
የትህነግን ትንኮሳ ቀልብሶ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ሥራ መጀመሩን ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ አስታወቁ።
ትህነግ በትግራይ ክልል በሚገኘው የሀገር መከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ መንግሥት የማያዳግም ርምጃ በመውሰድ ላይ መሆኑን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ አስታወቁ።
ይህንን ኃይል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ በሚደረገው ርምጃ ሕዝቡ ከመንግሥት ጎን ቆሞ ሊያግዝና አካባቢውን ነቅቶ ሊጠብቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።
አቶ ተመስገን ከተናገሩት የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፤
በየጊዜው የሸረሪት ድር ስናፀዳ አንኖርም፤ ትህነግ አልመዳ በሚባለው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ውስጥ የኤርትራ የመከላከያ ሰራዊት አልባሳትን በማምረት የኤርትራ ሰራዊት ወረረህ ለማለት ዝግጅት ያደረገ ነው፤
በአማራ ክልል በሶሮቃና ቅርቃር አካባቢ ትህነግ የጦርነት ሙከራ አድርጓል፤ ነገር ግን በአማራ ክልል ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ ተመክቶ ተመልሷል።
ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ለሚደረገው ርምጀ ህዝቡ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ከመንግስት ጎን ቆመው ሊያግዙና አካባቢያቸውን ሊጠብቁ ይገባል በማለት አቶ ተመሥገን ጥሩነህ ማሳሰባቸውን አብመድ ዘግቧል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply