ትላንት (May 15) በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አበጥር ወርቁ በተባለ የአማራ ብሔር ተወላጅ ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ግፍ ተመልክተናል፡፡ ይህ ከመሆኑ ከአንድ በፊት ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ527 በላይ አባወራዎች በድምሩ 2000 ከሚሆኑ ቤተሰቦቻቸው ተፈናቅለዋል፡፡ እነዚህ “ሕገ ወጥ ናችሁ” በሚል ሰበብ ተዘርፈውና ተደብድበው የተፈባቀሉት አማራዎች ህጋዊ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ያላቸው ናቸው፡፡ በባለቤትነት ለሚያስተዳድሩት መሬት በአግባቡ ግብር ይከፍላሉ! በፎቶው የሚታዩት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተሮች ባህርዳር ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን ተጠልለው የሚገኙ ሶስት አባውራዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች ያለ ምንም መነሻ ምክንያት ከመሬታቸው አልተፈናቀሉም፣ በግፍ አልተገደሉም፡፡ ከዚህ በስተጀርባ በጥላቻና ማንአለብኝነት የናወዙ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የመንግስት … [Read more...] about አማራ የሚፈናቀለው ሆነ የሚገደለው በመንግስት ፍቃድ ነው!
Opinions
የኔ ሃሳብ
የጠ/ሚ/ር አብይን የለውጥ መንገድ ለመርዳት ምን ማድረግ ያስፈልጋል?
የሚፈለገው ለውጥ ዋናው ዓላማ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈለገውን አስተዳዳሪዎቹንና የአስተዳደር ሥርዓትን በነፃነትና በዴሞክራሲ መንገድ ሊመርጥ የሚችልበትን ሥርዓት መመሥረት ነው። ህወሃት የዘረፋ ሥርዓቱን ለማቀላጠፍ እንዲመቸው ዘንድ ኢ-ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መመሪያ በማድረግ ፖለቲካውን የማጭበርበሪያ፣ ኢኮኖሚውን የመዝረፊያ፤ ዳኝነትን የመበቀያ፣ ደህነነትን የማሸበሪያና መከላከያን የማጥቂያ መዋቅሮች አድርጎ ለሃያ ሰባት አመት በኢትዮጵያ ሕዝብና በአገር ላይ ከባድ ግፍና መከራ እየፈፀመ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የመጀመሪያ ዋና ጥያቄ ይህንን ሕዝቡንና አገሪቷን ከላይ እስከ ታች በኢ-አብዮታዊ ዴሞክራሲና በኢ-ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት በመጠፍነግ ለጥቂቶች ገነት ለአብዛኛው ሕዝብ ግን መከራና ስቃይ የሆነውን ሥርዓት በሰላማዊ መንገድ መለወጥ ነው። ዶ/ር አብይ ከሚናገሩትም ሆነ ከገዱ ቡድንና … [Read more...] about የጠ/ሚ/ር አብይን የለውጥ መንገድ ለመርዳት ምን ማድረግ ያስፈልጋል?
ዘራፊዎችን ለማጋለጥ ሁሉም ይተባበር!!
በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል፥ ሰቆቃ፥ ስደታና ሞት ቀጥሎሏል። በአንድአማራ ጽኑ እምነት አሁን ካለው የባሰና የከፋ ከመምጣቱ በፊት ጠላት በመቀነስ ላይ ያተኮረ ትግል መደረጉ ተገቢ ነው በሚል ሙሉ እምነት ይዘን ዘረኛውና እብሪተኛው የትግራይ ጽንፈኛ ቡድን ላይ በማነጣጠር ትግላችንን አጠናክረን ይዘን እንገኛለን። ይህ ጽንፈኛ ተገንጣይ የትግራይ ወያኔ ቡድን አማራውን በግንባር ቀድምትነት ጠላት አድርጎ በመፈረጅ በተመቸው አጋጣሚ ሁሉ በደል እየፈጸመ ይገኛል። በቅርቡ የተቀየሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም የአማራውን ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄና የመኖር ህልውና በማረጋገጥ ረገድ እየሰሩ አለመሆናቸዉን ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው። ምንም እንኳን ጠ/ሚ አብይ አማራው የሚፈልገውን ጥያቄ ለመመለስ ባይችሉም በሚያደርጓቸው ትግሎች ላይ የጋራ ጠላታችንን የሚያነጣጥር ከሆነ አብረን … [Read more...] about ዘራፊዎችን ለማጋለጥ ሁሉም ይተባበር!!
ነፃ ያልወጣች ሠንደቅ
አዎ፤ አውሮፓዊው ቅኝ ገዢ ጣሊያን አድዋ ላይ ድል ሆኗል በ1888 ዓ/ም። በኢትዮጵያና ኢትዮጵያን በሚወክለው ቀስተ ደመናዊ ሠንደቅ ዓላማዋ ላይ ግን ከትውልድ የዘለለ ቂም ቋጥሮ የደማ ልቡን በመዳፉ ደግፎ በተቆረጠው ቋንጃው እያነከሰ አንድ እግሩን ኤርትራ ላይ ልብና ሌላ እግሩን ጣሊያን - አውሮፓ ላይ አድርጎና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ፍራንቺስኮ ክሪስፒን ከሥልጣን አባርሮ ድፍን ጣሊያን ሀዘን ተቀመጠ። አርባ ዓመት ሲታመምና ሲያገግም ኖረ። ጣሊያን በኢትዮጵያና በሠንደቋ ላይ ለአርባ ዓመት ያረገዘው ቂም ዱቼንና ፋሽስት ፓርቲን ወለደ። ለጣሊያን ትንሳዔ ኢትዮጵያ መሥዋዕት መሆን አለባት ሲል እነሆ ዱቼ በሮም አደባባይ ተጣራ። ሙሶሎኒ ኢትዮጵያን በመሥዋዕትነት ለተዋረደችው ጣሊያን ትንሳኤ አቀረበ። አውሮፓ አጨበጨበ፤ ቪቫ ዱቼ ሲል ደገፈ። ጥቁር ለባሽ የፋሽስት ጦር ከጣሊያን ጫፍ እስከ ጫፍ … [Read more...] about ነፃ ያልወጣች ሠንደቅ
የህወሓት ዕቅድ፥ የእስር ማዘዣው እና የብአዴን ጆከር!
በእርግጥ ፖለቲካ ማለት ልክ "Bicycle" ነው። ሁልግዜም በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል መሽከርከር አለበት። ለውጥና መሻሻል ከቆመ ልክ እንደ "Bicycle" ፖለቲካዊ ስርዓቱም ተንጋሎ ይወድቃል። ህወሓት የማይለወጥ የፖለቲካ ቡድን ከመሆኑም በላይ ሌሎች እንዳይለወጡ የሚያደርግ ፀረ-ለውጥ ቡድን ነው። ስለዚህ ይህ ቆሞ-ቀር ቡድን የሌሎችን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ያለመታከት ጥረት ያደርጋል። በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥና መሻሻል ጠፍቶ መንግስታዊ ስርዓቱ ለመውደቅ እየተንገዳገደ ባለበት ወቅት እንኳን ህወሓት በኦህዴድ መሪነት የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል ላይ-ታች ሲል ነበር። አዲሱ የኦህዴድ አመራር ወደ ስልጣን እንደመጣ የወሰደው የለውጥ እርምጃ ፀረ-ለውጥ አቋም ከሚያራምደው የህወሓት ቡድን ራሱን ማላቀቅ ነው። በዚህ ረገድ የክልሉ ፕሬዚዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ … [Read more...] about የህወሓት ዕቅድ፥ የእስር ማዘዣው እና የብአዴን ጆከር!
ከሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ግልጽ ውይይትና ድርድር ሊደረግ ይገባል!
ዶ/ር አብይ የኦህዴድ ጽ/ቤት አላፊ በነበሩበት ወቅት ኦህዴድ ሁሉንም ሰላም ወዳድ ዜጋን ያስደሰተ ጥሪ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ላሉ ተቃዋሚዎች አቅርቦ ነበር። ይህ ጥሪ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የቀረበ በመሆኑ አንዳንድ በኦሮሞ ስም የሚታገሉ በውጪም በውስጥም ያሉ ተቃዋሚዎች በደስታ የተቀበሉት ነበር። ነገር ግን ይህ የኦህዴድ ጥሪ ምንም ያህል ለሀገሪቱ ሰላም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ቢሆንም ያለ ኢህአዴግ አሺታ ሊሳካ እንደማይችል የገመቱ ነበሩ። ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን በመጡ የመጀመሪያዋ ቀን በፓርላማው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ኦህዴድ ለተቃዋሚዎች ካቀረበው ጥሪ ጋር ተመሳሳይነት ያለውን ሃሳብ ተናግረው ነበር። ጠቅላይ ሚንስተሩ በኢትዮጵያ ጉዳይ “በተለያየ መልኩ” ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ሀይሎች ጋር አብሮ ለመስራት እንደሚፈልጉ ጠቅሰው ነበር። የዲስፖራው ፖለቲካ ብዙውን … [Read more...] about ከሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ግልጽ ውይይትና ድርድር ሊደረግ ይገባል!
“EFFORTን” መውረስ የኢኮኖሚውን ጥገኛ ተውሳክ እንደማስወገድ ነው!
ትላንት በፌስቡክ ገፄ ላይ የትእምት (EFFORT) ድርጅቶች በመንግስት መወረስ እንዳለባቸው ለመጠቆም ሞክሬ ነበር። ለዚህ ያቀረብኳቸው ምክንያቶችና ማስረጃዎች እንዳሉ ሆነው እነዚህን ድርጅቶች መውረስና ወደ ግል እንዲዛወሩ ማድረግ ምን ፋይዳ አለው? በሀገሪቱ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ላይ ምን ዓይነት አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል? እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በዝርዝር መመልከት ያስፈልጋል። በቅድሚያ ግን ስለ ትእምት (EFFORT) ድርጅቶች አጠቃላይ ባህሪ የተወሰነ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል። ለዚህ ደግሞ ከትእምት (EFFORT) ድርጅቶች የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካን እንደ ማሳያ በመውሰድ እንመልከት። በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አመራር ሙያ (Business Administration) የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት በምማርበት ወቅት “Operation Management” የሚባለውን ኮርስ … [Read more...] about “EFFORTን” መውረስ የኢኮኖሚውን ጥገኛ ተውሳክ እንደማስወገድ ነው!
EFFORTን መውረስ ለዶ/ር አብይ ቀዳሚ ተግባር ነው!!!
ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው የተመረጡ ዕለት ባደረጉት ንግግር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት እና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ለማረጋገጥ፣ በተለይ አዳዲስ ባለሃብቶችን እንዲፈጠሩ ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል። ይህን እውን ለማድረግ የጠ/ሚኒስትሩ የመጀመሪያ ተግባር መሆን ያለበት #EFFORTን በመውረስ ወደ ግል ባለሃብቶች ማዘዋወር (privatize) ነው። ምክንያቱም፣ 1ኛ) ለሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ልማትና እድገት፣ በተለይ አዳዲስ ባለሃብቶችን በመፍጠሩ ረገድ ዋና እንቅፋት መሆናቸው በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ በዝርዝር ተገልጿል። 2ኛ) #በአርከበ_ዕቁባይ መሪነት ተግባራዊ የተደረገው የሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ፖሊስ የEFFORT ድርጅቶችን ተጠቃሚ በማድረግና የግል ቢዝነስ ተቋማትን እድገት በማቀጨጭ ላይ የተመሠረተ ስለመሆኑ ይህን ፅሁፍ ያንብቡ። 3ኛ፦ የEFFORT መነሻ ካፒታል 100ሚሊዮን … [Read more...] about EFFORTን መውረስ ለዶ/ር አብይ ቀዳሚ ተግባር ነው!!!
“ቃል ጉልበት አለው፤ ይተክላል ይነቅላል፤ ትውልድ ይፈጥራል ትውልድ ያጠፋል፤ ፍቅር ይዘራል ጥላቻ ይዘራል”
“ቃል ካልወጣ በአእምሮ ውስጥ ቢብሰለሰል ብቻውን ሀሳብ ሊሆን አይችልም።” ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የኮርያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የደቡብ ኮርያው ፕሬዚዳንት ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው አስቀድሞ ኢንተርቪው ሊያደርጉኝ መጥተው ከብዙ ውይይት በሁዋላ “እንዴት ስለስፔስ ታስባላችሁ? እናንተ ድሃ ሀገር ናችሁ። ህዝባችሁ አግራሪያን (አርሶ አደር) ስለሆነ ማሰብ ያለባችሁ አግሪካልቸር እንዴት መሻሻል እንዳለበት አይደለም እንዴ?” ብሎ በጣም ደፋር ወጣት ጋዜጠኛ ጠየቀኝ። የመለስኩለት መልስም እንዲህ ነበር፤- እናንተን ነፃ ለማውጣት ወደ ኮርያ ስንዘምት ጠቅላላ ጦርነቱን የመራው ሰውዬ ጄኔራል ማካርቲ ይባላል። አራት ኮከብ ማዕረግ ያለው የአሜሪካን ጄኔራል ነው። ጄኔራል ማካርቲ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጃፓንን ለመውረር ጦር አዝምቶ የገባና የኮርያ የርስ በርስ ጦርነት ሲነሳ … [Read more...] about “ቃል ጉልበት አለው፤ ይተክላል ይነቅላል፤ ትውልድ ይፈጥራል ትውልድ ያጠፋል፤ ፍቅር ይዘራል ጥላቻ ይዘራል”
ቋንቋን በቋንቋ
ስለ ቋንቋ የተለያዩ እይታዎች መኖራቸው አዲስ አይደለም። የሚገርመው ይልቅ፣ ብዙዎች እንደ ሹምና አቡን ትእዛዝ ሲሰጣጡ ማየት ነው። ትእዛዙን ማን፣ እንዴት ይፈጽም? እይታዎችን ማቀራረብና መተግበርስ ይቻላል? መቸ በምን ቅደም ተከተል? ወዘተ። ይህን ያሰቡበት ቢኖሩ ድምጻቸው አልተሰማም። የራስን አጉልቶ፣ የሌላኛውን ማድበስበስ የተለመደ በመሆኑ፣ የጽሑፌ ይዘት ለያንዳንዱ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፣ የተዘነጉ ጥቃቅን አሳቦችን ማነጋገር ይሆናል። ቋንቋ ቢያንስ ሀ/ ድንበር ተሻጋሪ መሆን ይኖርበታል፤ አማርኛ ተናጋሪ፣ እርስ በርሱ ብቻ ከሆነ፣ ከኬላው ውጭ በምን ይግባባል? ለ/ ድንበር ተሻግረን እንግሊዝኛ፣ አማርኛ፣ ወዘተ፣ የቆነጠርን ቢያንስ አኗኗራችንን ለማሻሻል እንደ ሆነ አንርሳ ሐ/ ቋንቋ ተሻጋሪ እንዲሆን፣ ድልድይ የሚሆን ቋንቋ ይሻል። አማርኛ ድልድይ ነው። እርግጥ፣ ሁሉን ቋንቋ ማወቅ … [Read more...] about ቋንቋን በቋንቋ










