• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

EFFORTን መውረስ ለዶ/ር አብይ ቀዳሚ ተግባር ነው!!!

April 26, 2018 04:43 pm by Editor 4 Comments

ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው የተመረጡ ዕለት ባደረጉት ንግግር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት እና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ለማረጋገጥ፣ በተለይ አዳዲስ ባለሃብቶችን እንዲፈጠሩ ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል። ይህን እውን ለማድረግ የጠ/ሚኒስትሩ የመጀመሪያ ተግባር መሆን ያለበት #EFFORTን በመውረስ ወደ ግል ባለሃብቶች ማዘዋወር (privatize) ነው። ምክንያቱም፣

1ኛ) ለሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ልማትና እድገት፣ በተለይ አዳዲስ ባለሃብቶችን በመፍጠሩ ረገድ ዋና እንቅፋት መሆናቸው በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ በዝርዝር ተገልጿል።

2ኛ) #በአርከበ_ዕቁባይ መሪነት ተግባራዊ የተደረገው የሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ፖሊስ የEFFORT ድርጅቶችን ተጠቃሚ በማድረግና የግል ቢዝነስ ተቋማትን እድገት በማቀጨጭ ላይ የተመሠረተ ስለመሆኑ ይህን ፅሁፍ ያንብቡ።

3ኛ፦ የEFFORT መነሻ ካፒታል 100ሚሊዮን ዶላር ሲሆን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጲያ ህዝብ እና የአለም አቀፉ ማህብረሰብ ላይ በተፈፀመ #ህገ_ወጥ_ዘረፋ የተገኘ ነው። ይህን ማያያዣ በመጫን ዝርዝሩን ማንበብ ይቻላል።

4ኛ) የEFFORT ድርጅቶች ጥራት ያለው ምርት በማቅረብ ተወዳዳሪ ከመሆን ይልቅ ከ47ሺህ በሚበልጡ ሰራተኞቹ ላይ የመብት ጥሰት የሚፈፀምባቸው የጭቆና መሣሪያዎች ናቸው።

ማጠቃለያ

*1ኛ እና 2ኛ ላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች መሠረት EFFORTን መውረስ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት ከማስቀጠል አንፃር ቀዳሚ ተግባር ነው።

** 3ኛ እና 4ኛ ላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች መሠረት EFFORTን መውረስ ከሞራል አንፃር አግባብ ነው።

ስለዚህ EFFORTን መውረስ ለዶ/ር አብይ ቀዳሚ ተግባር ነው!!!

ስዩም ተሾመ

ምንጭ፤ Seyoum Teshome facebook

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: effort, Full Width Top, Middle Column, pravatize, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    April 27, 2018 10:00 pm at 10:00 pm

    ባይሆን ሃገራቸውን ይገንቡበት ብትል ያምራል!!

    Reply
  2. በለው! says

    April 28, 2018 05:49 pm at 5:49 pm

    ኤፈርት ቢወረስ ባይወረስ የትግራይ ህዝብ አይሞቀው አይበርደው!
    ኢፈርት የትግራይ ህዝብ አይደለም! ሆኖም አያቅም! ህወሓት የሚባል የማፍያ የገዳዮች ስርአት እስካለ ድረስ ኢፈርት ለወደፊቱም የትግራይ ህዝብ አይሆንም! ስለዚህ ኢፈርት ቢወረስ ባይወረስ ለትግራይ ህዝብ የሚጨምርለትም የሚቀንስለትም ሳንቲም የለም። ኢፈርት ቢወረስ ፋብሪካው ተነቅሎ አዲስ አበባ ወይንም ሌላ ቦታ ይሄዳል ማለትም አይደልም፣ ኢፈርት መውረስ ማለት በኢፈርት ስም የሚነገድበት የትግራይ ህዝብ የትርፉ ተካፋይ እና ባለቤት ማድረግ ማለት ነው!!! በሌሎች ክልልሎች የሚገኙ የኢፈርት ድርጅቶችም ቢወረሱ ህዝቡን የትርፉ ተካፋይ ማድረግ ማለት ነው፣ ጥረት እና ድንሾ መውሰድ ይቻላል። በመጀመርያ ደረጃ የኢፈርት መቋቋም ትርጉሙ ምንድነው? ኢፈርት የተቋቋመበት ዋና አላማ.
    1. ለትግራይ ህዝብ ስራ በመፍጠር እድሜ ልኩ የህውሓት ተገዢ ማድረግ እና ጸረ ህወሓት እንዳይነሳ ማድረግ ነው። በኢፈርት ድርጅቶች የተቀጠሩ ሰራተኞች ህወሓትን መቃወም አይችሉም፣ ከተቃወሙ ከስራ ይባረራሉ፣ ከስራ ከተባረሩ ገቢ አልባ ይሆናሉ፣ ገቢ አልባ ከሆኑ ቤተሰብ የማስተዳደር አቅም አይኖራቸውም፣ ባጭሩ ሂወታቸው አደጋ ላይ ነው፣ ሂወታቸው አደጋ ላይ ላለማውደቅ ህወሓትን ከመቃወም ይልቅ ዝምታን ይመርጣሉ። የኢፈርት በትግራይ መገንባት ዋናው አላማ ይህ ነው። ጸረ ህወሓት ተቃውሞን ማፈን፣ ይህ ደግሞ ላለፉት ሃያ አመታት በተግባር ታይተዋል።
    2. ህወሓት የተባለ የቤተሰብ ስብስብ በኢኮኖሚ ማደለብ እና የቤተሰብ ስብስብ የሆነውን ህወሓት እድሜ ልኩ ስልጣን ላይ እንዲኖር ወይንም ገዢ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ ነው። የህውሓት ባለስልጣናትን የአገር ሃብት እንዲዘርፉ መንገድ መክፈት እና ልጆቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በኢፈርት ገንዘብ በውጭ አገር እንዲማሩ፣ እንዲታከሙ፣ ቤት እንዲገዙ፣ እንዲኖሮ እና የውጭ የባንክ ሂሳብ ከፍተው የመንግስት ለውጥ ሲመጣ አገር ጥለው መኖር እንዲችሉ ማድረግ ነው።
    3. በትግራይ ተወዳዳሪ የሆነ ኢንቨስተር እንዳይገባ ማድረግ፣ ነጋዴዎች ተወዳድረው ትልቅም ትንሽም ፋብሪካ እንዳይሰሩ ማድረግ፣ ባጭሩ የኢፈርት አላማ ትግራይ በመኖፖል መግዛት፣ ትንሹን ነጋዴ ወይንም ሃብታም በትልቁ ኢፈርት በተባለ ድርጅት ተወዳዳሪ እንዳይሆን ማድረግ ኢፈርት አላማው ይህ ነው። ኢፈርት አላማው በሌሎች ኢንቨስተሮች ትግራይ ውስጥ ስራ እንዳይፈጠር ማድረግ እና ነጻነት ያለው ዜጋ እንዳይፈጠር ማድረግ ነው።
    ታድያ የኢፈርት ድርጅቶች ግብ ይህ ከሆነ፣ ኢፈርት ቢወረስ ባይወረስ ለትግራይ ህዝብ ምኑ ነው? ከኢፈርት ድርጅቶች የተጠቀመ የትግራይ ህዝብ ነው የሚል የትግራይ ተወላጅ ካለ ኢፈርት ካለው ትርፍ ምን ያክል እንደተከፈለው ይንገረን? በኢፈርት ድርጅቶች እንደ ዜጋ፣ እንደ ዜጋ ስል እንደ ትግራዋይ በችሎታው እና በትምህርት ደረጃው ከኢፈርት እና የህወሓት ባለስልጣናት ዘመድ አዝማድ ጋር ተወዳድሮ የተቀጠረ ትግራዋይ ማን ነው?
    ህወሓት ኢፈርት የትግራይ ህዝብ ነው ስትል፣ ኢፈርት የትግራይ ህዝብ አይደለም ብሎ ሲከራከር የነበረ አሁን የኢፈርትን መወረስ የሚያስቆጣው ከሆነ እሱ ራሱ ኢፈርት ነው፣ ኢፈርት ማለት ደግሞ ህወሓት ማለት ነው፣ ስለዚህ የኢፈርት መወርስን የሚያስቆጣው ትግራዋይ ካለ እሱ ራሱ ህወሓት ነው። በኢፈርት ድርጅቶች የተመረቱ ምርቶች ትግራይ ውስጥ በእጥፍ እየተሸጡ አዲስ አበባ እና አዋሳ በርካሽ እየተሸጡ ኢፈርት አይወረስም የሚል ትግራዋይ ካለ እሱ ራሱ ኢፈርት መሆን አለበት። የህውሓት ባለስልጣናት እድሜ ለማራዘም ብለህ ኢፈርት አይወረስም ብለህ መከራከር ያስተዛዝባል፣ ሰከን ረጋ በል፣ ኢፈርት የትግራይ ህዝብ አይደለም ሆኖም አያቅም፣ ኢፈርት የስብሓት ነጋ እና ቤተሰቦቹ ነው!!! (ናትናዔል አስመላሽ)

    Reply
  3. Hassen says

    April 29, 2018 09:28 am at 9:28 am

    This application is very beneficial

    Reply
  4. Mulugeta Andargie says

    May 10, 2018 06:17 pm at 6:17 pm

    አገራቸውን ስል ኢትዮጵያን ማለቴ ነው።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule