በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸውን የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች እንዲታገዱ መወሰኑን ፌዴራል ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎቹ በቀጠሯቸው የጥበቃ አባላትና ተባባሪዎቻቸው ባንኮችንና የተለያዩ ድርጅቶችን ሲዘርፉ እና ሲያዘርፉ ነበርም ብሏል።
በተጨማሪም ‘የህወሓትን ተልዕኮ ለመፈፀም የተለያዩ ግለሰቦችን ወደ ኤጀንሲዎቹ አስርገው በማስገባት እና የጦር መሣሪያ በማስታጠቅ በኅብረተሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እያሴሩ ነበር’ ሲል አስታውቋል።
በዚህም:-
1. ንስር የሰው ሃይል እና የጥበቃ አገ/ሃ/የተ/የግ/ማ
2. አጋር የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
3. ስብኃቱና ልጆቹ የንብረት አስ/ጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
4. ሰላም ሴኩሪቲ ሶሉሽን ኃ/የተ/የግ/ማ
5. ኃይሌ ተክላይ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ስ/ማ
6. ክፍሌ ጎሳዬ ሃጎስ እና ወ/ገብርኤል የጥበቃ አገልግሎት ሽርክና /ማ
7. ዮናስ፣ ሮዛ እና መብርሂት የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሽ/ማ
8. ሃየሎም እና ብርሃኔ የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ
9. ደመላሽ፣ ሃፍቱ እና ጓደኞቻቸው የጥበቃ አገልግሎት ህ/ሸ/ማ
10. ህሉፍና ሃለፎም የጥበቃ አገ/ህ/ሽ/ማ
11. ዋልታ የጥበቃ የሰው ኃይልና ኮሚሽን ኃ/የተ/የግ/ማ
12. ሴፍ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
13. አትላስ ጠቅላላ አገ/ኃ/የተ/የግ/ማ
14. ጎህ የጥበቃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማ
ለሀገር እና ለዜጎች ሰላም እና ደህንነት ሲባል ስማቸው የተገለጸው የጥበቃ ተቋማት በአስቸኳይ ሥራቸውን አቁመው ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሪፖርት እንዲያደርጉም አሳውቋል። (EBC)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply