
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት ከህወሃት ጋር ድብቅ ግንኙነት በመፍጠር በአሶሳ ከተማ ጥፋት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ እንደሆኑ የተጠረጠሩ 20 ግለሰቦች ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱላዚዝ መሐመድ ተናገሩ።
ኮሚሽነሩ ለኢዜአ እንዳሉት፤ግለሰቦቹ በአሶሳ ከተማ ኢንቨስትመንትን ሽፋን በማድረግ ጥፋት ለመፈጸም ከህወሃት ድብቅ ትልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው።
ከዚህ ቀደም በክልሉ መተከል ዞን የተፈጸመውን ጥቃት ያስታወሱት ኮሚሽነሩ ግለሰቦቹ ይህንን ጥፋት ዳግም ማስቀጠል ዋነኛ ግባቸው እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ግለሰቦቹ “ከመስከረም 30፣2013 ዓ.ም. በኋላ መንግስት የለም” በሚል ከሃገር ውስጥ እና ከውጪ ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ ከሚሠራው የጥፋት ሃይል ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የፖሊስ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡
ግለሰቦቹ የአካባቢውን ወጣቶች በድብቅ በመመልመል ተጨማሪ ግጭት ለማስከተል ገንዘብ እና ሌሎችንም ሁኔታዎችን ሲያመቻቹ እንደነበር የሚያመላክት መረጃ ፖሊስ ማግኘቱን የፖሊስ ኮሚሽነሩ መናገረቸውን ሰምተናል።
በዚህም የክሉልን መንግስት ውጥረት ውስጥ በማስገባት ስልጣን ማስለቀቅና በአካባቢው ትርምስ እንዲፈጠር ማድረግ የግለሰቦቹ ፍላጎት እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
ኅብረተሰቡ መረጃ በመስጠት ትብብሩን እንዲያጠናክርም ጥሪ አቅርበዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply