• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሶስቱ ቀናት ፈታኝ ተጋድሎ በብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም አንደበት

November 12, 2020 01:30 am by Editor 2 Comments

ዳንሻ ከተማ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ አምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር ካምፕ ጊቢ ውስጥ የመከላከያ መኪናዎች በጥይት ተበሳስተው ይታያሉ። መስታወታቸው ረግፏል፤ ዛፎቹም የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል፤ መጥረቢያ እንጂ የጥይት ውርጅብኝ የቆረጣቸው አይመስሉም። የግንብና ቆርቆሮ ቤቶች እንደ ወንፊት ተበሳስተዋል። የጥይቶች ቀላሃ እንደ ጠጠር ተብትኗል።

ዕለተ ማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2013ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት አካባቢ በዳንሻ ከተማ ያልተጠበቀ፣ አሳዛኝ፣ አስደጋጭ ድርጊት ነው የተፈጸመው። በከተማዋ የሚገኘው የሰሜን ዕዝ የአምስተኛ መካናይዝድ ክፍለ ጦር የተደገሰለትን ጥቃት አያውቅም። በመካናይዝድ ክፍለ ጦሩ ስታፍ ውስጥ የሚሰሩት መደበኛ ስራቸውን ከውነው እንቅልፍ ላይ ናቸው።

በዚህ ምሽት ግን የትግራይ ልዩ ኃይል አባላት ወደ ካምፑ ዘለቁ፤ ብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም አድማሱን እንደሚፈልጉትና እንዲጠራላችሁ የበር ጥበቃዎችን ይጠይቃሉ።

ጀኔራሉም እንደማይመጡ ሲነገራቸው ተመልሰው ይሄዱና ተጨማሪ ኃይል ይዘው መጥተው በካምፑ ላይ የጥይት መአት ማውረድ ይጀምራሉ። ውስጥ የነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላትም በጽናት የመመከት ስራ ውስጥ ገቡ፤ ለሶስት ቀንና ሌሊት በጽናት ታገሉ።

አንድ የመከላከያ ሠራዊት የመረጃ ሰራተኛ ወደ ጀነራሉ ጆሮ ተጠግቶ አካባቢውን የትግራይ ልዩ ሀይሎች ከቦታል። ፍላጎት ካለህ ሽማግሌዎቹ ከአካባቢው እናስወጣው ብለው ነግረውኛል፤ ውሳኔህ ምንድነው ሲል ጠየቀኝ ያሉት ብርጋዴር ጀነራሉ፣ የእነሱ ፍላጎት እኔም ወኔዬን ተሰልቤ የሲቪል ልብስ ለብሼ ተደብቄ ወደ አማራ ክልል እንድወጣ፤ አልያም እኔን አታለው እንድያዝ በማድረግ ካምፕ ውስጥና በአቅራቢያው ባለው የመከላከያ ሠራዊት ላይ ለመሰንዘር ያቀዱትን ጥቃት የመከላከልና የመመከት ስራ ለማሰናከል ነው።

በዚህም በቀላሉ ሰራዊቱንና መሳሪያውን በቁጥጥር ስር ለማዋል አስበው መሆኑን ገለጹልን።

እኔም ምላሼ ሽምግልናውን አለመቀበል ብቻ ሳይሆን የመረጃ ሰራተኛው ከሽማግሌዎቹ ጋር ለጥሩም ይሁን ለመጥፎ መገናኘት እንደሌለበት አስጠንቅቄ ነገርኩት። አሁን ይህን ያለኝ ልጅ ቆስሎ ለህክምና ወደ ጎንደር ሄዷል። ሲመጣ ጠይቄ ዓላማቸው ምን እንደነበር የምረዳው ይሆናል። ተመትቶ ስለነበረ እኔም እንዳልሞት አስቦ ይሆናል የሚል ግምት አለኝ ብለውናል።

የሶስት ቀን ከበባው በጣም አስቸጋሪ ነበር። 24 ሰዓት ተኩስ ነው። ያጠቃሉ እኛ እንከላከላለን፤ ይሄዱና ምግብ በልተው ኃይል ጨምረው ያጠቃሉ፤ ሲታኮሱ የነበሩት ልዩ ሀይሎች ወደ ካምፓቸው ሄደው አርፈውና ጥይት ጭነው ይመጣሉ። እኛ ካለንበት ቦታ ውጭ መፈናፈኛ ስፍራ የለንም።

እንደ ቀለበት ዙሪያውን ከበውና ውሃ፣ ምግብ፣ ጥይት የለም። ያለችንን ነው በቁጠባ የምንጠቀመው ሲሉ ያብራሩት ጀነራሉ፣ እኔም አልፎ አልፎ እንደ ምሽግ ከተጠቀምኩበት ግንብ ቤት እየወጣሁ ለወታደሮቼ ጥይት በቁጠባ ተጠቀሙ እያልኩ አሳስብ ነበር ሲሉ ይገልጻሉ። እነሱም አላሳፈሩኝም በጽናት ተዋደቁ።

የሰራዊታችን በጽናት የመከላከል ሞራል የሚገርም፣ የሚደነቅና ታምር የሚያስብል ነው ይላሉ።

አርፒጂ፣ ቦንብ፣ መትረየስ፣ ክላሽ እንደ ዝናብ ቢያርከፈክፉብንም ለሶስት ቀናት ቀንና ሌሊት መክተናል።በፍጹም እንተርፋለን ብለን አላሰብነም፤ ከቻልን እስከ መጨረሻው እንከላከላለን፤ ካልቻልን ደግሞ በመጨረሻ ላይ ራሳችንን እናጠፋለን የሚል አቋም ነበርን።

ግን በእግዚአብሔር ቸርነት፤ በመከላከያ ሠራዊት ፈጥኖ ደራሽነት ቀለበቱ ተሰብሮ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግረናል ብለውናል ብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም።

ድርጊቱ የሚያሳዝን ነው፤ በህወሓት ከሀዲ ቡድን እንዲህ አይነት ጥቃት ይፈጸምብናል ብለን አስበን፤አልመንም አናውቅም የሚሉት በሰሜን ዕዝ የአምስተኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሙሉዓለም አድማሱ፤ ምክንያቱም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጀምሮ እዚሁ ነው እየኖርን ያለው። ህዝቡን መሪዎቹንም በደንብ እናውቃቸዋለን ብለዋል።

“አብረህ እየበላህ እየጠጣህ፣ ተዋልደህ ተጋምደህ፤ ትዳር መስርተህ፣ ልጆች ወልደህ፤ ቤተሰብ ሆነህ በፍጹም ጥቃት ሊሰነዝሩብኝ ይችላሉ ብለህ አታስብም፤ ሆኖም ያልታሰበው ተፈጸመ፤ ያልተጠበቀው ሆነ” ሲሉ በትግራይ ክልል ልዩ ኃይል የተሰነዘረባቸውን ጥቃት አሳዛኝ ሲሉ ይገልጹታል።

ኩርፊያና የተለያዩ መገለጫዎች ይታያሉ። ይህን ተከትሎ ጥርጣሬዎች ቢኖሩም ደፍረው መከላከያ ሠራዊት ካምፕ ውስጥ ገብተው ያጠቃሉ ብለን አላሰብንም።

ምክንያቱም ወንድምህ ሊያኮርፍ ይችላል እንጂ ያጠቃኛል፤ ይገለኛል ብለህ ፈጸሞ አትገምትም። የሚሉት ብርጋዴር ጀኔራሉ፤ ግን የትግራይ ልዩ ሀይሎች ዕለተ ማክሰኞ 25ቀን 2013ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ያለምንም ርህራሄ ዙሪያውን እንደ ቀለበት ከበውን አጠቁን፣ አጠቁን እኛም በጽናት ተከላከልን፤ መከትን ብለዋል።

የህወሓት ቡድን ዓላማ የመከላከያ ሠራዊትን መድፎች፣ ታንኮች፣ ብረት ለበሶችን መንጠቅና መከላከያን ማፍረስ ነው። በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ በራሳችን መሳሪያ ተመልሰው እኛን ለመውጋት ነበር ዕቅዳቸው። ይህ አልተሳካላቸውም። እኛም በያለንበት በጽናት ተዋግተን መክተናል።

አሁን እነሱ ባሰቡት ሳይሆን እኛ ባሰብነው መንገድ እየሄደ ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ ጦርነቱ ይቋጫል ብለን እናስባለን ሲሉ ገልጸውልናል።

ብርጋዴር ጀኔራል ሙሉዓለም አንድ የሚገርማቸው የሚደንቃቸው ነገር አለ። “እኔ አንድ ተራ ኢትዮጵያዊና ተራ ጄነራል ነኝ፣ በአንድ ክላሽ ጥይት ግፋ ቢል ደግሞ በስናይፐር መግደል ይችላሉ፤ ግን የጭካኔያቸው ጭካኔ አርፒጂ ነው የተኮሱብን”።

አርፒጂ የሚባለው መሳሪያ ደግሞ ለታንክ ወይም ለጠንካራ ምሽግ ነው የሚተኮሰው፤ የእኔን ቤት ለማፍረስ ግን አርፒጂ ነው የተኮሱት ሲሉ የከሀዲው ቡድን የጭካኔ ጥግ ምን ያህል እንደሆነ ይናገራሉ ።

እኔ ብሞትም ቤቱ የእነሱና የህዝቡ ንብረት ነው። ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ጸጥታ ለቆምኩ፣ ለአገር ሉዓላዊነትና ለህዝብ ሰላም ውድ ህይወቴን ለመስጠት በተሰለፍኩ የክህደታቸው፣ የክፋታቸው ጥልቀት እኔን በአርፒጂና በቦንብ ነው ያጠቁት ሲሉ የድርጊቱን ክፋት ገልጸውታል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ህዝብ ጋር አብሮ እየኖረ ያለ፣ ለህዝቡ የልማት ሥራዎች ወደ ኋላ የማይል፣ በማህበራዊ ድጋፎች የሚሳተፍ፣ ሁልጊዜ በየዓመቱ ለአቅመ ደካሞች የሚያርስ፣ የሚያርም፣ የሚያጭድና አንበጣ የሚከላከል ነው። 

በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ጣቢያዎች፣ በመንገድ ግንባታዎች በሚሳተፍ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈጸም የህወሓት ቡድን እወክለዋለሁ ቆሜለታለሁ ለሚለው ህዝብ ደንታ እንደሌለው ያሳያል ይላሉ።

የአገሩን ዳር ድንበር የሚጠብቀውን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስብስብ የሆነውን የመከላከያ ሠራዊት ለማውድምና ለማጥፋት ነው ጥቃቱን የሰነዘሩት። እነዚህ ሰዎች ከዚህ በኋላ ስለኢትዮጵያዊነት፣ስለብሄረሰቦችና ባጠቃላይ ስለኢትዮጵያውያን ቢሰብኩ፣ ቢለፈልፉ፣ ቢቀሰቅሱ ማን ጀሮ ይሰጣቸዋል።ምክንያቱም ጥቃቱን በጽናት ለመመከት የተዋደቁት ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተወጣጡ ወታደሮች ናቸው ብለዋል።

ጀኔራሉ በ1980ዓ.ም በወቅቱ ኢህዲን ተብሎ የሚጠራውን ትግል የተቀላቀሉ ናቸው። ከዚሁ ዓመት ጀምሮ ደርግ እስኪደመሰስ ድረስ በተደረጉ ውጊያዎች ተሳትፈዋል። ቆቦ አካባቢ በተካሄደው ሰላም በትግል ኦፕሬሽን፤ ሰሜን ሸዋ መራኛ፣ ጁሁርና መራቤቴ አውድ ውጊያዎች ተሳትፈዋል።

በጎጃም ደጀን፣ አምቦ፣ ነቀምት፣ ጅማ፣ ቡሌሆራ (አገረ ማርያም) ሞያሌ ድረስ በዘለቀው አውድ ውጊያ ተሳትፈዋል። በሀረርም ጸረ ሰላም ሀይሎችን በመከላከልና በማጥቃት ዘመቻ ተሳትፈዋል። በሩዋንዳ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ በ1986ዓ.ም ግድጃቸውን በስኬት አጠናቀው ተመልሰዋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሲቋቋምም 20ኛ ክፍለ ጦር መድፈኛ ብርጌድ አንደኛ ሻለቃ አዛዥ ሆነው አገልግለዋል። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም ትምህርታቸውን አቋርጠው በመሄድ ብርጌድ አዛዥ በመሆን በጾረና፣ በባድመ፣ በሽራሮ አዲኋላ ግንባር ተሳትፈዋል።

አሁንም በዳንሻ ከተማ በትግራይ ልዩ ኃይል የተካሄደውን ከበባና ሶስት ቀናት የዘለቀ ጥቃት ወስን ወታደሮችን መርተውና አዋግተው በተጨማሪ የመከላከያ ሠራዊት ዕገዛ መከላከሉን በድል አጠናቀው የማጥቃቱን ተልዕኮ በድል እየተወጡ ይገኛሉ። ©ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተወሰደ

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, Politics

Reader Interactions

Comments

  1. TAYE says

    November 12, 2020 05:19 am at 5:19 am

    I AM PROUD OF B. GENERAL MULUALEM HE MAKE HISTORY !!!! BUT EVEN IF THE WAR WILL OVER THERE IS TPLF TERRORIST ALL THROUGH ETHIOPIAN REGIONS WAITING TO CREATE CIVIL WAR.
    TO MINIMIZE DEATH RATE GOVERNMENT MUST HAVE SEARCH ALL BALK LIST HOMES OUT OF HIDDEN,OPERATION THAT ORGANIZED BY THIS TPLF TERRORIST GROUPS.
    FOREVER VICTORY TO ETHIOPIA DEATH TO HER ENEMY

    Reply
  2. Abraham says

    November 13, 2020 03:58 pm at 3:58 pm

    I salute you my guy , you are my hero and your country is proud of you love you from my soul

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule