• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የትግራይን ሕዝብ ለ20 ሲጠብቅ በነበረው መከላከያ ሠራዊት ላይ ትህነግ ጦርነት ከፈተ

November 3, 2020 11:44 pm by Editor Leave a Comment

ሕወሓት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱ እና በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት መክፈቱ ተገለጸ። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አህመድ እንዳስታወቁት ህወሓት የሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል።

ከቀናት በፊት ህወሐት የተባለው የበረኻ ወንበዴዎች ጥርቅም አባል የሆነው ስዩም መስፍን ከውጭ ኃይሎች ጋር ሆነን በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት እንሠነዝራለን ብሎ ሲናገር መደመጡ ይታወሳል።

የወንበዴዎቹ መሪ የሆነው ደብረጽዮን ደግሞ ጦርነት እንጀምራለን፤ እንዋጋለን፤ እናሸንፋለን በማለት የትግራይ ሕዝብ ለዳግመኛ ዕልቂት እንዲዳረግ ጥሪ ሲያደርግ ተሰምቶ ነበር።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ይህ ሠራዊት ከሃያ ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የቆየ ሠራዊት ነው። በቦታው የሚገኘውም የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ነው። ሕወሐት ግን እንደ ባዕድና እንደ ወራሪ ሀገር ሠራዊት ቆጥሮ፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምታትና ለመዝረፍ ተነሥቷል።

ህወሓት በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት ከፍቷል።

መንግሥት የትግራይ ሕዝብ እንዳይጎዳ በማሰብ፣ ጦርነት እንዳይፈጠር የትእግሥቱ ጫፍ ድረስ ታግሷል ያሉት ዶ/ር አብይ፤ ጦርነት የሚቀረው ግን በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም ነው ያለት።

“የመከላከያ ሠራዊታችን በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል። ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ነገሮችን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል፣ በየአካባቢው ሊከሠቱ የሚችሉ ትንኮሳዎች  በንቃት እንዲቃኝና ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገጻቸው ያወጡት መግለጫ ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል፤

“ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው የመከላከ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል። ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ ሙከራ አድርጓል። ይህ ሠራዊት ከሃያ ዓመታት በላይ የትግራይን ሕዝብ ሲጠብቅ የቆየ ሠራዊት ነው። በቦታው የሚገኘውም የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከል ነው። ሕወሐት ግን እንደ ባዕድና እንደ ወራሪ ሀገር ሠራዊት ቆጥሮ፣ የመከላከያ ሠራዊቱን ለመምታትና ለመዝረፍ ተነሥቷል። በዳልሻሕ በኩልም ጦርነት ከፍቷል።

“መንግሥት የትግራይ ሕዝብ እንዳይጎዳ በማሰብ፣ ጦርነት እንዳይፈጠር የትእግሥቱ ጫፍ ድረስ ታግሷል። ጦርነት የሚቀረው ግን በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም።

“የመከላከያ ሠራዊታችን በኮማንድ ፖስት እየተመራ ሀገሩን የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶታል።  ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል። ሀገርና ሕዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል።

“የኢትዮጵያ ሕዝብ ነገሮችን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል፣ በየአካባቢው ሊከሠቱ የሚችሉ ትንኮሳዎች  በንቃት እንዲቃኝና ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀርባለሁ።”

በቀጣይ ሊነጋ አካባቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቀጥታ ስርጭት ይህን መልዕክት አስተላፈዋል፤

ውድ የሀገሬ ህዝብ ሆይ ዛሬ ከሃዲ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን ወግተዋል።

ኢትዮጵያ በጎረሰ እጇ ባጠባ እጇ ተነክሳለች።

ላለፉት 20 ዓመታት የቀበሮ ምሽግ ውስጥ በመሆን ሀገሬን ወገኔን ህዝቤን ብሎ በብዙ ሺዎች መስዋዕትነት ከፍሎ ቆስሎ ደምቶ ሀገሩንና ህዝቡን የታደገው የመከላከያ ሰረዊት ላይ ዛሬ ምሽት ከመቀሌ ጀምሮ በበርካታ ስፍራዎች በካሃዲው ኃይሎች እና ባደረጁት ኃይል ጥቃት ተፈፅሞበታል።

ይህ ጥቃት በሀገራችን እስካሁን ከደረሱት ጥቃቶች እጅግ አሰፋሪ የሚያደርገው የሀገረ መከላከያ ሰራዊት ሰላም ለማስከበር በተለያዩ ሀገራት በተሰማራበት ሀገር በውጭ ኃይል  እንኳ አጋጥሞት በማያውቀው ሁኔታ በገዛ ወገኑ ከጀርባው  ጥቃት ተፈፀሞበታል።

በዳንሻ በኩል በአማራ ክልል ላይ የፈፀሙት ጥቃት በአማራ ክልል በነበረው ኃይል ተመክቷል።

የትግራይ ሕዝብ ወገናችን ነው ለጥቂት እኩዮች ሲባል ምንም እንኳ የእኩዮች መሸሸጊያ ዋሻ ቢሆንም ሕዝባችን ላይ ጥቃት አንሰነዝርም ብሎ በትዕግስት በቆየው ሰራዊት ላይ ጥቃት ተፈፅሞበታል።

በመላ ሀገራችን ቀድመው ባሰለጠኑት ባሰማሩት ባዘጋጁት ኃይል በተለያየ ቦታ በተለያየ ከተማ በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ሊፈፅሙ ስለሚችል መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚሊሻው ከፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም በአካባቢያቸው ከሚገኝ የመከለከያ ሰራዊት ጋር በመተባበር ቀያችሁን ሰፈራችሁን እንድትጠብቁ አሳስባለሁ።

የመከላከያ ሰራዊት ከጠቅላይ ሰፍር በሚሰጥ ትዕዛዝ መለዮውን ሀገሩንና ህዝቡን እንዲከላከል ለሚከፍለው መስዋዕትነት ዛሬም እንደተለመደው በታሪኩ ውስጥ የሚታሰብ መሆኑን እገልፃለሁ።

ይህ እኩይ ኃይል መጥፊያው በመድረሱ በሰላም በንግግር በውይይት ሊፈቱ የሚችሉ ነገሮችን ባለፉት ጥቂት ቀናት ካለምንም ሀፍረት በሚዲያ በመውጣት ከየትኛውም የውጭ ኃይል ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን እወጋለሁ ብሎ ሲያውጅ የነበረው ኃይል  ይህን ለማመን የሚያስቸግር ንግግር በተግባር ማዋሉን በዚህ ምሽት አረጋግጧል።

የትግራይ ህዝብ ወገኔ ዘመዴ ሕዝቤ ብሎ ላለፉት 20 ዓመታት በቀበሮ ምሽግ ውስጥ በመሆኑ በብዙሺዎች የሚቆጠር መስዋዕትነት የከፈለውን አንተን ለመጠበቅ አስፈላጊውን ሁሉ ያደረገው የመከላከያ ሰራዊት የደረሰበት ጥቃት ጥቃትህ መሆኑን በመገንዘብ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ሀገርህን ከነዚህ ከሃዲ ኃይሎች እንድትከላከልና በንቃት እንድትጠብቅ  አሳስባለሁ።

ይህ ጉዳይ ለኢትዮጵያ አሳዘኝ አሳፈሪም ተግባር ቢሆንም ዛሬም እንደተለመደው በተደመረ በተባበረ ክንድ ይህንን ከሃዲ ጡት ነካሽ ኃይል ለማሳፈርና ለመደምሰስ እስፈላጊውን ሁሉ የምናደርግ መሆኑን እገልፃለሁ።

ይህ አሳፈሪ ተግባር በማይደገምበት ሁኔታ የሚቀለበስበትን ተግባር መላው የኢትዮጵያ ህዝብና የሀገር መከላከያ ሰራዊት  በመተባበር የሚፈፅሙት ይሆናል።

ለመላው የሀገራችን ህዝቦች አስፈላጊውን መረጃ በየጊዜው በሚመለከታቸው የመንግስት አከላት የሚሰጥ መሆኑን እገልፃለሁ።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Right Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule