• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የትግራይ ተወላጅ የፖሊስ አባላት አፈሙዝ ወደ እኛ በማዞር የፈጸሙብን ክህደት በጣም አሳዝኖናል”

November 17, 2020 02:41 am by Editor Leave a Comment

በትግራይ ክልል መቀሌ ሀራ ገበያ ዓዲ ጉደም ምድር ባቡር ፕሮጀክት በሚጠብቁት ላይ ከተፈጸመ ጥቃት የተረፉት ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት አዲስ አበባ ከተማ ገብተዋል።

የህዝብና መንግስት መሰረተ ልማቶችን በመጠበቅ ከ10 ዓመታት በላይ መቆየታቸውን የገለጸው ዋና ሳጅን ድረስ ስንሻው የተለመደዉን መደበኛ የጥበቃ ስራችን እያከናወን በነበርንበት ወቅት በፕሮጀክቱ ባሉ ሳይቶች ላይ የነበሩ የስራ ባልደረቦቻችንን ትጥቅ በማስፈታት፣ አፍነውና እጃቸውን በካቴና አስረው ወደ መቀሌ ሲወስዷቸው እጃችንን ከምንሰጥ ብለን ወደ ጫካ በመግባት ለሚተኮስብን ተኩስ ምላሽ በመስጠት ለማምለጥ ችለናል ብለዋል።

እኛ ለአንድ ብሔር የቆምን ሳይሆን ከሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ የተውጣጣንና ሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድነት ስንጠብቅ የኖርን በመሆኑ እንደዚህ አይነት የሀገር ክህደት ይፈጸምብናል ብለን አልጠበቅንም ነበር በማለት ገልጸዋል።

የታፈኑ አባሎቻችንን ለማስለቀቅ ብንሞክርም ከአቅማችን በላይ በመሆናቸውና እኛንም ለማስቀረት ከፍተኛ የሆነ ተኩስ ስለ ከፈቱብን ለጽንፈኛው ቡደኑ እጅ ከምንሰጥ በማለት ለሶስት ቀናት የሚበላና የሚጠጣ ባልነበረበት በበረሃ ጫካ ለጫካ እየተጓዘን አፋር ክልል ስንደርስ አባላ የሚባል አካባቢ የክልሉ ህዝብ ተቀብሎን ወደ መስመር አወጣን ሲሉ ተናግረዋል።

የህወሓት ጽንፈኛ ቡድኑ በእኛ በፌደራል ፖሊስ አባላትና በሀገር መከላከያ ሰራዊት የፈጸመው አረመናዊ ድርጊት በጣም አሳዝኖናል፣ በተለይ ከ10 ዓመታት በላይ አብሮን የሰሩና የኖሩ የትግራይ ተወላጅ የፖሊስ አባላት ወደ ክልሉ ልዩ ሀይል በመቀላቀል አፈሙዝ ወደ እኛ በማዞር የፈጸሙብን ክህደት በጣም አሳዝኖናል፣ አስከፍቶናልም ብለዋል።

ከዚህ ቀደም አባት አርበኞች ከፍተኛ መስዋትነት ከፍለው ኢትዮጵያን እንዳስረከቡን ሁሉ ዛሬም በርካታ የሀገር ተቆርቋሪ የሆኑ ጓዶች ስላሉን ሀገራችን ለማዳን እየተከናወኑ ያሉ የህግ ማስከበር ስራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ እስከ መጨረሻ ከህዝብ ጋር በመቆም ለዚህ አስነዋሪ ድርጊት የተሰለፉትን የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን ለህግ ለማቅረብ ለሚደረገው ርብርብ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ሌላኛዉ የሰሜን ዲቪዥን፣ ሶስት፣ ሻለቃ 4፣ ሻምበል 1 አባል ኮንስታብል ድረስ ንጉሴ እኛ ሰላም ነው ብለን በተቀመጥንበትና ባላሰብነው ሰዓት የክልሉ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ተደራጅተው በመምጣት አንድ ዳቦ ለሁለት በመካፈል አብረውን ሲበሉ ከነበሩ ከትግራይ ተወላጅ የስራ ባልደረቦቻችን ጋር በመሆን ጥቃት ቢፈጽሙብንም የአፋር ህዝብ ላደረገልን አቀባበልና ድጋፍ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

እኛ የትግራይ ህዝብን ከወንጀል በመከላከልና በክልሉ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ማህበራዊ እንቅስቃሴ ስናግዝና ስንተባበር ነው የቆየነው፣ የትግራይ ህዝብ ይህንን ጽንፈኛ ቡድን በማጋለጥ ነጻነቱን ሊያረጋግጥ ይገባልም ብሏል። (ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ፌስቡክ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule