሳስበዋል። አቶ ተመስገን ከተናገሩት የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፤ በየጊዜው የሸረሪት ድር ስናፀዳ አንኖርም፤ ትህነግ አልመዳ በሚባለው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ውስጥ የኤርትራ የመከላከያ ሰራዊት አልባሳትን በማምረት የኤርትራ ሰራዊት ወረረህ ለማለት ዝግጅት ያደረገ ነው፤ በአማራ ክልል በሶሮቃና ቅርቃር አካባቢ ትህነግ … [Read more...] about ትህነግ የኤርትራን ወታደራዊ ዩኒፎርሞች አልሜዳ በማሰፋት ሻዕቢያ ወረርህ ለማስባል ተዘጋጅቷል
ከኦነግ ሸኔ ጀርባ ህወሃት መሪውን የያዘው መሆኑ ታወቀ
“ከኦነግ ሸኔ ጀርባ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) መኖሩን የሚያሳዩ መረጃዎች በፖሊስ ተደርሶባቸዋል” ሲሉ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ገለጹ። ጀኔራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ የደረሰውን ጥቃት በተመለከተ ከትላንት በስቲያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው እንዳመለከቱት፤ “በህወሃት ስልጠና ተሰጥቷቸው በኦሮሚያ ክልል ሽብር እንዲፈጽሙ ከተላኩት መካከል የተያዙ ሰዎች እንዳሉ አረጋግጠናል” ብለዋል። ድምጸ ወያኔ ቲቪ እና ኦኤንኤን ቲቪ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ዘገባዎች በመስራት ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ሃይል ባለፉት ሁለት ዓመታት በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች የመንግስት ሰራተኞችን፣ አመራሮችን፣ ነጋዴወችን ጨምሮ በንጹ ዜጎች ላይ ግድያ ሲፈጽም መቆየቱን አስታውሰዋል። አሁንም … [Read more...] about ከኦነግ ሸኔ ጀርባ ህወሃት መሪውን የያዘው መሆኑ ታወቀ
ህወሃት በአማራ ክልል የሰነዘረው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ከሸፈ
በአማራ ክልል በሶሮቃና ቅርቃር አካባቢ ትህነግ ያደረገው የጦርነት ሙከራ በአማራ ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ መክሸፉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ። ርዕሰ መስተዳደሩ በመንግስት እየተወሰደ ያለውን እርምጃ አስመልከቶ በሰጡት መግለጫ ምሽቱን በሰሜን ዕዝ መከላከያ ካንፖችና የተለያዩ መሰረተ ልማት ያሉባቸው አካባቢዎች የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ የተቀናጀ ጥቃት ማድረሳቸውን ገልፀዋል። በአማራ ክልል በሶሮቃና ቅርቃር አካባቢ ትህነግ የጦርነት ሙከራ ማድረጉንና በአማራ ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ መክሸፉንም ነው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን የገለፁት። ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ለሚደረገው ርምጀ ህዝብ ከመንግስት ጎን ቆሞ ሊያግዝ ና አካባቢውን ሊጠብቅ እንደሚገባም አቶ ተመስገን ጥሪ … [Read more...] about ህወሃት በአማራ ክልል የሰነዘረው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ከሸፈ
ቀዩ መስመር ታልፏል
የሥራ አስፈጻሚው ከፍተኛው አካላት የሆኑት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅና ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ህወሃት ቀዩን መስመር ማለፉን አስታውቀዋል። ፕሬዚዳንት ሳህለ-ወርቅ ዘውዴ በምዕራብ ወለጋ ዞን በንጹሀን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት። “የሰማሁት አሰቃቂ ግድያ ልቤን በእጅጉ ሰብሮታል። ንጹሀን ዜጎች በሌሎች እብደት ውድ ሕይወታቸውን የሚከፍሉበት ንብረታቸው የሚወድምበት መሄጃ አጥተው የሚንከራተቱበት ምንም ምክንያት የለም። የዛሬ ዓመት በ30/10/2019 የጻፍኩትን ትዊት ልድገመው። “ዘርና ሀይማኖት ለፖለቲካ ጥቅም እንዲውሉ ሲደረግ፤ ንጹሀን ዜጎቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉና ሲንከራተቱ ስናይ ስሜትን ለመግለጽ ቃላት ያጥራል። ለቅሶ፣ ድንጋጤና ሥጋት የብዙዎችን በር አንኳኩቷል ሃዘናቸው ሃዘኔ/ሃዘናችን ነው። “ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም ሲባል … [Read more...] about ቀዩ መስመር ታልፏል
የትግራይን ሕዝብ ለ20 ሲጠብቅ በነበረው መከላከያ ሠራዊት ላይ ትህነግ ጦርነት ከፈተ
ሕወሓት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱ እና በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት መክፈቱ ተገለጸ። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አህመድ እንዳስታወቁት ህወሓት የሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል። ከቀናት በፊት ህወሐት የተባለው የበረኻ ወንበዴዎች ጥርቅም አባል የሆነው ስዩም መስፍን ከውጭ ኃይሎች ጋር ሆነን በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት እንሠነዝራለን ብሎ ሲናገር መደመጡ ይታወሳል። የወንበዴዎቹ መሪ የሆነው ደብረጽዮን ደግሞ ጦርነት እንጀምራለን፤ እንዋጋለን፤ እናሸንፋለን በማለት የትግራይ ሕዝብ ለዳግመኛ ዕልቂት እንዲዳረግ ጥሪ ሲያደርግ ተሰምቶ ነበር። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ይህ ሠራዊት ከሃያ ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የቆየ ሠራዊት ነው። በቦታው የሚገኘውም የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ነው። ሕወሐት ግን እንደ ባዕድና እንደ … [Read more...] about የትግራይን ሕዝብ ለ20 ሲጠብቅ በነበረው መከላከያ ሠራዊት ላይ ትህነግ ጦርነት ከፈተ