
በአማራ ክልል በሶሮቃና ቅርቃር አካባቢ ትህነግ ያደረገው የጦርነት ሙከራ በአማራ ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ መክሸፉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።
ርዕሰ መስተዳደሩ በመንግስት እየተወሰደ ያለውን እርምጃ አስመልከቶ በሰጡት መግለጫ ምሽቱን በሰሜን ዕዝ መከላከያ ካንፖችና የተለያዩ መሰረተ ልማት ያሉባቸው አካባቢዎች የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ የተቀናጀ ጥቃት ማድረሳቸውን ገልፀዋል።
በአማራ ክልል በሶሮቃና ቅርቃር አካባቢ ትህነግ የጦርነት ሙከራ ማድረጉንና በአማራ ልዩ ኃይል ሙሉ በሙሉ መክሸፉንም ነው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን የገለፁት።
ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ለሚደረገው ርምጀ ህዝብ ከመንግስት ጎን ቆሞ ሊያግዝ ና አካባቢውን ሊጠብቅ እንደሚገባም አቶ ተመስገን ጥሪ አቅርበዋል።
ክልሉም ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በቅንጅት እየሠራ እንደሆነም ገልፀዋል። (ፎቶ፤ ከጦርነቱ ያልተገናኘ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply